Tenders

 

Type: Garment

 

Organization: ናይል ኢንሹራንስ ኩባንያ አ.ማ.

Dead Line: 2017-02-14

 

Tender Detail:

 

 



ናይል ኢንሹራንስ ኩባንያ አ.ማ. የሠራተኞች የደንብ ልብስ (Uniform) በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል:: ስለሆነም መጫረት የሚፈልጉ፣

1. ተጫራቾች ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና የተጨማሪ እሴት ታክስ የተመዘገቡበትን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው::

2. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ብር 10,000.00 በባንክ በተረጋገጠ ቼክ (ሲፒኦ) ወይም ባንክ ጋራንቲ ማስያዝ ይኖርባቸዋል::

3. ተጫራቾች ስለጨረታው የሚገልፀውን ሠነድ የማይመለስ ብር 5ዐ /ሃምሣ/ በመክፈል ዘወትር በሥራ ሰዓት ናይል ኢንሹራንስ ኩባንያ አ.ማ. ዋናው መ/ቤት የሀብት ሥራ አመራር መምሪያ /3ኛ ፎቅ/ በመምጣት መግዛት ይችላሉ::

4. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ በሰም በታሸገ ኤንቬሎፕ እስከ የካቲት 6 ቀን 2ዐዐ9 ዓ.ም. 11፡ዐዐ ሠዓት ድረስ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል::

5. ጨረታው የካቲት 7 ቀን 2ዐዐ9 ዓ.ም. ከጠዋቱ በ3፡3ዐ ሠዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በኩባንያው ዋና መ/ቤት ይከፈታል፡:

 6. አንዱ ተጫራች በሌላው ዋጋ ላይ ተንተርሶ መጫረት አይችልም::

7. ኩባንያው ጨረታውን በከፊል ወይም በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::

አድራሻ፡- ናይል ኢንሹራንስ ኩባንያ አ.ማ. ዋናው መ/ቤት /ጎተራ/ የሀብት ሥራ አመራር መምሪያ /3ኛ ፎቅ/ የመ.ሣ.ቁ. 12836 የስልክ ቁጥር 0114-42 60 00 አዲስ አበባ