Tenders

 

Type: Services

 

Organization: ሕብረት ባንክ ኢ.ማ በደ/ብ/ብ/ሕ/ክልላዊ መንግስት

Dead Line: 2016-11-21

 

Tender Detail:

 

 


ሕብረት ባንክ ኢ.ማ በደ/ብ/ብ/ሕ/ክልላዊ መንግስት በሀዋሳ ከተማ አዲስ ከተማ ክ/ከተማ ደካ ቀበሌ 01 የቤት ቁጥር….. የሆነውን እና ስፋቱ 300 ካ.ሜ የሆነ መጋዘን የጨረታ መነሻ ዋጋው መነሻ ዋጋው ብር 5000 /አምስት ሺህ/ ሆኖ በጨረታ አወዳድሮ ማከራየት ይፈልጋል፡፡


1. ተጫራቾች ይህ የጨረታ ጥሪ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ከ2(ሁለት) ቀናት በኃላ ማለትም ከጥቅምት 28 ቀን 2009 ዓ.ም ጀምሮ የማይመለስ ብር 100 (አንድ መቶ) በመክፈል የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡

2. የጨረታ ሰነዱን ሐዋሳ ከተማ በሚገኙበት የባንኩ ዓረብ ሰፈር ቅርንጫፍ እና ሐዋሳ ቅርንጫፍ በመገኘት መግዛት ይችላል፡፡


3. ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ ተ.እ.ታን የሚያካትት ስለመሆኑ በግልፅ ማስፈር አለባቸው፡፡


4. ተጫራቾች በጨረታው መመሪያው መሰረት የጨረታ ሰነዱን ሞልተው ሕብረት ባንክ ዓረብ ሰፈር ቅርንጫፍ እና ሐዋሳ ቅርንጫፍ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡


5. እያንዳንዱ የመጫረቻ ሰነድ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ መቅረብ አለባቸው፡፡



6. ተጫራቾች ጨረታው ከወጣበት ቀን ከጥቅምት 28 ቀን 2009 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ህዳር 12 ቀን 2009 ዓ.ም 10፡00 (አስር) ሰዓት ድረስ የመጫረቻ ሰነዳቸውን በባንኩ ዓረብ ሰፈር ቅርንጫፍ እና ሐዋሳ ቅርንጫፍ ማስገባት ይችላሉ፡፡


7. ጨረታው ህዳር 13 ቀን 2009 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 (አራት ሰዓት) በባንኩ ዓረብ ሰፈር ቅርንጫፍ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡


8. በጨረታ ሰነዱ ላይ የተገለፀውን መመሪያ ያልተከተለ ተጫራች ከውድድር ሊታገድ ይችላል፡፡


9. ባንኩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡


ለበለጠ መረጃ፡- በስልክ ቁጥር 0114 65 52 22 የውስጥ መስመር 299/250 ወይም 0114 16 97 57 እና ሐዋሳ ከተማ በሚገኘው ሕብረት ባንክ ሐዋሳ ቅርንጫፍ 046 220 43 39/046 220 42 68 ወይም ሕብረት ባንክ ሐዋሳ ዓረብ ሰፈር ቅርንጫፍ 046 212 26 30/046 212 26 33 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡