Biography Catagories

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

Biruktawit Dawit

 

ብሩታዊት ዳዊት አብዲ ይበልጥ የምትታወቀው፤ በኢትዮጵያ ባንኮች በዋና ሥራ አስፈፃሚነቷ፤ እንዲሁም በአቢሲኒያናና በወጋገን ባንኮች መሥራች ፕሬዚዳንትነቷ ነው። ለዚያውም ደግሞ፤ ወቅቱ በኢትዮáያ ባንኮች ውስጥ ሴቶች ለምክትል ፕሬዚዳንትነት እንኳ በማይታሰቡበት ጊዜ ነበር። እንዲያም ሆኖ፣ ለአዳዲስ ተሞክሮዎችና ለፈታኝ ሥራዎች ያላት  ጥልቅ ፍላጎትና ጥማት ሁሌም የሙያ ሕይወቷ ልዩ ምልክት ሆኖ ዘልቋል። በኢኮኖሚክስ ሙያ የሰለጠነችውና በባንክ ዘርፍ የራሷን ትልቅ አስተዋፅኦ ያበረከተችው ብሩታዊት፤ ለትርፍ ባልተቋቋሙ ድርጅቶችም ውስጥ በኃላፊነት ሰርታለች። መቀመጫውን በአሜሪካ አድርጎ ኤችአይቪ ኤድስን ለመከላከል በተቋቋመ የረድኤት ድርጅት በፋይናንስ ዳሬክተርነት ሰርታለች፤ በአርብቶ አደር አካባቢዎች የእንስሳት ገበያ የማስፋፋት ዓላማ ይዞ በሚንቀሳቀሰው የአሜሪካ የልማት ረድኤት ድርጅት፣ የኢትዮጵያ ቅርንጫፍ ኃላፊና ዋና ተወካይ ሆና ማገልገሏም ይጠቀሳል። በተጨማሪም፣ በባህሬን ኮፐርስ ኤንድ ሊይብራንድ ለተሰኘው ድርጅት የኢኮኖሚክስ ባለሙያ ነበረች። በኢትዮጵያ የመጀመሪያዋ ሴት የባንክ ኃላፊ የሆነችው ብሩታዊት፤ በአቢሲኒያ ባንክ፣ በወጋገን ባንክ እና በዘመን ባንክ ውስጥ የአመራር መዘውሩን በመጨበጥ አገልግላለች፤ አዳዲስ ዘመናዊ አገልግሎቶችንና አሰራሮችን ለአገሪቱ ገበያ በማስተዋወቅ መልካም ስም አትርፋለች። ብሩታዊት፣ በሙያ ዘመኗ ለመጀመሪያ ጊዜ ዓምና እረፍት ከወሰደች ወዲህ፤ ለአገሯ የእድገት ግስጋሴ ተጨማሪ አስተዋፅኦ ለማበርከት፣ አዳዲስ አማራጮችን በማሰስና በመመርመር ላይ ትገኛለች።

 

ስድስት ልጆች ባፈራው ቤተሰብ ውስጥ የበኩር ልጅ የሆነችውና እ.ኤ.አ በ1939 ዓ.ም በአዲስ አበባ የተወለደችው ብሩታዊት፤ ብዙውን ጊዜ በዲፕሎማትነት ከአገር አገር ይዟዟሩ ከነበሩት አባቷ፣ አምባሳደር ዳዊት አብዱ አልተለየችም።  የሁለተኛ ደረጃ ትምህርቷን እስክታጠናቅቅ ድረስ ከአዲስ አበባ በተጨማሪ፣ በጋና፣ በናይጄሪያ፣ በሱዳን፣ በካናዳ እና በአሜሪካ ኖራለች። የደሴ አገረ ገዢ የነበሩት አባቷ አምባሳደር ዳዊት አብዱ ወደ ጋና፣ ከዚያም ወደ ናይጄሪያና ወደ ሱዳን፤ በመጨረሻም ወደ ካናዳ ሲመደቡ አብራ ሄዳለች። ወላጆቿ፣ ሁልጊዜ ልጆቻቸው ራሳቸውን እንዲችሉ ከማበረታታት የተቆጠቡበት ጊዜ የለም። እንደ ማንኛውም የዲፕሎማት ቤተሰብ፣  የቤት ውስጥ ሥራዎችን የሚያግዙ የቤት ሰራተኞች የነበሯቸው ቢሆንም፤ ልጆቹ ዘወትር የየራሳቸውን ክፍል እንዲያፀዱና በሳምንት አንድ ቀን ለቤተሰቡ ምግብ እንዲያሰናዱ ያደርጓቸው ነበር። ለብሩታዊት ወላጆች፤ ‘መማር እና ራስን መቻል’ ከሁሉም የላቀ የቤተሰብ እሴትና እምነት ነበር። ከአባቷ ያገኘችው ዋነኛ ምክር፣ “የማንም ሸክም አትሁኚ፤ በሁለት እግርሽ ቁሚ፤ ትምህርትሽን ተማሪ” የሚል ነው።

 

ለመጀመሪያ ዲግሪ ትምህርቷ በጆርጅ ዋሺንግተን ዩኒቨርሲቲ የተመዘገበችው ብሩታዊት፤ የጋዜጠኝነት ትምህርት የጀመረችው የመፃፍ ፍቅር ስለነበራት ነው። የዩኒቨርሲቲ ተማሪ ሳለች፣ ራሷን በገንዘብ ለመደገፍ ‘ዩኤስ ኒውስ ኤንድ ወርልድ ሪፖርት’ በተሰኘው የሚዲያ ተቋም ውስጥ በፀሐፊነት የመጀመሪያ ሥራዋን ያዘች። ሥራዋን ብትወደውም ቅሉ፤ አለቃዋ ግን የጋዜጠኝነት ሃሳቧን አልደገፉትም፤ ምክንያቱም እ.ኤ.አ. በ1960ዎቹ የውጭ አገር ስምና ቅላፄ ይዞ የሬድዮና የቴሌቪዥን ጋዜጠኛ መሆን የሚሞከር አልነበረም። የወደፊት ፍላጎቷን ገና በውል ያልለየችው ብሩታዊት፤ ወደ መምህርነት የትምህርት ዘርፍ ለመግባት ዳር ዳር ብትልም፤ በመጨረሻ በማኔጅመንትና ኢንተርናሽናል ትሬድ ላይ ፀናች። ነገር ግን በጆርጅ ዋሺንግተን ዩኒቨርሲቲ ሦስት ዓመት ከተማረች በኋላ ክፍያውን አልቻለችውም፤ ብዙ የወሰደቻቸው ኮርሶች እንደሚቃጠሉባትና የመመረቂያ ጊዜዋ እንደሚራዘምባት ብታውቅም፣ በክፍያ አነስ ወደሚለው ወደ ሃዋርድ ዩኒቨርሲቲ መዛወር ነበረባት።


በትርፍ ሰዓት እየሰራች፣ የዩኒቨርሲቲ ክፍያዋን ስትሸፍን የቆየችው ብሩታዊት፤ በዓለም ባንክ ውስጥ የአፍሪካ አገራት ክፍልን  ለሚመሩ ላይቤሪያዊ ዋና ዳሬክተር፣ በፀሐፊነት ተቀጠረች። ‘አይሆንም’ የሚል ምላሽ አሜን ብለው ከሚቀበሉት ተርታ ያልሆነችው ብሩታዊት፤ ሁሉንም የመመዘኛ ፈተናዎች በጣጥሳ ብታልፍም፤ የተለመደው የሥራ ቅጥር ዕድሜ (18 ዓመት) ስላልሞላት አትቀጠሪም ተብላ ነበር። እሷ ግን በጄ አላለችም፤ ሥራውን እንደምትችለው ፅኑ እምነት ስለነበራት፤ ወደ ዋና ዳሬክተሩ ቢሮ ተንደርድራ ገባችና እንዲቀጥራት አሳመነችው። ይኸኔ ነው፣ አፕላይድ ኢኮኖሚክስ ማጥናት እንደምትፈልግ በእርግጠኝነት የወሰነችው። መጀመሪያ በፀሐፊነት ብትቀጠርም፤ ብዙም ሳትቆይ እድገት አግኝታ ወደ ምክትል ሥራ አስኪያጅ(Adimministrtive Assistant)  ስትሸጋገር፤ ከዋና ዳሬክተሮች ጋር በቀጥታ የመሥራት፣ ለአባል አገራት ሪፖርት የማዘጋጀት እንዲሁም ስብሰባዎችንና የምክክር ፕሮግራሞችን የማሰናዳት ዕድል አግኝታለች። ከስድስት ዓመት ተኩል ቆይታ በኋላ የዓለም ባንክን በመልቀቅ፣ በአሜሪካ ባንከኞች ማህበር (American Banker’s Association) የትምህርት ክፍል ውስጥ የተቀጠረች ሲሆን፤ ወደ ጆርጅ ዋሺንግተን ዩኒቨርሲቲ ተመልሳ በአፕላይድ ኢኮኖሚክስና በኢንተርናሽናል ትሬድ የማስተርስ ዲግሪዋን ለመሥራት ከማህበሩ የገንዘብ ድጋፍ አግኝታለች። በዋሺንግተን ትዳር ይዛ ሦስት ልጆች ከወለደች በኋላ፣ በፍቺ ከባለቤቷ ስትለያይ የ23 ዓመት ወጣች ነበረች። እናም በዚህ ጊዜ ነው፤ ልጆቿን ብቻዋን እያሳደገች፣ ከሥራ ለቅቃ ለድህረ ምረቃ ትምህርት ዩኒቨርሲቲ የገባችው። ትምህርቷን ለማጠናቀቅ መቻልዋና በሁለት እግር በራሷ መቆሟ፣ ከሕይወት ዘመኗ ታላላቅ ስኬቶች አንዱ መሆኑን ብሩታዊት ታምናለች።

 

በአፕላይድ ኢኮኖሚክስና በ¹ለማቀፍ ንግድ የማስተርስ ዲግሪዋን እንደተቀበለች፤ ብሩታዊት ሥራዋን ቀይራለች። እዚያው የአሜሪካ ባንከኞች ማህበር ውስጥ፤ ወደ ኢኮኖሚክስና የጥናት ክፍል ተዛውራ በ”ኢኮኖሚስት” ደረጃ  መሥራት ጀመረች። ትንሽ ቆይታ ግን ወደ “ከፍተኛ ኢኮኖሚስት” ደረጃ አድጋለች። የአሜሪካ ባንከኞች ማሕበር በጣም ሳይስማማት አልቀረም። ከማሕበሩ ጋር ለ15 ¹መታት  ቆይታለች። በእርግጥም፤  የሚያማርር ነገር አልገጠማትም። በተቋሙ ውስጥ በሙያተኛ ደረጃ የሚሰሩ ሴቶች ሁለት ብቻ ሲሆኑ፤ ጥቁር ሴት ሙያተኛዋ ደግሞ ብሩታዊት ብቻ ናት። ቢሆንም፤ በሴትነትዋና በጥቁርነቷ  አድልዎ እንዳልደረሰባት ትገልፃለች። ብዙም ባይሆን፣ በተለይ በደቡባዊው የአሜሪካ ክፍል፣ ሙያተኛነቷን አምነው ለመቀበል የተቸገሩ ጥቂት ሰዎች አልጠፉም። አንድ ሁለቴ ደግሞ ከፍ ዝቅ አድርገው ሊያዩዋት የሚሞክሩ አጋጥመዋታል። ነገር ግን የማንምም አልባሌ ባህርይ የማስተናገድ ትእግስት የላትም፤ ለእያንዳንዱ እንደአመጣጡ ትመልሳለች። በቀናነት የሚመጣውን በትዕግስትና በብልሐት ጭምር ታስተናግዳለች። ካልሆነም እንደ አመጣጡ ነው። በዚህም ተባለ በዚያ፤ አደናቃፊ ተደርድሮ ቢጠብቅ እንኳ፤ የመጣችበትን ስራ ማከናወኗ አይቀርም። አላማና ግቧን፤ እንዲሁም በምን መንገድ ግቧን ለማሳካት እንደምትፈልግ በግልፅ እንዲያውቁ ታደርጋለች። ነገርን ሳትሸፋፍን፣ ዳር ዳሩን ሳትዞር፣ ፈራ ተባ ሳትል፤ እቅጩን በቀጥታ  የመናገር ድፍረቷና ሃይለኝነቷ፣ አንዳንድ ሰዎችን ቅር ሊያሰኝ ቢችልም፤  ለአለቆቿ ግን ጠቅሟቸዋል። የሆነ ቦታ አንዳች ችግር ሲፈጠርባቸው ወይም አንዳች ፈታኝ ሥራ ሲደቀንባቸው፤ ብሩታዊት ትጠራለች። ችግሩን እንድታስተካክልና ፈታኙን ሥራ እንድታስፈፅም የሚልኳት እሷን ነው። አንድ አለቃዋ፣ "አንቺኮ ከዲያብሎስ ጋር ሳይቀር መሥራት ትችያለሽ" ይላት እንደነበር ታስታውሳለች። እንዲህ በየቦታው ችግሮችን ለመፍታትና ፈታኝ ሥራዎችን ለማስፈፀም እየተላከች፤ ከ50ዎቹ የአሜሪካ ግዛቶች መካከል ወደ 42ቱ በተደጋጋሚ ተጉዛለች። በጉዞ በተጣበቡ አስር የጥድፊያ አመታት፣ በሆቴሎች ውስጥ ያሳለፈቻቸው ሌሊቶች እጅግ ብዙ ናቸው። 


ከዚህ ሁሉ በኋላ፣ ብሩታዊት ፈታኝ ሥራዎችን የማሰስ ወይም አሜሪካን የመዞር ጉጉት ሊያድርባት ይችላል ብሎ ማሰብ ይከብዳል። ግን፤ ለ15 ¹መታት ከcራችበት ከአሜሪካ ባንከኞች ማሕበር፣ የአንድ መት እረፍት የወሰደችው፤ ለሌላ ምክንያት ሳይሆን፤ አዳዲስ ፈታኝ ሥራዎችን ለማፈላለግና አሜሪካን በመኪና ለመዞር ነው። ግን፣ ወር እንኳ ሳይሞላት፣ ሁለት የእረፍት ሳምንታት እንኳ ሳታገባድድ፤ ከታዋቂዋ የአርኤንድቢ (R&B) ዘፋኝ ከዶኒ ዋርዊክ አስቸኳይ የስልክ ጥሪ ደረሳት። በኒውዮርክ ኤችአይቪ ኤድስን ለመከላከል ትልቅ የገቢ ማሰባሰቢያ ፕሮግራም እያዘጋጀች የነበረችው ዶኒ ዋርዊክ፤ ገንዘብ ነክ ጉዳዮቿን ለማስተዳደርና ለመቆጣጠር የሚረዳት ሰው ስለፈለገች ነው ለብሩታዊት የደወለችላት። ብሩታዊት ለሁለት ወራት ያህል ብቻ እንደምታግዛት ተስማማች። የሥራ ግንኙነታቸው ግን፤ እንደታሰበው በአጭሩ አልተቋጨም። የኤችአይቪ ኤድስ ረድኤት ላይ ብቻ ሳይሆን፤ ፋታ የማይሰጡ የዘፋኟ በርካታ የቢዝነስ እንቅስቃሴዎች ላይም ጭምር የፋይናንስ ሃላፊነትን የተቀበለችው ብሩታዊት፣ ለሦስት ¹መታት የሚዘልቅ የወከባ ስራ ውስጥ ገባች። ከኮንጎ ወጣቶችና ጎልማሶች መካከል 65 በመቶ ያህሉ በኤችአይቪ ኤድስ መጠቃታቸውን በመጥቀስ የአገሪቱ ፕሬዚዳንት የእርዳታ ጥሪ ባስተላለፉበት ወቅት፤ ታዋቂዋ ዘፋኝ እጇን እንድትዘረጋ ያሳመነቻት ብሩታዊት ናት። ኮንጎ ድረስ ሄዳ የተለያዩ መንደሮችንና ክሊኒኮችን የጎበኘችው ዶኒ ዋርዊክ፤ የእርዳታና የህክምና መገልገያዎችን፣ የግንዛቤ ማስጨበጫ ቁሳቁሶችንና ኮንዶም የያዙ በሺ የሚቆጠሩ ካርቶኖችን አከፋፍላለች። ከዘፋኟ ዶኒ ዋርዊክ ጋር ለሦስት ¹መታት ከcራች በኋላ፤ ብሩታዊት በወከባ ከተሞላው ኑሮ የወጣችው፤ ኩፐር ኤንድ ሊብራንድ ከተሰኘው ታዋቂ ኩባንያ የሥራ ግብዣ ስለቀረበላት ነው። በቢዝነስ የሂሳብ ሥራ ላይ ከተሰማሩት ትልልቅ የአሜሪካ ኩባንያዎች መካከል አንዱ በሆነው ኩፐር ኤንድ ሊብራንድ ተቀጥራ፤ በባህሬን በ”ኢኮኖሚስት” የሙያ ደረጃ ለሁለት ¹መት cራች።

 

አባቷን ለመጠየቅ ወደ ኢትዮጵያ ስትመጣ ነው፤ እዚሁ አገሯ ውስጥ የሚያስቀር ሥራ የገጠማት። የአባቷ ጓደኛ አቢሲኒያን ባንክ ለማቃቋም እንድታግዛቸው ሲጠይቋት፤ ተስማማች። በምሥረታው ወቅትም ለአምስት ወራት ያህል የባንኩ ፕሬዚዳንት ሆና cርታለች። ከዚያ በኋላ ደግሞ ወደ ወጋገን ባንክ ተዛወረች። ለሰባት ¹መታት ባንኩን በፕሬዚዳንትነት ስትመራ፤ በአሜሪካ ባንኮች ከነበራት ተመክሮ በመነሳት፣ በርካታ አዳዲስ አcራሮችና አገልግሎቶች በኢትዮጵያ እንዲታወቁና ተግባራዊ እንዲሆኑ አድርጋለች። የመኪናና የፍጆታ እቃዎች መግዣ ብድር፤ እንዲሁም የመማሪያ ብድር እንዲለመድ ፈር ከመቅደዷም በተጨማሪ፤ ሴቶች ጌጣጌጥ በዋስትና አስይዘው መበደር የሚችሉበትን አሰራር መፍጠሯ ያስደስታታል። የብድር መያዣ ዋስትና ዝቅ ማድረግ እንደሚቻል በተግባር ያሳየችው ብሩታዊት፤ ጠንካራ የቢዝነስ እቅድ የሚያቀርቡ ሥራ ፈጣሪዎች ያለመያዣ ብድር የሚያገኙበት አሰራር ፈጥራለች። የወጋገን ባንክን በብቁ ባለሙያዎች ለማጠናከር በማሰብ፣ cራተኞችን ማሰልጠኗ ለባንኩ ብቻ ሳይሆን በአጠቃላይ ለአገሪቱ የባንክ አገልግሎት ትልቅ ጥቅም አስገኝቷል። በዘመናዊ የባንክ አcራሮች ዙሪያ ያሰለጠነቻቸው 109 ወጣት ባለሙያዎች፤ ዛሬ በመላ አገሪቱ በሚገኙ የባንክ ተቋማት ከፍተኛ የሃላፊነት ቦታ ይዘዋል።

 

ብሩታዊት ሥራ የምትለውጥበትን ጊዜና አቅጣጫ አስቀድሞ ለመተንበይ አስቸጋሪ እንደሆነ በእስካሁኖቹ ሥራዎቿ በግልፅ ታይቷል። አሁንም ወዳልተጠበቀ አቅጣጫ ዞረች። የልማት ስራዎች ላይ የሚያተኩርና ለትርፍ ያልተቋቋመ ACDI/VOCA የተሰኘ የአሜሪካ ድርጅት ውስጥ ገባች። የድርጅቱ የኢትዮጵያ ተጠሪና ወኪል ሆነች። በዚህ ሃላፊነቷም፤ ለአፋር፣ ለሶማሌና ለቦረና አርብቶ አደሮች የሚያገለግሉ 25 የእንሰሳት ገበያ ማዕከሎችን አስገንብታለች - በአሜሪካ የአሰራር ደረጃ። እግረመንገዷንም፤ ሳታውቀው የቆየ አዲስ የኢትዮጵያ ገፅታ በማየት ተደንቃለች።
እንደገና ወደ ባንክ ሥራ የተመለሰችው፤ አዲስ የተቋቋመውን ዘመን ባንክ በፕሬዚዳንትነት ለመምራት ነው። ዘመን ባንክ በአዳዲስ የባንክ አcራሮቹ በግንባር ቀደምትነት የሚታወቅ ሲሆን፤ ብሩታዊት ከባንኩ ምስረታ አንስታ ለሁለት ¹መታት በፊታውራሪነት መርታዋለች። ከዚህ በኋላ ነው፤ ለብዙ ¹መታት ስትመኘው የነበረ የአንድ ¹መት እረፍት ለማግኘት የቻለችው። ልጆቿን እንደየአላማቸው እያገዘች የእረፍት ጊዜዋን ያሳለፈችው ብሩታዊት፤ አሁንም አንደገና አዳዲስ የሥራ አማራጮችን በማሰስ ላይ ናት።

 

የግል ምኞቷ የልጆቿን ደስታ ማየት ነው። ለኢትዮጵያ ያላት ህልም ደግሞ፤ ሴቶች እውነኛ እኩልነት ሲቀዳጁ ለማየት መብቃት ነው።

ለወጣት ሴቶች እንዲህ ስትል ምኞቷን ትለግሳለች፡ ማንነትሽንና ፍላጎትሽን እወቂ። የምትፈልጊውን ለማሳካት፣ ምንም ቢሆን ወደ ኋላ አትበዪ። ለራስሽ አለኝታና ጠበቃ ሁኚ። ፍላጎትሽንና እንዴት ፍላጎትሽን ለማሳካት እንዳሰብሽ በግልጽ አሳውቂ። ሀያ ሚሊዮን እንቅፋቶች ቢደረደሩብሽ፤ አንድ በአንድ እየነቀልሽ ጣያቸው።