Tenders

 

Type: Construction

 

Organization: የደ/ብ/ብ/ህ/ክ/መንግሥት በወላይታ ዞን የቦሎሶ ወረዳ ፋይ/ኢ/ል/ጽ/ቤት

Dead Line: 2017-03-12

 

Tender Detail:

 

 

 

 

በደቡብ ብ/ብ/ህ/ክ/መንግሥት በወላይታ ዞን የቦሎሶ ሶሬ ወረዳ ፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ጽ/ቤት በ2009 መደበኛ ካፒታል በጀት በወረዳችን ምንጭ የግንባታ ቁሳቁስ ከራሱ አቅርቦ የሚሠራ ባለሙያ አወዳድሮ ለማስገንባት ይፈልጋል፡፡

በዚሁ መሠረት wwc-6 እና ከዚያ በላይ ተቋራጮች የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያለው የዘመኑን ግብር የከፈለና ያሳደሰ የቲንና ቫት ተመዝጋቢ የሆነ ማህበር ወይም ግለሰብ መወዳደር ይችላል፡፡

  1. የጨረታ ማስከበሪያ ብር 3000 /ሦስት ሺህ/ በባንክ የተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ ወይም በባንክ ጋራንቲ ማስያዝ ይኖርበታል፡፡
  2. ተጫራቾች የጨረታውን ዝርዝር የሚያሳይ የጨረታ ሰነድ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ተከታታይ በ21 / ሃያ አንድ / የሥራ ቀናት ውስጥ በቦሎሶ ሶሬ ወረዳ ገቢዎች ባ/ሥ/ን/ቅ/ጽ/ቤት ድረስ ቀርበው የማይመለስ ብር 50 /ሀምሳ/ በመክፈል ሰነዱን ከወረዳው ፋይ/ ኢ/ል/ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 8 ማግኘት ይችላሉ፡፡
  3. ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሀሳባቸውን ታሸጎ ኤንቨሎፕ ዋናውንና ኮፒ በመለየት ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ 21  ሃያ አንድ / የሥራ ቀናት ለጨረታው በተዘጋጀው ሣጥን ማስገባት የሚችሉ ሲሆን፣ 21ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ጨረታው የሚታሸግ ሆኖ በዕለቱ 4፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች / ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
  4. 21ኛው ቀን ሰንበት/የበዓላት ቀን/ ከዋለ በማግስቱ ይሆናል፡፡
  5. አሸናፊው የውል ማስከበሪያ ያሸነፈበት ጠቅላላ ዋጋ 10% ማስያዝ ይኖርበታል፡፡
  6. ተጫራቾች / ህጋዊ ወኪሎቻቸው በሰዓቱ ያለመገኘት ጨረታውን ከመክፈት አያስተጓጉልም፡፡
  7. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ በጨረታው አይገደድም፡፡
  8. ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 046-552-0373 / 046-552-0409 መጠቀም ይችላሉ፡፡
  9. የደ/ብ/ብ/ህ/ክ/መንግሥት በወላይታ ዞን የቦሎሶ ወረዳ ፋይ/ኢ/ል/ጽ/ቤት