Tenders

 

Type: Multiple Items

 

Organization: በደ/ብ/ብ/ሕ/ክ/መንግሥት በካፋ ዞን የቢጣ ወረዳ ፋይ/ኢ/ል/ጽ/ቤት

Dead Line: 2017-04-09

 

Tender Detail:

 





በደ/ብ/ብ/ሕ/ክ/ መንግሥት በካፋ ዞን የቢጣ ወረዳ ፋይ/ኢ/ል/ጽ/ቤት ለወረዳው ውሃ/ማዕ/ኢነ/ጽ/ቤት በ2009 ዓ.ም በጀት ዓመት የምንጫ ውሃ ግንባታ / spring development and collection box/ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለማሠራት ይፈልጋል፡፡

በዚሁ መሠረት፡-

1. የዘመኑን ግብር የከፈሉና የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፍቃድ ያላቸው እና የቫት ተመዝጋቢ የሆኑ እንዲሁም በውሃ ግንባታ ፍቃድ ያላቸውና ደረጃቸው 9 እና ከዚያ በላይ የሆኑና WWC/water work constraction/ ፍቃድ ያላቸው፡፡

2. ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ 15 ቀን በአየር ላይ የሚቆይ ሲሆን ጨረታው በቀጣዩ የሥራ ቀን በ4:00 ሰዓት ላይ ታሽጎ በዕለቱ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ4፡30 በግልጽ ይከፈታል፡፡

3. ተጫራቾች ለእያንዳንዱ ክላስተር የጨረታ ማስከበሪያ 6000/ስድስት ሺህ ብር/ በCPO ወይም በካሽ ማስያዝ አለባቸው፡፡

4. ተጫራቾች የጨረታውን ዶክመንት በታሸገ ፖስታ ኦርጅናል እና ሁለት ፎቶ ኮፒ በማመሳከርና ለየብቻ በማሸግ ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በቢጣ ወረዳ ፋይ/ኢ/ል/ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 7 በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ዘውትር በስራ ሰዓት ማስገባት ያለባችሁ ሲሆን የጨረታ ማስከበሪያ CPO ከኦርጅናል ዶክመንት ጋር መታሸግ አለበት፡፡

5. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ከማይመለስ በብር 100 /አንድ መቶ ብር/ በመግዛት መወዳደር የምትችሉ ሲሆን ተጫራቾች በሌሎች ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይፈቀድም፡፡

6. ተጫራቾች በጨረታው /በዘርፋ ከዚህ በፊት የውሃ ግንባታ ሥራ ልምድ ያላቸውና መልካም አፈጻጸም ማቅረብ የሚችሉ፡፡

7. መ/ቤቱ በጨረታው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

8. ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር፡- 047-773-0018 / 04 /-773-0019 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡

9. ማሳሰቢያ፡- ተጫራቾች ጨረታው 2% ፐርሰንት ቅድመ ታክስ ታሳቢ ዊዝሆልድ የሚሆን መሆኑን እንገልጻለን፡፡

10. በደ/ብ/ብ/ሕ/ክ/መንግሥት በካፋ ዞን የቢጣ ወረዳ ፋይ/ኢ/ል/ጽ/ቤት