Tenders

 

Type: Construction

 

Organization: በኢትዮጵያ ኤርፖርቶች ድርጅት የአዲስ አበባ ቦሌ ዓለም አቀፍ ኤርፖርት አስተዳደር

Dead Line: 2017-03-09

 

Tender Detail:

 

 

 

የኢትዮጵያ ኤርፖርቶች ድርጅት አዲስ አበባ ቦሌ ዓለም አቀፍ ኤርፖርት ተርሚናል 2 ውስጥ ለሆቴሎች ወይም ለቱሪስት ኤጀንቶች ኢንፎርሜሽን አገልግሎት መስጫ ቡዝ የተዘጋጁ ቦታዎችን በጨረታ አወዳድሮ ለአራት ዓመት የቆይታ ጊዜ ለማከራየት ተጫራቾችን ይጋብዛል፡፡

ስለሆነም፡-

  1. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ የዘመኑን ግብር የተከፈለበትን ማስረጃ ለሚጫረቱበት አገልግሎት ዘርፍ ሕጋዊና የታደሰ ሕጋዊ ፈቃድ እና የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሠረተፍኬት ማስረጃዎች ኮፒ ከጨረታ ሰነዱ ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡ ዋናውንም ማስረጃ ጨረታ ሰነድ ሲገዙ እና ጨረታው ሲከፈት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡

  2. ተጫራቾች የማይመለስ በር 100.00 /አንድ መቶ ብር/ በመክፈል ከኢትዮጵያ ኤርፖርቶች ድርጅት ዋጋ መ/ቤት ምድር ቤት ከሚገኘው ካሸር ቢሮ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፣

  3. ተጫራቾች ለእያዳንዱ ይዞታ የጨረታ ሰነድ በመግዛት ከአንድ በላይ ለሆነ ይዞታ (ቦታ) መወዳደር ይችላሉ፡፡

  4. በጨረታው የሚካፈል ማንኛውም ተጫራቾች ለሚጫረቱበት እያንዳንዱ ይዞታ የጨረታ ማስከበሪያ (Bid Bond) ብር 10000 /አሥር ሺህ ብር/ ለ120 ቀናት ፀንቶ የሚቆይ በባንክ በተረጋገጠ ቼክ (CPO) ወይም የባንክ ዋስትና በ’ ኢትዮጵያ ኤርፖርቶች ድርጅት የአዲስ አበባ ቦሌ ዓለም አቀፍ ኤርፖርት አስተዳደር “ ስም አዘጋጅቶ ማቅረብ ይኖርባታል፡፡ ከማንኛውም የኢንሹራንስ ድርጅት የሚቀርብ ዋስትና ተቀባይነት አይኖረውም፡፡

  5. ለጨረታ የተዘጋጁት ቦታዎች ብዛት 11 ሲሆን ተጫራቾች መጫረት የሚፈልጉትን ቦታ ለይተው መግለጽና የጨረታ ማስከበሪያ (Bid Bond) ማቅረብ ይኖርባቸዋል፣

  6. ተጫራቾች ጨረታውን ሰነድ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ እስከ የካቲት 30 ቀን 2009 ዓ.ም ጠዋቱ  4፡00 ሰዓት ድረስ በኢትዮጵያ ኤርፖርቶች ድርጅት ዋና መ/ቤት ምድር ቤት ከሚገኘው ኤርፖርት ኮንትራት አስተዳደር ማኔጅር ቢሮ ለዚሁ ተብሎ በተዘጋው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ ሆኖም ከጨረታው መዝጊያ ሰዓት በኃላ የሚቀርብ የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት አይኖረውም፡፡ ጨረታው የካቲት 30 ቀን 2009 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዕለቱ 4፡30 ሰዓት በድርጅቱ ዋና መ/ቤት የሰብሰባ አዳራሽ ይከፈታል፡፡

  7. ተጫራቾች ስለ ጨረታው ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ከፈለጉ የኢትዮጵያ ኤርፖርቶች ድርጅትን በስልክ ቁጥር፡- 011-6-65-04-49 ወይም በፋክስ ቁጥር 011 6 65 07 11 ወይም በፖ.ሣ.ቁ 90652 መጠየቅ ይችላሉ፡፡

  8. ድርጅቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

  9. በኢትዮጵያ ኤርፖርቶች ድርጅት የአዲስ አበባ ቦሌ ዓለም አቀፍ ኤርፖርት አስተዳደር