Tenders

 

Type: Accounting / Audit

 

Organization: የኢትዮጵያ የባህር ትራንስፖርት ሎጂስቲክስ አገልግሎት ድርጅት

Dead Line: 2017-04-04

 

Tender Detail:

 

 



የኢትዮጵያ የባህር ትራንስፖርት ሎጂስቲክስ አገልግሎት ድርጅት የተለያዩ የደንብ ልብሶች ማቅረብ ከሚችሉ ድርጅቶች አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም በጨረታው ለመሳተፍ የተዘረዘሩትን ሁኔታዎች በማሟላት መጫረት የሚችሉ መሆኑን ይገልፃል፡፡

  1. በዘርፋ የተሰማሩ ድርጅቶች የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የተ.እ.ታ ሰርተፍኬት፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር እና የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው የሚሳይ መረጃ ማቅረብ አለባቸው፡፡
  2. የጨረታ  ፖስታው ከአንድ ኮፒ ጋር አንድ ላይ መቅረብ አለበት፡፡
  3. የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የጠቅላላ ዋጋውን 2% ያላነሰ በሲፒኦ ወይም በባንክ ጋራንቲ << የኢትዮጳያ የባሕር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ አገልግሎት ድርጅት>> በሚል ስም በማሰራት በማቅረብ መጫረት ይችላሉ፡፡
  4. ተጫራቾች በሁሉም ዓይነት ወይም የተወሰነ እቃዎች ላይ መጫረት ይችላለ፡፡
  5. የጨረታ ሠነዱን  የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ ብር) በመክፈል ለገሐር በሚገኘው የቀድሞው የማሪታይም ሕንፃ 1ኛ ፎቅ ላይ ቢሮ ቁጥር 106 በሚገኘው የፋክናንስ ክፍል ቢሮ መውሰድ ይቻላል፡፡
  6. ጨረታው << በኢትዮጵያ የባሕር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ አገልግሎት ድርጅት>> 8ኛ ፎቅ መጋቢት 26 ቀን 2009 ዓ.ም ከቀኑ በ8፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዘሁ እለት በ8፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ፖስታው ይከፈታል፡፡
  7. ከጨረታ መክፈቻው ቀንና ሳዓት በኃላ ዘግይቶ የሚወጣ የጨረታ ሠነድ ተቀባይነት የለውም፡፡
  8. ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ ጨረታውን የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  9. ስልክ ቁጥር፡ 011 554 97 81
  10. የኢትዮጵያ የባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ አገልግሎት ድርጅት