Biography Catagories

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

Derartu Tulu

 

Derartuእኔ ወልጄ ነው ለተወሰኑ ዓመታት ያቋረጥኩት፡፡ በነገራችን ላይ ኒውዮርክ ማራቶን 3ኛ ወጥቼ ነው በ2005 ሩጫ ያቆምኩት፡፡ ከአራት ዓመት በኋላ ሮጬ ነው ይህን ውጤት ያመጣሁት፡፡ከወለድኩ በኋላ በማራቶን ይህ ውድድር አራተኛዬና የተሻለ ውጤቴ ነው፡፡ወደ በፊቱ ውጤት መምጣት አስቸግሮኝ ነበር፡፡ “ትንሽ ብታገስ ይመጣልኛል “ ብዬ ነው የሞከርኩት፡፡ በእኛ 2002 ውጤት ካልመጣልኝ ወደማቆሙ እሄድ ነበር፡፡ ማሸነፍን አላሰብኩትም፡፡ ግን ኒውዮርክ ከመሮጤ ስድስት ሳምንት በፊት ፍላደልፊያ ባፈው ጥር ግማሽ ማራቶን ስሮጥ 2፡14፡57 ነው ያመጣሁት፤ “ወደ ውጤት ቀርቢያለሁ “ ብዬ አሰብኩ፡፡ ይህ የልብ ልብ ሰጥቶኝ ባላሸንፍም ጥሩ እፎካከራለሁ ብዬ ነው የገባሁት፡፡በመጨረሻ በእግዚአብሔር ፍቃድ አሸንፌያለሁ፡፡63 ኪሎ ነበርኩ፡፡18 ኪሎ ነው የጨመርኩት፡፡በማራቶንና ግማሽ ማራቶን የቻልኩትን ያህል ለመሮጥም ውጤት ለማምጣትም አስባለሁ፡፡ ግን ደግሞ ያው የእድሜና የተፈጥሮ ህግ በመሆኑ ከተወሰነ ጊዜ በኋላ ሩጫን አቆማለሁ፡፡

በኢንተርናሽናል ውድድሮች ላይ መሳተፍ  21ኛ ዓመቴን ይዣለሁ፡፡ በ1981 ነው የጀመርኩት፡፡ በወቅቱ በሴቶች አምስት ኪሎ ሜትር ሮጩ 23ኛ ነው የወጣሁት፡፡ ትልቁ የራቀ ውጤቱም እሱ ነው፡፡ ከዚያ እያሻሻልኩ ነው የመጣሁት፡፡እንግዲህ እኔና ፓውላ ለ15 ዓመት በላይ አብረን ሮጠናል፡፡ ሀገር አቋራጭና ትራክ ማለት ነው፡፡ ከቅርብ ጊዜ (ከ 2002) ጀምሮ ማራቶንና ግማሽ ማራቶን እንሮጣለን፡፡ ፓውላ ከእኛ ልጆች ጋር ከእኔም፤ ከብርሃኔም፤ ከጌጤም ጋር የመሮጥ እድል ገጥሟታል፡፡ ለእኛ ቅርባችን ናት፡፡ በቅርበት የምናውቃት ጓደኛችን ናት፡፡ የቅርባችን ስለሆነች በሩጫው ላይ ስለደከማት ላበረታታት ሞከርኩ፡፡ ግን አብረን መሄድ አልቻልንምና እኛ ቀደምን፡፡እረፍታችን እሁድ ብቻ ነው፡፡ በተረፈ ደብሮኝ፤ ወይም የሆነ ከባድ ጉዳይ ገጥሞኝ ካልሆነ በሳምንት ስድስት ቀን ጠዋትና ማታ ሮጣለሁ፡፡

የኒውዮርክ ማራቶን 130,000.00 (አንድ መቶ ሰላሳ ሺ) ዶላር ነው ያገኘሁት፡፡ ያው አሜሪካ በቀኝ እጇ የሰጠችውን በግራዋ ትወስዳለች፡፡ 30% (ሰላሳ በመቶ) ታክስ ትወስዳለች፡፡ ማናጀሬ 15% ይወስዳል፡፡የተረፈው የራሴ ነው፡፡እኛ ሀገር በሩጫ ከምናገኘው ገንዘብ ላይ የሚወስድብን ምንም የለም፡፡ ድሮ የተወሰነ ፐርሰንት ለፌዴሬሽንና ለአሰልጣኝ ተብሎ ይቆረጥ ነበረ፡፡ ልክ እንዳልሆነ ታምኖበት ነው መሰለኝ ቀርቷል፡፡በተረፈ መንግስታችን ምንም አይቆርጥብንም፡፡ተተኪዎች ለማፍራት ያደረኩት ጥረት የለም፡፡ በተለያዩ አጋጣሚዎች ለማገኛቸው አትሌቶች ልምዴን ከማካፈል ውጭ እውነቱን ከመናገር ምንም አላደረኩም፡፡ ትኩረቴን ራሴ ላይ ነው ያደረኩት መሰለኝ፡፡

ከእኔ በፊት ኢትዮጵያን ወክላ በዓለም የታወቀችና ለእኔ መነሻ የምትሆነኝ አትሌት አልነበረችም፡፡ ብትኖርም እኔ በቆጂ ነው ያለሁት፡፡ ምንም የምሰማው ነገር የለም፡፡ ፋጡማ ከእኛ አካባቢ ቀደም ብላ ብትወጣም እንደ እሷ እሆናለሁ ብዬም ባላስብ አርሲን ወክዬ በ1980 አዲስ አበባ መጣሁ ኢትዮጵያ የሚለውን ቱታ ለብሰው ሳይ በጣም እጓጓ ነበር፡፡ ይህን ልብስ መልበስ አለብኝ ብዬ አስቤያሁ እንጂ እሷን አይቼ ተከተልኳት የምላት የለችም፡፡ሱሉልታ ደርሶ መልስ (ጠዋትና ማታ) ሶስት ሰዓት ይፈጅብኛል፡፡ አድካሚ ልምምድ አደርጋለሁ፡፡ ቤት መጥቼ ማረፍ አለብኝ፡፡ ካላረፍኩ ምግብም አይበላልኝም፡፡ ቤቴ ውስጥ ስድስት ልጆች አሉኝ፡፡ የእነሱን የትምህርት ሁኔታ እከታተላለሁ፡፡ ማህበራዊ ህይወት አሉ፡፡ መቼ ነግቶ እንደሚመሽም አላውቅም፡፡

ብዙ ሰዎች “እናትሽን ትመስያለሽ “ ሲሉኝ እሰማለሁ፡፡ ጎበዝና ጠንካራ እናት ነው ያለችኝ፡፡ አረቄና ጠላ ጠምቃ እየሸጠች ነው ያሳደገችኝ፡፡ ዛሬም ትሰራለች፡፡ አንዳንዶች “ልጅሽ ብር እያላት እንዴት ትሰሪያለሽ? “ ይሏታል፡፡እሷ ግን “መስራት እየቻልኩ ለምን የልጅ እጅ አያለሁ? “ ነው የምትላቸው፡ እኔም በመስራቷ ቅሬታ የለኝም፡፡ ስራ ክቡር ነው፡፡

የልጅነት ጊዜዬ ከባድ ነበር፡፡ እኔ የመጣሁት ከደሃ ገበሬ ቤተሰብ ነው፡፡ በተለይ ከእናታችን ጋር ሆነን የእለት ሩሯችንን ለማሟላት እነሰራ ነበር፡፡ አባታችን ጥሩ ሰው ቢሆንም በስራ የእናታችንን ያህል ጠንካራ አልነበረም፡፡ እናቴ ጠንካራ ናት፡፡ ሰባት ልጆች ነበርን፡፡ እሷ የምትሰራውን ሁሉ እነሰራ ነበር፡፡ እረፍት የሚባል ነገር አልነበረኝም፡፡ ትምሀርት ቤት ደርሼ ከመጣሁ ከጥናት በላይ ወላጆቼን በማገዝ ነው ያሳለፍኩት፡፡ ከብት ከማገድ ጀምሮ ሁሉንም ሰርቼ ነው እዚህ የደረስኩት፡፡ ካላጋነንኩት በስተቀር ስፌት መስፋት ብቻ እንጂ ሁሉም ስራ ላይ ጎበዝ ነበርኩ፡፡ እርሻ አርሳለሁ፤ አጭዳለሁ፤ ከብት እጠብቃለሁ …… አሁንም እናቴ ጋር ስሄድ ሁሉንም ስራ እሰራለሁ፡፡ያገኘሁትን ነው የምለብሰው፡፡ ለልብስ አልጨነቅም፡፡እንደውም አንዳንድ ወዳጆቼ “ለምንድነው እንዲህ የምትለብሽው? “ ይሉኛል፡፡“የኢትዮጵያ ህዝብ የሚያውቀኝ በሩጫ እንጂ በፋሽን ሾው አይደለም “ እላቸዋለሁ፡፡አሁን የምንገኘው እጅግ ዘመናዊ በሆነው መኖሪያ ቤትሽ ውስጥ ነው፡፡ እንደ ድካምሽ ሊያንስሽ ይችላል፡፡ ግን እንደው ዛሬ ላይ ሆነሽ የአርሲዋን ትንሷን ደራርቱን ህይወቷን ስታስቢ ምን ይሰማሻል?

አንተ ልጅ ግን እሩጫ ሞክረህ እምቢ ሲልህ ሳትተው አትቀርም …../ሳቅ/ ….. ይሄ ቤት ያንሰኛል አልልም፡፡ ትልቅ ነው ብዬ ነው የምገምተው፡፡ እኛ ሀገር ብዙ ለፍተው ጥሩ የስፖርት ጫማ እንኳን የሌላቸው ምንም ሳያገኙና ከገንዘቡም ከሰውነታቸውም ሳይሆኑ የቀሩ አሉ፡፡ አንድ ቀን እንኳን ውጪ ሀገርን ሳያዩ የቀሩ አሉ፡፡ እንደዚህም እንዳለ አስበዋለሁ፡፡ አመጣጤን ሳስበው ይህ ቤትና ኑሮ ለእኔ በጣም ትልቅ ነው፡፡ አሁን ሳር ቤት ውስጥ ብኖርም የምችል ነኝ፡፡እናቴን ነጋጠባ ስትሰራ ነው የማያት፡፡ እኔም ራሴን የማውቀው ከስራ ነው፡፡ የወላጅ አስተዋጽኦ በልጅ ላይ ይታያል፡፡ራሴን እንደ እድለኛ ሴት አድርጌ ነው የምቆጥረው እኔም፤ ቤተሰቤም እድለኞች ነን ብዬ ነው የማስበው፡፡

መጀመሪያ በት/ቤት ውስጥ ጥሩ ማርክ ለማግኘት ሮጬ፤ በዚያው ለትምህርት ቤት፤ ለሀገር እያልኩ አለምን ዞርኩ፡፡ ይህ ለእኔ የሎተሪዎች ሁሉ ሎተሪ ነው፡፡እናታችን ራሷ ባለመማሯም ይቆጫታል፡፡ እኛም እሷ ማድረግ ያልቻለችውን እንድንችልላት ነው ፍላጎቷ፡፡ግን እሷ “ተማሪ! “ ብላኝም በእግዚአብሔር ፈቃድ ሮጬ ለዚህ በቅቻለሁ፡፡ዛሬ ብዙ ቦታ ሩጫ አለ፡፡ እኔ ወደ ፌዴሬሽን የመሄድ ብዙ እድል የለኝም፡፡ ዘንድሮ ሁሉም ሊባል ይችላል መሰለኝ ብሄራዊ ቡድን እንደ ድሮው የለም፡፡ እስከ ሲድኒ ኦሎምፒክ ድረስ ከሚመጡት አዳዲስ አትሌቶች ጋር እንገናኝ ነበር፡፡ ከክለብ እየመጡ ብሄራዊ ቡድን ይሰሩ ነበር፡፡ አሁን ሁሉም በየክለቡ ቀር ቷል፡፡ እንደ ድሮው በብሄራዊ ቡድን መገናኘት ቀርቷል፡፡

አዳዲስ አሰልጣኞች ስለመጡም ሁሉም በግላቸው ነው ተበታትነው የሚሰሩት፡፡ እኔም በግል ነው የምሰራው፡፡ እስከ ሲዲኒ ድረስ ጥሩ ግንኙነትና መመካከር ነበር፡፡ አሁን የለም፡፡እኔ የድሮውን ነው የምመርጠው፡፡ እኛ ስንሰራም፤ ስንበላም፤ ስንሄድም አብረን ነው በፈረንጆች 2000 እኔና ጌጤ አገር አቋራጭ አንደኛ እና ሁለተኛ ስንወጣ አንዳችን ለአንዳችን ውሃ አንስተን እየተቀባበልን ነው የሮጥነው፡፡ ልምምድ ስናደርግም ደስ እያለን ነው፡፡ ያኔ ፈራጅ ነበርን፡፡ አሁን ደግሞ ተፈረደብን፡፡ኬኒያዎች ያኔ ሲገኙ “ሃይ! ….. ሃይ!....“ ነው የሚባባሉት፡፡ እኛ ደግሞ ጠዋት ስንገናኝም ሆነ ማታ በድጋሚ ስንገናኝ ተቃቅፈንና ተሳስመን “እንዴት ነሽ?“ ተባብለን ነው፡፡ እነሱ ከሩቁ ነው በእጅ ጭምር ሰላም የሚባባሉት፡፡ “በስመአብ እነዚህ ምንድነው ሰላም እንኳ የማይባባሉ? “ የአንድ ባንዲራ ልጆች አይመስሉም እያልን በእነሱ ስንፈርድ ነበረ፡፡ የእኛም እንደዚያ እየሆነ ነው፡ ታዲያ ተፈረደብን አይባልም? ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተባለ ነው፡፡ ድሮ እኛ አብረን ወጥተን ስንመለስም አብረን ነው፡፡ ሌላ ቀርቶ ውጭ ሌላ ውድድር  ከቀናት በኋላ እያለንም ከቡድኑ ላለመለየት እዚህ መጥተን ነው ተመልሰን የምንሄደው፡፡አሁን አትሌቱ ውድድሩን ሲጨርስ ተነስቶ ነው የሚመጣው እኛ ይህን እናደርግ የነበረው ሞኝ ስለሆንን አይመስለኝም፡፡ሞኝ ሆነን ከሆነም ፍቅራችን ነው ሞኝ ያደረገን፡፡ የድሮው ቡድን የሚመጣ አይመስለኝም፡፡