Tenders

 

Type: Services

 

Organization: ዓባይ ባንክ አ.ማ

Dead Line: 2017-03-28

 

Tender Detail:

 




ዓባይ ባንክ አ.ማ ለቅርንጫፎች ግልጋሎት የሚሆን የጥበቃ ቤት ሥራ የሚሰሩ ድርጅቶችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል:: ስለሆነም ፡-

  1.  የሥራው ዓይነት : የጥበቃ ቤት ሥራ

• ተጫራቾች የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የምዝገባ ምስክር ወረቀት፣የግብር ከፋይ ምስክር ወረቀት፣ታክስክሊራንስ እና የተጨማሪ እሴት ታክስ ማቅረብ ይኖርባቸዋል::

• ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 50 /ሃምሳ ብር ብቻ / በመክፈል ዓባይ ባንክ አ.ማ ዋና መስሪያ ቤት ፋሲሊቲና ግዥ ዳይሬክቶሬት ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ መጋቢት 19/2009 ዓ.ም ድረስ ዘወትር በስራ ሰዓት ማግኘት ይችላሉ::

• ተጫራቾች ከጨረታው በኃላ የሚመለስ የጨረታ ማሰከበሪያ ብር 5,000.00 (አምስት ሺህ ብር ብቻ) ማስያዝ ይኖርባቸዋል::

• ተጫራቾች ዋጋቸውን በታሸገ ኢንቨሎፕ እስከ መጋቢት 19/2009 ዓ.ም እስከ 6፡00 ሰዓት ድረስ ማስገባት አለባቸው::

• ጨረታው ተጫራቾች እና ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት መጋቢት 19/2009 ዓ.ም ከቀኑ በ8፡00 ዓባይ ባንክ አ.ማ ዋና መስሪያ ቤት ፋሲሊቲና ግዥ ዳይሬክቶሬት ይከፈታል::

• ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 011-554-97-41 እና 011-557-07-53 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል::

• ባንኩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::

ዓባይ ባንክ አ.ማ