Tenders

 

Type: Building Materials

 

Organization: ኢትዮ-ሳሜል ኃ/የተ/የግ/ማህበር

Dead Line: 2017-02-16

 

Tender Detail:

 

 



 

ኢትዮ-ሳሜል ኃ/የተ/የግ/ማህበር በሻላ ሐይቅ ለሚያስገነባው ሎጅ የተለያዩ መጠንና ደረጃ ያላቸውን የብረት በርና መስኮቶችን ከነፍሬማቸው በጨረታ አወዳድሮ ማሠራት ይፈልጋል::


በመሆኑም፡-

- በተመሳሳይ የብረት በርና መስኮት ከነፍሬሙ ሥራ ልምድ ያለው - የታደሰ የሥራ ፈቃድ ማቅረብ የሚችል

- የመልካም ሥራ አፈፃፀም ማስረጃ ያለው

- የዘመኑን ግብር የከፈለ ለመሆኑ ማስረጃ ማቅረብ የሚችል

- ቦታው በመሄድ የበርና የመስኮቶቹን ርዝመትና ስፋት ለክቶ ዝርዝር መረጃውን ከቦታው ለመውሰድ የሚችል በዚህ ጨረታ መካፈል የምትፈልጉ ተጫራቾች በድርጅቱ ጽ/ቤት አድራሻ አዲስ አበባ ወሎ ሰፈር ወንጌላዊት ህንፃ ፊት ለፊት በመምጣት የጨረታ ሰነዱን ገዝታችሁ የሥራ ዝርዝሩን ሰነድ ኦርጅናልና ፎቶ ኮፒ ለየብቻ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ማቅረብ የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን::

  • ጨረታው የሚቆይበት ጊዜ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ8 ተከታታይ የሥራ ቀናት ይሆናል
  • የጨረታ ሰነዱ ዋጋ ብር 100 (አንድ መቶ ብር)
  • ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ማስያዣ (Bid Bond Guarantee) ለጨረታ ከገቡት ዋጋ 1(አንድ በመቶ) ያላነሰ በተረጋገጠ ማቅረብ የሚችል
  • ተጫራቾች ለጨረታው ሥራ አፈፃፀም የጨረታውን ዋጋ 10% የሆነ (Performance Bank Guarantee) ማቅረብ ይኖርበታል
  • ለቅድመ ክፍያ ዋስትና የጨረታውን ዋጋ 30% (Advance Payment Guarantee) ከባንክ ያቀርባል::

ማሳሰቢያ

  • • ማኅበሩ ሌላ አማራጭ ካገኘ በጨረታው አይገደድም
  • • ጨረታው የሚከፈተው የካቲት 19/2009 በ4፡00 ሰዓት በጽ/ቤቱ ይሆናል
  • • ሥራው ተጠናቆ ርክክብ የሚፈጸምበት ቀን አሸናፊው ውሉን ከፈረመበት ቀን ጀምሮ በሁለት ወር (61ኛው ቀን) ላይ ይሆናል::

 • በዚህ ቀን ካላለቀ ተጫራቹ ባቀረበው የአፈፃፀም ዋስትና መሠረት ተጠያቂ ይሆናል:: ለበለጠ መረጃ፡- 0911-20 24 80 ወይም 0911 41 28 30/ 0911 00 28 05 ይደውሉ::