Tenders

 

Type: Stationery

 

Organization: ግሎባል ኢንሹራንስ ኩባንያ (አ.ማ)

Dead Line: 2017-03-18

 

Tender Detail:

 




ግሎባል ኢንሹራንስ ኩባንያ (አ.ማ) በውጭ ሀገር የሚታተሙ የ2010 ዓ.ም አጀንዳ (ኖርማል)፤ የጠረጴዛ ካላንደር እና ፖስት ካርድከነፖስታው በጨረታ አወዳድሮ ለማሠራት ይፈልጋል::በመሆኑም በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች በዘርፉ የተሠማሩ እና የንግድ ፈቃድ ፤ ቫት ተመዝጋቢ ፤ የግብር መለያ ቁጥር ምስክር ወረቀት እና ንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት እና የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆን ይኖርባቸዋል :: በኩባንያው የተዘጋጀውን የጨረታ ሠነድ ጎበና አባጥጉ መንገድ / ሶማሌ ተራ/ ከሚገኘው ዋና መ/ቤት 4ኛ ፎቅ ፋይናንስ መምሪያ በመቅረብ የማይመለስ ብር 50.00 በመክፈል መግዛትና መወዳደር ይችላሉ::

ተጫራቾች የጨረታ ሠነዱን ሞልተው ሲመልሱ ለጨረታ ማስከበሪያ የሚሆን ጠቅላላ ዋጋውን 15% በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ በማስያዝና በኤንቨሎፕ በማሸግ እስከ መጋቢት 09 2009ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ በዋናው መ/ቤት በሰው ሃይል ልማትና ንብረት አስተዳደር መምሪያ 4ኛ ፎቅ ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ገቢ ማድረግ ይጠበቅባቸዋል::

ጨረታው መጋቢት 09 2009ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት በኩባንያው መሰብሠቢያ አዳራሽ 2ኛ ፎቅ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል::

ኩባንያው የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::

ለበለጠ መረጃ ግሎባል ኢንሹራንስ ኩባንያ አ.ማ

በስልክ ቁጥር 0111565854 ወይም 0911469494 መጠየቅ ይችላሉ አዲስ አበባ ኢትዮጵያ