Biography Catagories

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

Dr. Eleni Zaude Gabre Madhin

 

ዶክተር እሌኒ ዘውዴ ገብረመድህን

የግብርና ኢኮኖሚስት፣ የመንግስትና የግል ኩባንያ ሥራ አስፈፃሚ የንግድ ሥራ ፈጣሪ

`

Dr Eleni Gebremedihin Biograph“ህልሞቻችን ግን ቤታችን ውስጥ የምናስባቸው ትርኪሚርኪ ሀሳቦች መሆን የሌለባቸው፡፡ እንደ ሌላው ሰው ትርጉምና ፋይዳ ያላቸው ሕልሞች ሊሆና  ይገባል፡፡"

አንድ ሴትነታችን ሕልም መተለምን ለራሳችን መፍቀድ አለብን፡፡ ህልሞቻችን ግን ቤታችን ውስጥ የምናስባቸው ተናንሽ ሀሳቦች ሳይሆን እንደ ሌላው ሰው ትርጉምና ፋይዳ ያላቸው ትላልቅ ህልሞች ሊሆኑ ይገባል፡፡ እናንተ ራሳችሁ በልማችሁ ካላመናችሁ፣ ማንስ ሊያምንላችሁ ይችላል፡፡ ገና ድሮ የሁለተኛ ትምህርት ቤት የምረቃ መጽሄት ላይ ስለ ወደፊት ሕልሜ ስጽፍ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የመጀመሪያ ሴት ዋና ፀሀፊ መሆን እንደምፈልግ ከትቤ ነበር፡፡ ይሄን ሕልሜን ገና አላሳካሁትም ወደ ፊት ግን ማን ያውቃል፡፡

ትላልቅ ነገሮችን ማለም የቻልኩት ወላጆቼ፣ በእኔና በእህቶቼ ላይ ከፍተኛ እምነት ስለነበራቸው ነው፡፡ እናቴ፣ ብልህ ሴት ብትሆንም፣ በነበረባት የቤተሰብ ኃላፊነት፣ የኮሌጅ ትምርህቷን አላጠናቀቀችም በአስተዳደር ሥራዋ ሁሌም ቁርጠኛና ስኬታማ የነበረችው እና የበለጠ ብዙ መስራት ትችል ነበር፡፡ እኛን ከወለደች በኋላ ሳታሳካ የቀረቻቸውን ሥራዎች፣ እኛ እንድናሳካ ትፈልግ ነበረ ብዬ አስባለሁ፡፡ መቼም በሴት ልጆቿ ላይ የነበራት እምነት ወደ የለሽ ነው፡፡ በትምህርት የመጠቀና በሙያው የተሳካለት አባቴ ደግሞ ከተባበሩት መንግስታት ከፍተኛ አመራሮች አንዱ ነበር፡፡ ብሩህ አዕምሮ እንዳለን፣ ትላልቅ ስኬቶችን ከኛ እንደሚጠብቅና ለእኛነታችን ከራሳችን ሌላ ማንም ተጠያ እንደሌለ ይነግረን ነበር፡፡ ወላጆቻችን በእኛ ላይ የነበራቸው እምነት ነው፡፡ ስናጠናና ስናነብ ለነገ አንልም ነበር፡፡ እኔና እህቴ በሳንት 15 ገደማ መፃህፍት ጥርግ አድርገን እናነባለን፡፡ ማታ ማታ እናታችን እንድንተኛ ከነገረችን በኋላ፣ አልጋ ውስጥ ባትሪ አብርተን እናነብ እንደነበር አስታውሳለሁ፡፡

የረዥም ጊዜ ዕቅዶችን ነድፎ መያዝ ውጤት እንደሚያመጣ ከልብ አምናለሁ፡፡ በሩዋንዳ የ15 ዓመት ታዳጊ ሳለሁ ነበር፣ የግብርና ኢኮኖሚስት እሆናለሁ ብዬ የወሰንኩት፡፡ ወዲያው በግብርና ኢኮኖሚክስ የዶክትሬት ዲግሪዬን አይዛለሁ፡፡ መጽሐፍ እፅፋለሁ፣ ድህነትን ከአፍሪካ አጠፋለሁ በማለት የአስር ዓመት የሕይወት ዕቅዶቼን በጽሁፍ አሰፈርኩ፡፡ ከልማት ሥራ ጋር የተዋወቅሁት አባቴ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ውስጥ በነበረው የኃላፊነት ሚናና  በእናቴ የበጎ ፈቃደኝነት ሥራ አማካኝነት ነበር፡፡ ተጽዕኖ ካሳደሩብኝ መፃሕፍት መካከል ከአባቴ ወስጄ ያነበብኩት በዋተር ሮድኒ የተፃፈው “አውሮፓ እንዴት አፍሪካን እንዳታደርግ አደረገች፡፡ (How Eorope underdeveloped Africa) የተሰኘው መጽሐፍ ነበር፡፡ መጽሐፉ የአፍሪካ ምሁራን ለምን ለአፍሪካ ችግሮች አፍሪካዊ መፍትሄዎችን መፍጠር እንደሳናቸው ይጠይሰቃል፡፡ ይሄን መጽሐፍ ካነበብኩ በኋላ፣ የአፍሪካን ችግሮች ከሚፈቱ አፍሪካውያን አንዷ እሆናለሁ ብዬ ቆረጥኩ፡፡ እቅድም ነደፍኩ፡፡ ለቀጣዮቹ 10 ዓመታትም፣ ከእቅዴም ውልፊት ሳልል ይዤው ዘለቅሁ፡፡

ይሄ ጉዞዬ አትብቴ ከተቀበረባት አገር ጋር ያለኝን ትስስር መፈተሸንም የሚያካትት ነበር፡፡ ለመጀመሪያ ጊዜ ከአገሬ የወጣሁት የአራት ዓመት ሕፃን ሳለሁ ቢሆንም በዚያው አልቀረሁም፡፡ በዘጠኝ ዓመቴ ለሁለተኛ ጊዜ ስወጣ ግን በዚያው ቀረሁ፡፡ ዳግም ወደ ኢትዮጵያ የመጣሁት ባለሙያ ከሆንኩ ከ30 ዓመት በኋላ ነበር፡፡

በስድስት የተለያዩ ሀገራት ማደጌ የብዙ ቋንቋዎች ተናጋሪና በየሄድኩበት ባይተዋርነት የማይሰማኝ ጠንካራ ሴት እንድሆን አድርጎኛል፡፡ በሌላ በኩል ግን አገር አልባ የመሆን ስሜትም ፈጥሮብኝ ነበር፡፡ ይሄ ደግሞ  በኢትዮጵያዊ ማንነቴን የበለጠ አጥብቄ እንድይዝ አደረገኝ፡፡ አግሬ አንድ ቀንም እንኳ የኢትዮጵያ ት/ቤትን ባይረግጥም የሁለተኛ ደረጃ ትምህርቴን ባጠናቀቅሁበት የኬንያ አዳሪ ት/ቤት፣ አማርኛ ማንበብና መፃፍ እራሴን አስተምሬአለሁ፡፡ የመመረቂያ ጥናቴን የሰራሁትም በኢትዮጵያ ታሪክ ላይ ነበር፡፡ በእንደዚህ አይነት ሂደት ነው፣ ኢትዮጵያዊ ማንነቴንና ኩሩነቴን በጽናት የገነባሁት፡፡ ከዚያም ለመጀመሪያ ዲግሪዬን ለመማር ኒውዮርክ በሚገኘው ኮርኔል ዩኒቨርሲቲ ገባሁ፡፡ እዚያው ሳለሁ የ1977 ዓ.ም የኢትዮጵያ ረሃብ ትኩስ የዜና ርዕሰ ጉዳይ ሆነ፡፡ ታላቋ አገሬ እንዲያ ያለ አስከፊ ችግር መጋፈጧ፣ ቁፃና ኀዘን ፈጠረብኝ፡፡ በዚያው ጊዜ አንድ ምሽት ላይ ደግሞ በዩኒቨርስቲያችን ካፍቴሪያ ውስጥ የምግብ መወራወር ድብድብ ተነሳ፡፡ ተማሪዎቹ ያንን ሁሉ ምግብ እንደጨዋታ እተወራወሩ ሲያባክኑ ደንታ አልሰጣቸውም፡፡ እኔ ግን ቱግ አልኩኝ፣ ደሜ ፈላ፡፡ የዚያኑ ዕለት ሌሊት፣ ከኢትዮጵያ ጓደኛዬ ጋር የተማሪዎች ጋዜጣ ላየ የሚወጣ ጽሁፍ ስናዘጋጅ አደርን፡፡ ጽሁፉ በኢትዮጵያ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሕዝች ላይ ስለደረሰው ረሃብና ስለዩኒቨርሲቲው መረን የለሽ ተማሪዎች የሚያትት ሲሆን መሪዎችን በሚያፈልቀው ኮርኔል ዩኒቨርሲቲ፣ የሚማሩና መሪዎች እንደሚሆኑ የሚጠበቁ ተማሪዎች ለሰው ልጅ ረሃብ ደንታ ቢስ መሆናቸውን በማሳየት በትችት የሚሸነቁጥ ጽሁፍ ነበር፡፡ ያ አጋጣሚ፣ በኢትዮጵያ ረሃብና የምግብ እጥረትን ማስወገድ ላይ አተኩሬ፣ እንድሰራ አደረገኝ፡፡ ከዚያ ጊዜ በኋላ ያጠናሁት ነገር ሁሉ፣ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ከዚህ ጉዳይ ጋር የተገናኘ ነበር፡፡

በሚቺጋን ዩኒቨርሲቲ ለድህረ ምረቃ የማስተርስ ዲግሪ የግብርና ኢኮኖሚክስ እያጠናሁ ሳለ፣ አንድ አስደንጋጭ ጽሁፍ አነበብኩ፡፡ በኢትዮጵያ ሰሜናዊ ክፍል፣ ወሎና በትግራይ ሕዝብ ተርቦ በነበረበት ወቅት፣ በምዕራቡ የኢትዮጵያ ክፍፍል ትርፍ የእህል ምርት እንደነበር ጽሁፍ ይገልፃል፡፡ ይሄኔ ነው ከተለመደው የእህል ስርጭት ችግሮች ላይ አተኩሬ ለማጥናት የወሰንኩት፡፡ አመለ ሸጋው የመመረቂያ ጽሁፍ አማካሪዬ፣ የጥናት ሀሳን መደገፍ ብቻ ሳይሆን ምርምር ፕሬጀክቴን በማሊ የእህል ገበያዎች ላይ እንዳደርግ እረዳኝ፡፡ እንደኔ ፍላጎት ቢሆንማ፣ ጥናቴን በኢትዮጵያ ላይ ባደረግሁት ነበር፡፡ ክፋቱ ግን ኮሚኒስታዊወ የደርግ አገዛዝ በስልጣን ላይ ስለነበር፣ በኢትዮጵያ ላይ ለሚሰሩ ምርምሮች የገንዘብ ድጋፍ ማግኘት የሚታሰብ አልነበረም፡፡

የማሊ ነገር እናቴን ቢሰቀጥጣትም (በልቧ ግን መኩራቷም አልቀረ) ከማሊያዊው ወንድ ባልደረባዬ ጋር በመላ አገሪቱ ተጓዝኩ፡፡ የ24 ዓመቷ ኮስማና ኢትዮጵያዊት ወጣት፣ በማሊ ገጠራማ ሥፍራዎች እየተጓዝኩ የእህል ነጋዴዎችና ገበሬዎችን አነጋገርኩ፡፡ የበረሃው ፣ሁኔታ ሙቀቱና  አስቸጋሪ መንገዶቹ ለመስክ ሥራ ፈጽሞ የሚመች ስላልነበሩ ማንም ሰው ለምን የማሊን  ለገጠር ለጥናቴ እንደመረጥኩ ሊገባው አልቻለም፡፡ እኔ ግን የግብይት ወጪዎች ትንተና የተሰኘውን አዲስ የጥናት ዘዴ ለመሞከር ጓጉቼ ነበር፡፡ ይሄ የአጠናን ዘዴ፣ አንድ ጆንያ እህል ከገበሬው አንስቶ የመጨረሻ ቦታው እስኪደርስ ያለውን የጉዞ ሂደት በመከታተል፣ በእያንዳንዱ ምዕራፍ ያሉትን ወጪዎችና እንቅፋቶች ያሰላል፣ በግብይት ሂደት ወስጥ ያሉ ማነቆዎችንም ለይቶ ያወጣል፡፡ ያገኘሁት ውጤት አስገራሚ ነበር፡፡ የጥራት ማረጋገጫ ወይም ትክክለኛ መለኪያ አሊያም አስተማማኝ የዋጋ ትመና መረጃ የሚገኝበት ሥርዓት ስላልተዘረጋ ዋናው በገበያው ተዋናዮች መካከል ያለው አለመተማመን ነበር፡፡ በኋላ ግን በስታንድፎርድ ዩኒቨርሲቲ ለዶክትሬት ዲግሪዬ ሳጠና በኢትዮጵያ የመንግስት ለውጥ መደረጉን ተከትሎ ከሮክፌለር ፋውንዴሽን ድጋፍ በማግኘቴ፣ ወደ አገሬ መጥቼ የእህል ገበያዎችን ለማጥናት ቻልኩ፡፡ በማሊ ከተቀረጽኩትና ከተጠቀምኩበት በእጅጉ የረቀቀ የጥናት ዘዴ ስለታጠቅሁ አመጣጤ የዋዛ፣ አልነበረም፡፡ ከመሃል አገር ጀምሮ በየአቅጣጫው (1987-88) ብዙ ሺህ ኪሎሜትሮችን አካልያለሁ፡፡ አገሬን በቅጡ አወቋኋት፡፡ በመቶዎች የሚቆጠሩ ነጋዴዎችንና ገበሬዎችን ባነጋገርኩበት በዚሁ ጥናቴ ማጠቃለያ ላይ ያገኘሁት ውጤት ከማሊው ጋር ተመሳሳይ ነበር፡፡ እዚህም በገበያው ተዋናዮች  መካከል መተማመን አልነበረም፡፡ ግብይቱ በከፍተኛ ወጪ የተንዛዛና በኪሳራ አደጋ የተከበበት ነው፡፡ እነዚህ ሁሉ ተዳምረው ገበያውን ደካማ አድርገውታ፤ ለአሜሪካ የጥናት አማካሪዎቼ ጋር ካደረግሁት የተሟሟቀና ተከታታይ ውይይት በኋላ፣ የምርት ገበያ ማቋቋም ለእነዚህ  የገበያው ችግሮች መፍትሄ ይሆናል የሚል ሀሳብ ቀረጽኩ፡፡

በስታንድፎርድ ትምህርቴ በክፍሌ ውስጥ ብቸኛዋ ሴት ነበርኩ፡፡ የመስክ ጥናት በመስራትም ብቸኛዋ ተማሪ ነኝ፡፡ በዚህ ወቅት የመጀመሪያ ልጃችንን ያሬድን እርጉዝ በመሆኔ፣ ባለቤቴን ትልቅ ጭንቀት ላይ ጥሎት ነበር፡፡ ያሬድ የተወለደው በዶክትሬት ፕሮግራሙ መሃል ላይ ነበር፡፡ እንዲያም ሆኖ የመመረቂያ ወረቀቴን በሰዓቱ ነበር ያጠናቀቅሁት፡፡ ያስደነቀኝና ያስፈነደቀኝ ደግሞ በ1981 ዓ.ም የአሜሪካ የእርሻ ኢኮኖሚክስ ማህበርን የላቀ የመመረቂያ ጽሁፍ ሽልማት ዲሲ በዓለም አቀፍ ደረጃ ስመጥር በሆነ የምርምር እና ፖሊሲ ማዕከል ውስጥ ተመራማሪ ሆኛለሁ፡፡

በዚሁ ዓመት መጨረሻ ላይ ዓለም ባንክ በኢትዮጵያ ባዘጋጀው የምግብ ዋስትና ኮንፍረስን ላይ ጥናት እንዳቀርብ ተጋበዝኩ፡፡ የኢትዮጵያ ጠ/ሚኒስቴር መለስ ዜናዊ በተገኙበት በዚሁ ኮንፍረስን ላይ አጋጣሚውን ተጠቅሜ ኢትዮጵያ የምርት ገበያ ድርጅት ያስፈልጋታል የሚለውን ሀሳብ አቀረብኩኝ፡፡ ያ ጉባኤ በአፍሪካ በዓይነቱ የመጀመሪያ የሆነውን የኢትዮጵየ ምርት ገበያን የመመስረት ጉዞዬ መነሻ ሆነ፡፡ ቤተሰቦቼ ደርግን ሸሽተው ከአገር ከወጡ ከሰላሳ ዓመት ገደማ በኋላ በ1996 ዓ.ም በዓለም ባንክ ውስጥ የነበረኝን ሥራ በመተው በአገሬ ለመኖር ወደ ኢትዮጵያ ተመለስኩ፡፡ በ2000 ዓ.ም ከፍተኛ ብቃት ባለው የባለሙያዎች ቡድን ታግዘን፣ የእኔ ህልም ብቻ ሳይሆን ብዙዎች ተስፋ የጣሉበትን ይሄን አዲስ ተቋም ለመጀመር ተዘጋጀን፡፡ ቀጣዮቹ አራት ዓመታት በሙያ ዘመኔ ውስጥ ፈታኝና አስደሳች ዓመታት ነበሩ ማለት እችላለሁ፡፡ በምርት ገበያ የአመራር ጊዜዬ አርባ የነበረው የሠራተኞች ቁጥር ከአንድ ሺህ በላይ የደረሰ ሲሆን አንድ የነበረው የኢትዮጵያ ምርት ገበያ ድርጅት መጋዘንም 55 ደርሷል፡፡ ሁለት መቶ ሚሊዮን ዶላር ማደግ ችሏል፡፡ የኢትዮጵያ ምርት ገበያ ድርጅት የሚሊዮን ገበሬዎች ገቢ አሻሽሏል፡፡ ግልፀነት ባለው አስተማማኝ የገበያ ሥርዓት አማካኝነት የግብይት ስጋቶችና ወጪዎችን መቀነስ በመቻሉ፣ ገበሬዎች ከምርታች የመጨረሻ ዋጋ ከፍተኛ ድርሻ ማግኘት ችለዋል፡፡

 

“ወደ ስት በሚያደርሰን ጎዳና ላይ የቆምነው፣እኛና እኛ ብቻ እንደሆንን ጽኑ እምነት አለኝ፡፡

የምርት ገበያ ድርጅትን ሳስተዳድር፣ ሥራን በቅጡ በማከናወን የሚገኘውን ደስታ ማጣጣምን ተምሬአለሁ፡፡ ሰዎችን በመምራት፣ ራዕዬ ሌሎች በደስታ ስሜት በማጥለቅለቅ፣ ሀሳቦችን ለደንበኞች በማጋራት እንዲሁም የድርጅትን መለያ ምልክትና ልዩ መታወቂያ በመፍጠርና በዳበር የሚገኘው ሀሴትና እርካታ ማጣጣምንም ተመሬአለሁ፡፡ ነገሮች ሲበላሹ ተወቃሿ እኔ እንደሆኩ እንዲሁም ከአካዳሚ ረዥም የሥራ ቀን በኋላ፣መብራት አጠፋፍቶ መውጣት የእኔ ድርሻ መሆኑንና አንዳንዴም ከባባድ ውሳኔዎችን ለመወሰን ለመወሰን አስፈሪ ብቸኝነትን መጋፈጥንም ተምሬአለሁ፡፡ የኢትዮጵያ ምርት ገበያ ስኬትና ዓለም አቀፍ እውቅና፣ በትላልቅ ሕልሞች ተዓምራዊ ኃይል ላይ የነበረኝን እምነት በእጅጉ አጠንክሮኛል፡፡ በሠራተኞቼ በተለይ ደግሞ በወጣት ሴቶች አዕምሮ ውስጥ ትልልቁን ነገር ለማለም መድፈር፣ አደጋን ሳይፈሩ ያሰቡትን ማከናወን፣ አዳዲስ ነገሮችን ለመሞከር ክምችቶች ቀጠና መውጣት እንዲሁም በቁርጠኝነትና በኋላ ጥልቅ ስሜት (በፍቅር ጭምር) መስራት የቱን ያህል አስፈላጊ እንደሆነ ለማስረጽ ሞክሬአለሀ፡፡ ወደ ስኬት በሚያደርሰን የራሳችን ጎዳና ላይ የቆምነው እኛና እኛ ብቻ እንደሆንን ጽኑ እምነት አለኝ፡፡

አንድ ሰው በየሺ ቀናት አንዴ ራስሽን እንደገና መፍጠር ሀሰአለብሽ” ብሎኝ ነበር፡፡ ድንቅ ሀሳብ ነው፡፡ አስር ዓመት ገደማ የሚሆነውን የሙያዬን የመጀመሪያ ክፍል ያሳለፍኩት በምርምር ነው፡፡ ከዚያም ለበርታ ዓመታት በልማት ባለሙያነት ሰራሁ፡፡ ለዚህም ቀጣዩን አስር ዓመት ደግሞ በንግድ ባለሙያት ለማሳለፍ አቅጃለሁ፡፡ ለዚህም ለመላው አፍሪካ ተመሳሳይ የምርት ገበያዎችን የሚፈጥር ተቋም መስርቻለሁ፡፡ ተቋሙ የእስካሁኑን ሥራዬን በሕገወጥ ተጽእኖ የሚያሰፋ ይሆናል፡፡ ከዚያም በኋላ ደግሞ ማን ያውቃል ምናልባት የበጎ አድራጎት ሥራ ውስጥ ልገባ እችላለሁ፡፡ ወይም ደግሞ ፖለቲካ ውስጥ፤ ብቻ ማንኛውም ነገር ሊሆን ይችላል፡፡

ትልቁን ፈተና የተጋፈጥኩት ከሴትነቴ ጋር ተያይዞ በመጣ ችግር አይደለም፡፡ የመመረቂያ ጽሁፍ አማካሪዬ ድጋፍ ቢያደርግልኝም፣ ቅሉ ልወልድ የደረስኩት ለእኔ እጅግ ከባድ ነበር፡፡ ከሁሉም የሚብሰው ፈተና ግን መስራት የምፈልገውን ነገር አይሳካም የሚሉ ሰዎች ሁል ጊዜ መኖራቸው ነው፡፡ ደግነቱ በልጅነቴ በራስ የመተማመን ስሜት በውስጤ ስለፀረሰ ይመስለኛል፣ እንዲህ ያሉ ሰዎች በሕይወቴ ውስጥ እጃቸውን እንዲያስገቡ አልፈቅድላቸው፡፡

ሌላው ፈተናዬ ሥራዬንና ቤተሰባዊ ሕይወቴን አመጣጥኖ መምራት ነበር፡፡ ሁለት ወርቅ የሆኑ ወንድ ልጆች በመውለዴ እድለኛ ነኝ፡፡ አብዛኛውን ጊዜ ከነሱ ጋር ማሳለፍ ብችልና የተለመደውን የእናትነት ወግ ባሳያቸው ደስ ይለኝ ነበር፡፡ በሁሉም ረገድ በጣም የምትመች ምናልባትም የእኔ እናት ለእኔ እንደነበረችው አይነት፣ ሕይወትን የምትቀይር እናት እሆናለቸው እያልኩ አስባለው፡፡ በተግባር ያደረግሁት ግን በተቻለኝ መጠን ልጆቼን ከሥራ ሕይወቴ ጋር ማዋሃድ ነው፡፡ በዶክትሬት ዲግሪ የመስክ ስራ ላይ ገና በማህፀን እያለም ጭምር ካልተለየኝ የበኩር ልጄ ጀምሮ ልጆቼ ነፍስ አውቀውም ጭምር ለኮንፈራንስም ሆነ ለውጪ ስራ ጉዞ ስወጣ፣ ከአጠገቤ ተለይተው አያውቁም፡፡ ከት/ቤት ሲመለሱ ቢሮዬ ውስጥ የቤት ሥራቸውን እየሰሩ ወይም እያነበቡ ሰዓቱን ያሳልፋሉ፡፡ በቻልኩ ጊዜ ሁሉ ቁርሳቸውን እሰራላቸዋለሁ፡፡ እራት አብረን እንበላለን አንድ ላይም እንፀልያለን እስኪተኙ ድረስ ያለውን ጊዜ አብረን እናሳልፋለን፡፡ ከዚያ በኋላ ወደ ሥራ ተመልሼ እሄድና አብዛኛው ጊዜ እስከ ማለዳ ድረስ እሰራለሁ፡፡ ማሀበራዊ ሕይወትና የስፖርት ማዕከል ማዘውተር ብዙም ትኩረት ያልሰጠኋቸው ነገሮች ነበሩ፡፡ እንግዲህ ሕይወታችንን የምንመርጠው እራሳችን ነንና የመረጥነውን ሕይወትም እንኖረዋለን፡፡ በእኔ በኩል በኖርኩት አንዳችም የምፀፀትበት ነገር የለም፡፡ ዕድለኛ ነኝ ማለት እችላለሁ፡፡ እልህኛ ስለሆንኩም ሊሆን ይችላል፡፡ እስካሁን የምኖረው ሕልሜን ነው፡፡ ዛሬ በውስጤ ያቺ የአፍሪካን ድህነት ለማጥፋት የምታለም የ15 ዓመት ታዳጊ ነኝ ይህንን ሕልሜን እንደማሳካው ደግሞ አሁንም አምናለሁ፡፡ ለዛሬ ልጃገረዶች የምለግሰው ሰዎች ሕልማቸውን ማሳካት እንደማትችሉ ሲነግሯችሁ በእጅ ብላችሁ አትስሙ፡፡ ለራሳችም ቢሆን ሕልማችንን ማሳካት አንችልም ብላችሁ ለሀሳብ መፍቀድ የለባችሁም፡፡ ሕልማችሁ ምንም ይሁን ምን አልሙት ውደዱት፣ እመኑት፣ ታገሉለት፣ ትጉለት፣ አትልቀቁት፤ ያን ጊዜ ታሳኩታላችሁ፡፡