Tenders

 

Type: Agricultural Products

 

Organization: ብሔራዊ የትምባሆ ድርጅት /ኢትዮጵያ / አ.ማ

Dead Line: 2017-03-21

 

Tender Detail:

 

 

 

 

ብሔራዊ የትምባሆ ድርጅት /ኢትዮጵያ / አ.ማ በአዋሳና ብላቴና ለሚገኙ የትምባሆ እርሻ ልማቶች የትምባሆ ቅጠል መጥበሻ አገልግሎት የሚውል 5250 ሜትር ኩብ የማገዶ እንጨት በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

በመሆኑም ከዚሁ ቀጥሎ የተዘረዙትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾችን ለውድድር

  1. ተጫራቾች ለዘመኑ የታደሰ የንግድ ፈቃድና የግብር ከፋይነት የምስክር ወረቀት ኦሪጂናልና ፎቶ ኮፒ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡

  2. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ የማይመለስ ብር 100.00/ አንድ መቶ ብር/ መክፈል የጨረታው ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ አዲስ አበባ ዋናው መስሪያ ቤት የአገር ውስጥ ግዥ ዋና ክፍል ቢሮ ቁጥር 008 በሥራ ሰዓት መግዛት ይችላሉ፡፡ እንደዚሁም በአዋሳ ብላቴና ወላይታ በሚገኙት ድርጅቱ እርሻ ልማቶች ሰነዶቹን መግዛት ይችላል፡፡

  3. ተጫራቾች በጨረታ ዋስትና ማስከበሪያ /ቢድ ቦርድ/ የጠቅላላው ዋጋው ከ1% ያነነሰ በባንክ በተመሰከረ ቼክ /ሲፒኦ/ ወይም የባንክ ዋስትና ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡

  4. ተጫራቾች የማገዶ እንጨቱን የሚሸጠብትን ዋጋና ሌሎች ዝርዝር ሁኔታዎችን በመግለጽ ዋጋቸውን እስከ የካቲት 23 ቀን 2009 ዓ.ም ከቀኑ 8፡45 ሰዓት ድረስ በብሔራዊ ትምባሆ ድርጅት /ኢትዮጵያ/ አ.ማ መዝገብ ቤት ማስገባት አለባቸው፡፡ የመሸጫ ዋጋ ከጨረታው መክፈቻ ቀን ጀምሮ ለ3 /ሦስት / ወር የፀና መሆኑን መግለጽ ይኖርባቸዋል፡፡

  5. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የካቲት 24 ቀን 2009 ዓ.ም ከቀኑ 9፡00 ሰዓት ላይ በዋናው መ/ቤት የስብሰባ አዳራሻ ይከፈታል፡፡

  6. አሸናፊው ተጫራች የጠቅላላ ዋጋ 10% የመልካም ስራ አፈፃፀም ማስያዝ ይጠበቅበታል፡፡

  7. አሸናፊው ተጫራች የጨረታው ውል በተፈረመ በሁለት ሣምንት ጊዜ ውስጥ የማገዶ እንጨቱን ለየእርሻ ልማቶች ማቅረብ መጀመር ይኖበታል፤

  8. ድርጅቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

  9. አሸናፊ ተጫራቾች ቅድሚያ ክፍያ ከጠየቁ የቅድሚያ ክፍያውን ሙሉ ዋጋ በባንክ ጋራንቲ ወይም ሲፒኦ ያቀርባል፡፡

  10. ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር፡ 0115 51 00 44

  11. ብሔራዊ የትምባሆ ድርጅት ኢትዮ/ አ.ማ