Tenders

 

Type: Construction

 

Organization: ከተማ ልማትና ቤቶች ቢሮ

Dead Line: 2017-03-06

 

Tender Detail:

 

 

 

 

ደ/ብ/ብ/ህ/ክ/መንግሥት ከተማ ልማትና ቤቶች ቢሮ ሀዋሳ ከተማ ለሚገኘው የምክትል ርዕስ መስተዳድር መኖሪያ ጥገናና የጥበቃ ማማ ግንባታ ሥራ ሕጋዊ ተጫራቾችን አወዳድሮ ለማሠራት በመፈለጉ በክልሉ በኮንስትራክሽን ሙያ የተደራጁ የጥቃቅን እና አነስተኛ ማህበራትን አወዳድሮ በግልጽ ጨረታ ለማሠራት ይፈልጋል፡፡

በዚሁ መሠረት፡-

    1. ደረጃቸው GC/BC-9 እና ከዛ በላይ ያሉ ሥራ ተቋራጮች ማህበር

    2. ፍቃዳቸውንና የምዝገባ ሠርተፍኬታቸውን ለ2009 ዓ.ም ያሳደሱ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያላቸውና ለተጨማሪ እሴት ታክስ የተመዘገቡና የታክስ መለያ ቁጥር ያላቸው

    3. ተጫራቾች ለሥራው የተዘጋጀው ሰነድ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ለእያንዳንዱ ዶክመንት የማይመለስ ብር 50/ሃምሳ ብር/ በመክፈል ዘወትር በሥራ ቀናት ከቢሮ ግዥ ፋይ/ንብ/አስ/የሥራ ሂደት በመቅረብ መግዛት ይችላሉ፡፡

    4. ተጫራቾች ጨረታ ፋይናንሻል ዶክመንት አንድ ኦርጅናል እና ሁለት  ፎቶ ኮፒ እያንዳንዳቸውን በሰም በማሸግ ማቅረብ አለባቸው፡፡

    5. ተጫራቾች ከሚያቀርቡት አጠቃላይ ዋጋ 5,000 /አምስት ሺህ ብር/ የጨረታ ዋስትና በባንክ በተጋገጠ ቼክ (CPO) ኦሞ ማይክሮ ዋስትና ወይም በባንክ ዋስትና ደብዳቤ ማቅረብ አለባቸው፡፡

    6. ጨረታው በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡00-6፡00 ሰዓት ከተማ ልማትና ቤቶች ቢሮ ለዚሁ በተዘጋጀው ጨረታ ሳጥን በመክተት ይታሸግና በዚያው ዕለት ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ተጫራቾችና ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡

    7. 16ኛው ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በቀጣይ የሥራ ቀን የሚከናወን ይሆናል፡፡

    8. መ/ቤቱ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

    9. ከተማ ልማትና ቤቶች ቢሮ

    10. ሀዋሳ