Tenders

 

Type: Construction

 

Organization: የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ

Dead Line: 2017-04-21

 

Tender Detail:

 

 

 

 

የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ ለኤርታሌ መገንጠያ-አህመድ ኢላ መንገድ ሥራ ፕሮጀክት ለአማካሪ መሐንዲሶች አገልግሎት ግዥ የሚውል supply and construction of prefabricated camp House የአገልግሎት ግዥ ለመፈጸም ተጫራቾችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

ስለሆነም፡-

  1. ተጫራቾች በመስኩ /ህጋዊ/ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና ለተጨማሪ እሴት ታክስ የተመዘገቡበትን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡

  2. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የሚያቀርቡት ገንዘብ በተጫራቾች መመሪያ ITB 16.1 ፣ 7.3 መሠረት መሆን አለበት፡፡

  3. ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ በጨረታ ሠነዱ በተጠቀሰው ብዛት መሠረት እንዲገነቡ ለታሰቡት ቤቶች በሙሉ መሆን ይኖርበታል፡፡

  4. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200.00 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል ዘወትር በሥራ ሰዓት ወሎ አካባቢ በሚገኘው የመከላከያ ኮንስትራክሽን ዋና መ/ቤት የግዥ የሥራ ሂደት ኬዝ ቲም ቢሮ መግዛት ይቻላሉ፡፡

  5. ተጫራቾች የሚወዳደሩባቸው ዋጋ በታሸገ ኢንቨሎፕ እስከ ሚያዝያ 13 ቀን 2009 ዓ.ም ከጥዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡

  6. ጨረታው ሚያዝያ 13 ቀን 2009 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡15 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በድርጅቱ መሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል፡፡

  7. ኢንተርፕራይዙ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

  8. አድራሻ፡- የመካላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ የቀጥታ ስልክ ቁጥር 0114-42-22-70/71/72 ፖ.ሳ.ቁ 3414 ፋክስ.ቁ 0114-40-04-71/0114-42-07-46 ኢትዮ ቻይና ወዳጅነት ጎዳና