Biography Catagories

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

Dr Mulatu Teshome

 

የፕሬዝዳንቱ ሕልም - ቤተመንግስቱን የሁሉ ማድረግ

የቀድሞው ፕሬዝዳንት ግርማ ወ/ጊዮርጊስሰ ከብሔራዊ ቤተ መንግስት ከወጡ በኋላ ለቁም ነገር አስተያየታቸውን ሲሰጡ “አሁን ነፃ  ወጣሁ፤ ቤተ መንግስት ውስጥ አጀቡ ብቻ ሳይሆን ብዙ ጫና አለው…” ያሉት ምን ማለት እንደሆነ የተረዳሁት ሁኔታውን ስመለከት ነበር፡፡

የፕሬዝዳንቱ ሕልም - ቤተመንግስቱን የሁሉ ማድረግጥቅምት 22/ደ2006 ዓ.ም ለአዲሱ የኢትዮጵያ ርዕሰ ብሔር ዶ/ር ሙላቱ ተሾመ በቸልታ የሚታይ ቀን አይመስልም፡፡ የዘመነ ኢህአዴግ አራተኛው ፕሬዝዳንት ሆነው ከተሾሙ ድፍን አንድ ወር የደፈኑበት ዕለት በመሆኑ ባለፉት 30 ቀናት በቤተ መንግስት ምን አከናወንኩ የሚል ጥያቄ እንዲያጭርባቸው ያደርጋል፡፡

በዚሁ ዕለት ከጠዋቱ 4፡30 አከባቢ ከቁም ነገር መጽሄት ዋና አዘጋጅ ታምራት ኃይሉ ጋር በመሆን በቤተ መንግስት ተገኝተናል፡፡ ቀጠሯችን ከፕሬዝዳንቱ ጋር ሲሆን ከፊት ለፊታቸው ተቀምጠን ጥያቄያዎችን ለመወርወር “ቁም ነገር” ያቀረበችው ጥያቄ ተቀባይነት በማግኘቱ ነው፡፡ እለታዊ ግጥጥሞሹ ደግሞ ሙላቱ በግርማ ወንበር ተከተለው ቤተ መንግስት ከገቡ አንድ ወር የደፈኑበትመሆኑ ነው፡፡

“ሕገ-መንግስቱ ላይ የተቀመጡትን የርዕሰ ብሔሩን ኃላፊነቶችን እያከናወንኩ ነው፡፡ በአገራዊ አጀንዳዎች ዙሪያም በሁሉ ቦታ የተቻለውን ያህል እየተንቀሳቀስኩ ነው፡፡ የሚሰለች ሳይሆን ጥሩ ሥራ ነው ብዬ አስባለው፡፡ ሲሉ ስለ አዲሱ የኃላፊነት ቦታ የአጭር ጊዜ ቆይታቸው የሚናገሩት ዶ/ር ሙላቱ አንኳር የሆኑ ጉዳዮች ለመከወን ግን አንድ ወር ገና መሆኑን ጠቁመዋል፡፡

ቤተ መንግስቱ

“ጥብቅ” ሊባል የሚችለውን የውጪ ፍተሻ አልፈን የእጅ ስልካችንን አስቀምጠን ወደ ውስጥ ስንዘልቅ በአረንጓዴ ተክሎች ያማረ ነፋሻማ አየር ያለውና በጥቅሉ  “ማራኪ” ብሎ መግለጽ የሚቀጥለው ግቢ ተቀበለን፡፡ ሁለተኛው የኢትዮጵያ ፕሬዝዳንት የነበሩት ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ “ዳንዲ የነጋሶ መንገድ” በሚባለው መጽሐፋቸው ላይ ስለ እዚህ ግቢ ሲገልጹ “ምንም እንኳ ቤተ መንግስቱ እጅግ ውብና ለኑሮ የሚመች ቢሆንም ችግሩ ነፃነት የሌለው መሆኑ ነው፡፡ ከሳሎኖቹ ምግብ ቤት መኝታ ቤቶችና ፎቅ ላይ ካሉ ክፍሎች በስተቀር ከበር በር ለሃያ አራት ሰዓት የማይለዩ በፈረቃ እየተቀያየሩ የሚጠብቁኝ ጠባቂዎች ነበሩ፡፡ ወደ ላይ ስንወጣና ስንወርድ፤ ወደ ቢሮ ገብቼ ስወጣ በሁለት በኩል ጥበቃ ነበረኝ፡፡” ብለው ነበር

አዲሱ ፕሬዝዳንት ከዚህ የደህንነት ጥበቃ የሚያመልጡ አይመስልም፡፡ ከቢሯቸው በር ላይ በርካታ ጠባቂዎቻቸውን ተመልክተናልለለ ሁለተኛው የውስጥ በር ኤሌክትሮኒካል ጥበቃ አልፈን ፕሬዝዳንቱ እኛን ከማግኘታቸው በፊት አንድ ከአሜሪካ የመጣ ልዑካን ተቀብለው እያስተናገዱ ብን ጠብቀናቸዋል፡፡ ሲቪሎች ባቂዎችምም ሳሎኑን በትኩረት ይቃኛሉ፡፡ የቀድሞው ፕሬዝዳንት ግርማ ወ/ጊዮርጊስ ከብሔራዊ ቤተመንግስት ከወጡ በኋላ ለቁም ነገር አስተያየታቸውን ሲሰጡ አሁን ነፃ ወጣሁ፤ ቤተ መንግስቱ ውስጥ አጀቡ ብቻ ሳይሆን ብዙ ጫና አለው….” ያሉት ምን ማለት እንደሆነ የተረዳሁት ሁኔታሁት ሁኔታውን ስመለከት ነበር፡፡

በወሬ ደረጃ የሰማሁትን የንጉሱ (አፄ ኃይለ ስላሴ) ዘመን ለእንግዶች የሚቀርብ የሻይ ጣዕም ዝና ታውሶኝ ስለነበር የቤተመንግስትን ሻይ የመጠጣት ጉጉት ነበረኝ፡፡ የመስተንግዶ ደንብ ልብስ የለበሱት አስተናባሪዎች ሻዩውን ጣዕም ግን በአንድ አነስተኛ ካፌ ከምጎነጨው የተለየ ጣዕም አልነበረውም፡፡

ከዶ/ር ሙላቱ ጋር

በ1949 ዓ.ም በቀድሞ ወለጋ ክፍለ ሀገር ውስጥ በምትገኘው አርጆ ከተማ እንደተወለዱ የሕይወት ታሪካቸው የሚያሳይ ዶ/ር ሙላቱ ተሾመ የፊት ገጽታቸው ቁጡሰ ይመስላል፡፡ ሲያወሩ ግንባራቸው አራት ቦታ መሸብሸብን ስትመለከት አስበርጋጊ ስብዕና እንዳላቸው ልትጠረጥሩ ትችላላችሁ፡፡ በ82 ደቂቃ የቤተ መንግስቱ ቆይታችን ከዚህ ፍጹም ተቃራኒ መሆናቸውን ተመልክተናል፡፡

ቀለል የሚሉና ስሜት መፍጠር የሚችሉ ዓይነት ናቸው ከጥያቄዎቻችን ጋር ደጋግመን እንድንጎበኛቸው ቃል በመግባት ተቀራርበው ለመስራት ፍቃደኛ መሆናቸው አሳይተዋል፡፡ ወደ እን ስልኮቻቸው የሚመጡ ጥሪዎችን እንደሚመልሱ አጠገባቸው የተቀመጡት ሶስት ዘመናዊ “ስማርት ፖኖች” ጠቋሚ ናቸው ለቃለ ምልልሱ ክብር ሲሉ ወደ ተንቀሳቃሽ ስልኮቹ የሚመጡትን ጥሪዎችን ሳያነሱ ያቋረጥኳቸው ነበር ድምጽ እና ንዝረት አልባ ሞድ ላይ ከማድረጋቸው በፊት፡፡

መስከረም 27/2006 ዓ.ም ፕሬዝዳንት ሆነው “ሲቀቡ” ብቸኛው የተቃዋሚ ፓርቲ ተወካይ የአቶ ግርማ ሰይፉን ይሁንታ ጭምር በማግኘት በሙሉ ድምጽ የተመረጡት ዶ/ር ሙላቱ ተሾመ ለኢትዮጵያ የዴሞክራሲ ግንባታ ገዢውም ሆነ ተቃዋሚ ፓርቲዎችን በእኩል ዓይን በመመልከት ከጎናቸው እንደሚቆሙ በቃለ ምልልሱ ወቅት ቃላቸውን ሰጥተዋል፡፡ ሁሉም ለአገራችን የሚጠቅም ነገር ሲሰሩ አይዟችሁ ማለት ይገባል፡፡ ብለዋል፡፡ “ ፓርቲዎቹ በተቃራኒ ከተጓዙ ደግሞ አረ ተው! ብሎ መምከር ተገቢ ነው፡፡

እንደ ፕሬዝዳንቱ ገለፃ ከሆነ በገዢውም ሆነ በተቃዋሚ ፓርቲዎች ዙሪያ ለመስራት ያላቸው ፍላጎት ከመምከር እና ከመበረታታም ከፍ ያለ ነው፡፡

በእርግጥ “የሁሉም ፓርቲዎች ፍላጎት ከሆነ አንድ ላይ ተቀምጦ መምከር ይቻላል፡፡ ፓርቲዎችን የማቀራረብ ሚና መጫወት በሌሎች አገርም የተለመደ ነው፡፡ ይህን ማድረግ የዜግነትም ግዴታ ነው፡፡ የሚሉት መላቱ “ እንደ ሁኔታው በቅርብ  ጊዜ ይህን ማድረረግ የምንችል ይመስለኛል፡፡ ብለዋል፡፡ ዶክተሩ ይህንን በብልሀት መከወን ከቻሉ የተከበሩ አቶ ግርማ ሰይፉ የአንድነት ለዲሞክራሱ እና ለፍትህ ም/ፕሬዝዳንት) በፓርላማ ፕሬዝዳንት ሆነው እንዲመረጡ ድምጽ ሲሰጧቸው “በአገራችን መግባባት እንዲሰፍን ተቃዋሚዎችን እና ገዢው ፓርቲ ተነጋጋሪው በአገራዊ ጉዳዮች ላይ የምንሰራበት ምቹ ሁኔታ ለመፍጠር ትኩረት ሰጥተው ይሰራሉ በሚል ተስፋ ድጋፋችንን እንሰጣለን ሲሉ ማሳሰቢያ ላይ ተመርኩዘው የሰጧቸው የድጋፍ ድምጽ ዋጋ እንደነበረ ማሳየት ይችላል፡፡

አዲሱ ርዕሰ ብሔር በእሳቸው የስልጣን ዘመን በቤተ-መንግስት የሚደረጉ አገራዊ ጉዳይ ላይ የተመሰረቱ የምሳ እና ራት ግብዣዎችን ተቃዋሚ ፓርቲዎችን ባገለለ መልኩ እንደማይሆን ቃል ገብተዋል፡፡  ፋይዳ ያለው ነገር ለመስራት ቤተ መንግስቱን የሁሉ ለማድረግም ተልመዋል፡፡ እውን ቃላቸውን ጠብቀው ይህን በተግባር ያውሉታል? በመጪው ጊዜ የምናየው ይሆናል፡፡

አቅም ያለው ሰው ፕሬዝዳንት ይሆናል

በሕገ-መንግስቱ አንቀጽ 69 ላይ ፕሬዝዳንቱ የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፓብሊክ ርዕሰ ብሔር (Head of state) መሆኑን አስቀምጧል፡፡ ስልጣንና ተግባሩም አንቀጽ 71 ከጠቅላይ ሚኒስትሩ (Head of Government) በእጅጉ ያነሰ ያደርገዋል፡፡ አገሪቷን በውጪ አገሮች የሚወከሉትን አምባሳደሮች እና ሌሎች መልዕክተኞች ይሾማል፡፡

 ይህም ቢሆን በጠቅላይ ሚኒስትሩ አቅራቢነት የሚከወን ነው፡፡ ሌላው የፕሬዝዳንቱ ዋና ተግባር ተደርጎ የሚወሳው የውጪ አገር አምባሳደሮችን ሹመት መቀበልና መሸኘት ነው፡፡ በዚህ የተነሳም “ፕሬዝዳንቱ ፈገር ነው” የሚሉ እና የስልጣናዊ አቅሙ የመነመኑበት ቦታ መሆኑን በአገራችን ተደጋግሞ ተነግሯል፡፡ በዚህ አባባል እንደማጠናከሪያነት የሚወሰደው ደግሞ “ስለ ሕግ አፀዳደቅ፡፡ የሚገልፀው ሌላው የሕገ መንግስቱ አንቀጽ 57 ነው፡፡ ምክር ቤቱ መከሮ የተስማማነት ሕግ ለአገሪቱ ፕሬዝዳንት ለፊርማ ካቀረበ በኋላ ፕሬዝዳንቱ በአስራ አምስት ቀናት ውስጥ ካልፈረመ ሕጉ በሥራ ላይ ይውላል ማለቱ ሲታይ (ፈረመም፤አልፈረመም ሥራ ላይ መዋሉ) የርዕሰ ብሔሩ ስልጣን ለማነሱ እንደማሳያ ያቀርባል፡፡

ይሄን የተመለከቱ እንደ እነ አቶ ቡልቻ ደመቅሳ አይነት ፖለቲከኞችም አቅም ያለው ሰው በፕሬዝዳንትነት ወንበር ላይ ተቀመጥ ሲባል እሺ እንደማይል በመጠቀም በገደምዳሜ ቦታው የአቅም አልባዎች መሆኑን ይገልፃሉ ቁመተ መስሎን የሚያስከነዳ የአፍሪካ ምድራዊ አቀማመጥ  ምስል ከኋላቸው በተንዠረገገበት ቢሮአቸው የሚገኙት አዲሱ ፕሬዝዳንት አምባሳደር ዶ/ር ሙላቱ ተሾመ ግን በዚህ የሚስማሙ አይመስሉም፡፡ ዛሬም ሆነ ወደፊት ወንበሩ ላይ መቀመጥ ያለበት አቅም ያለው ሰው መሆኑን አበክረው ይከራከራሉ፡፡ ባለፉት 30 ቀናት ሥራ አጥቼ አንድም ያዛጋኝ እና ጭንቅላቴን ያከከኩበት ቀን አልነበረም” በማለት በሥራ መወጠራቸውን በማሳያነት አቅርበው ብዙ ለመስራት የሚያስችል ወንበር መሆኑን ጠቁመዋል፡፡ በተለይም በኢኮኖሚ ዲፕሎማሲው መስክ አበከረው በመስራት ተጽዕኖ መፍጠርን ይሻሉ ለ”ሁሉ” ለማድረግ ባቀዱት ብሔራዊ ቤተ

 

የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ሙላቱ ተሾመ

በበ1974 ዓ.ም በፖለቲካል ኢኮኖሚ ፍልስፍና የመጀመሪያ ዲግሪ በ1980 ዓ.ም በዓለም አቀፍ ሕግ ሁለተኛ ዲግሪ፤በ1983 ዓ.ም የዶክትሬት ዲግሪያቸውን በዓለም አቀፍ ሕግ (በቤጂንግ ዩኒቨርሲቲ)በጃፓን ከ1984-86 ዓ.ም በቻይና ከ1986-87፤ በቱርክ ከ1999 የኢትዮጵያ ፕሬዝዳንት ሆነው እስከተሾሙበት ጊዜ ድረስ ባለ ሙሉ ስልጣን አምባሳደር ከ1987-1993 ዓ.ም የኢኮኖሚና ትብብር ሚኒስቴር የአለም አቀፍ ኢኮኖሚ ትብብር ሚኒስቴር የዓለም አቀፍ ኢኮኖሚ ትብብር ዘርፍ ምክትል ሚኒስቴር

ከ1993-94 ዓ.ም የግብርና ሚኒስቴር፤ ከ1994-98 ዓ.ም የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ ሆነው ሰርተዋል፡፡ አዲሱ ፕሬዝዳንት አምባሳደር ዶ/ር ሙላቱ ተሾመ በብሔራዊ ቤተ መንግስት ለ82 ደቂቃዎች ያህል ከቁም ነገር ጋር ተከታዩን ቆይታ አድርገዋል፡፡

 

ቁም ነገር፡- ዛሬ ጥቅምት 27 በፕሬዝዳንትነት ተመርጠው ወደ ቤተ መንግስት ከገቡ አንድ ወርዎት ነውና፤ ሕይወት በበተ ምን ይመስላል?

ፕሬዝዳንት ሙላቱ፡- ሳቅ/ ቆንጆ ጥያቄ ነው፤ ቀኑን ካልኩሌት አድርጋችሁ የመጣችሁ ነው የሚመስለው፤ እንደተባለው ዛሬ አንድ ወሬ ነው፤ እንግዲህ እስከ ዛሬ ድረስ ካለው የሥራ እንቅስቃሴም ሆነ ራሴ ባለኝ የስራ ግንኙነት ጥሩ ነው፡፡ በግሌም በኑሮ በኩል ያየሁት ችግር የለም በአጠቃላይ የሀገሪቱ ፕሬዝዳንት የሚሆን ሰው በሕገ-መንግስቱ ላይ በግልጽ የተቀመጡ የሥራ ኃላፊነቶች አሉ፤ እነሱን እሰራለሁ፤ ከዚህም በላይ የሀገሪቱን ዕድገት የሚያፋጥኑ ልዩ ልዩ ሥራዎችን ለመስራት አስባለሁ፡፡ ይሄ ጉዳይ አይመለከተኝም የምለው ነገር አይኖርም፡፡ ለሀገሪቱ የሚጠቅም እስከሆነ ድረስ የተቻለኝን ሁሉ ለማድረግ ስንቀሳቀስ ነው ከዚህም በፊት የቆየሁት፡፡ በዚሁ እቀጥላለሁ ብዬ ነው የማስበው ስራውም የሚያሰለች አይደለም፡፡ ከተለያዩ ሰዎች ጋር መገናኘት ስላለው ማለት ነው፡፡

ቁም ነገር፡- ባለፈው አንድ ወር ግን ምን ምን ተግባራትን አከናወኑ

ፐሬዝዳንት ሙላቱ፡- ይሄ ነው የምለው የተሰሩ አንኳር ጉዳዮች የሉም ገና ነው፤ ነገር ግን እኔን  ለመጠየቅ ከሚመጡ ሰዎችና ደስታቸውን ሊገልፁልኝ ከሚፈልጉ ሰዎች ጋር እንደተገናኘሁ ነው፡፡ እንግዲህ በዚህ በኩል ከሀገር ውስጥ ብቻ ሳይሆን ከውጪ ሀገር በግሌም የማውቃቸው በኢትዮጵያ ውስጥ መዋዕለንዋያቸውን ለሚያፈሳሉ እንዲሁም ከዚህ በኋላ ኢንቨሰት ማድረግ ከሚፈልጉ የተለያዩ ሰዎች ጋር ግንኙነት ሳደርግ ነበር፡፡

ቁም ነገር፡- የሀገሪቱ ፕሬዝዳንት ሆነው እንዲሰሩ ለመጀመሪያ ጊዜ መታጨትዎን የነገርዎት ሰው ማነው

ፕሬዝዳንት ሙላቱ፡- ትንሽ ካሰቡ በኋላ እንግዲህ እንደምታውቁት ቀደም ሲል በስራዬ ላይ ቱርክ አንካራ ነበር የለሁት እንደ ማንኛውም ጊዜ እንደሚደረገው የውጪ ጉዳይ  የሥራ ኃላፊዎች በውጪ ሀገር ያሉ ዲፕሎማቶችን ጠርተው የሚነጋገሩበት የተለመደ ዓመታዊ ሥራ አለ፡፡ በዚህ በኩል እኔ ቀደም ሲል የተሰጠኝ ሥራ አዋሽ ወልዲያ የባቡር ሀዲድሰ ግንባታ ፕሬጀክትን መከታተል ስለነበር እሱን የማስፈፀም እሱን ሥራ ነበር የምሰራው፤ እዚህ ሀገር ከተመለስኩ በኋላ ከጠቅላይ ሚኒስቴር ጽ/ቤት አስቸኳይ ስብሰባ አለ ሲባል ዶክመንቶቼንም ሰብስቤ የመጣሁት ለዚሁ ነበር፡፡

ቁም ነገር፡- መቼ ማለት ነው

ፕሬዝዳንት ሙላቱ፡- ይሄ እንግዲህ እንደሰኞ ፓርላማው ሊከፈት ወደ ሀገር ቤት የመጣሁት ማክሰኞእንደሚያደርገው ወዲያውኑ ስንብት ባላደርግም ወደ ቱርክ ተመልሼ ማስተካከል ያለብኝ ነገሮች ለማስተሰካከል ማለትም የክሬዲት ካርድ መመለስን የመሳሰሉትን አጠናቅቄ ለመመለስ ሄድኩ፤ ቅዳሜ ማታ ተመልሼ መጣሁና ሰኞ ፓርላማው ላይ ተገኘሁ ማለት ነው፡፡

ቁም ነገር፡- ማነው መታጨትዎን ለእርስዎ የነገርዎት

ፕሬዝዳንት ሙላቱ፡- ጠቅላይ ሚኒስትሩ ናቸው የነገሩኝ፡፡

ቁም ነገር፡- ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር ሲጠሩ አልተጠራጠሩም

ፕሬዝዳንት ሙላቱ፡- ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትሩ ብቻ ሳይሆኑ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩም አምባሳደሮችን የመጥራት ስልጣን አላቸው፤ በወቅቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ዶ/ር ቴዎድሮስ በሀገር ውስጥ ስላልነበሩ ነው ጠቅላይ ሚኒስትሩ የጠሩኝ ብዬ ነው ያሰብኩት፡፡ ያም ሆኖ በፕሬዝዳንትነት እንድሰራ ሊነግሩኝ ነው የጠሩኝ የሚል ግምት በኔ ጭንቅላት ውስጥ አልነበረም፡፡

ቁም ነገር፡- ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሲነግርዎት ምን አይነት ስሜት ተሰማዎት

ፕሬዝዳንት ሙላቱ፡- እንግዲህ ያልጠበቅሁት ነገር ነው፤ ጠቅላይ ሚኒስትሩም የመንግስት አቋም እነዚህ እንደሆነ እንድታውቅ ነው ያሉኝ፡ ከዚህ በኋላ ደግሞ ገና ፓርላማ ቀርቦ ሁኔታው መጽደቅ ያለበት ዕጩ ፕሬዝዳንቱን የማቅረብ ስልጣን አለው ፓርላማው ስለሆነ እንደዚህ ታስቧል፡፡

በኔ በኩል አንድ ነገርህ ስለተባለ ከወዲሁ እንድትዘጋጅበት ነው ያሉኝ በወቅቱ እንደማንኛውም ሰው “እንዴት እሆናለሁ” የሚል ስሜት ተሰምቶኛል፡፡ ምክንያቱም እዛ ውጪ ሀገር የሰቀልኩትን ኮት እንኳን ሳላመጣ ወይም ቁምሳጥኔ ሳልቆልፍ የሚል ስሜት መጥቶብኛል፡፡ ከዚህ ባለፈ ደግሞ ለሀገር እስከሆነ ጊዜ ድረስ መንግስታዊ ኃላፊነት ሲመጣ የምት ቦተታ ቢሆን ተቀብለሎ ለመስራት መዘጋጀት አለ፡፡ ከዚህ በፊትም ከአንድ መ/ቤት ወደ ሌላ መ/ቤት ከአንድ ተቋም ወደ አንድ ተቋም ተዘዋውሮ መስራት ለኔ አዲስ አይደለም፡፡ በእርግጥ ጊዜው ማጠር ትንሽ ድንጋጤ ፈጥሮብኝ ነበር፡፡ ከሀገር ውጪ ያሉ የቤተሰብ የልጅ ጉዳይ ትንሽ ያሳስብ ነበር፡፡

ቁም ነገር፡- ከሰሙ በኋላ ወደ ቱርክ ተመልሰው ቅዳሜ ነው የመጡትና ለባለቤትዎ ነግረዋቸው ነው የተመለሱት

ፕሬዝዳንት ሙላቱ፡- አልነገርኳትም፣ ፕሬዝዳንት ሊሆን ነው ብዬ ልነግራት አልችልም፤ ምክንያቱም ገና ፓርላማ ቀርቦ ሲፀድቅ ነው የሚታወቀው፡፡ ፓርላማው የማይቀበለኝ ቢሆንስ ስለዚህ ሳልነግራት ነው የመጣሁት፡፡

ቁም ነገር፡- በዚሁ አጋጣሚ ባለቤትዎን እንተዋወቃቸው ማን ይባላሉ፡፡

ፕሬዝዳንት ሙላቱ፡- ባለቤቴ ወ/ሮ መዓዛ አብርሃም ነው የምትባለው አንድ ወንድ ልጅ አለን፡፡

ቁም ነገር፡- በምን ስራ ላይ ነው ያሉት

ፕሬዝዳንት ሙላቱ፡- የቤት እመቤት ናት ትዳር ከመሰረትን ጊዜ ጀምሮ አምባሳደር እስከሆንኩበት ጊዜ ድረስ ስራ አትሰራም፤ በቬይና ኮንቬንሽን መሰረት የአምባሳደር ሚስቶች ስራ እንዲሰሩ ስለማይደረግ የቤት እመቤት ናት፡፡ በሕጉ መሰረት ባለቤትዎን ከኋላ ሆና መርዳት ነው ያለባት፡፡

ቁም ነገር፡- የት ነው የተገናኛችሁት

ፕሬዝዳንቱ ሙላቱ፡- የተዋወቅነው ጃፓን ነው፡፡ የተጋባነው ወደ ቻይና በአምባሳደርነት ከተዘዋወርኩ በኋላ ነው፡፡

ቁም ነገር፡- መቼ ማለት ነው

ፕሬዝዳንት ሙላቱ፡- በ1987 ዓ.ም ገደማ ማለት ነው፡፡

ቁም ነገር፡- አሁን አብረዎት ናቸው፡፡ እዚሁ ቤተመንግስት ገብተዋል ወይስ እዛው ናቸው

ፕሬዝዳንት ሙላቱ፡- ልጄ ሌላ ሀገር ነው ያለው አዳሪ ት/ቤት ነው፡፡ ምናልባት ሁኔታው አመቺ የሆነው ለልጃችን ሳይሆን አይቀርም ምክንያቱም ጊዜው ቀደም ብሎ ት/ቤት የተከፈተበት ወቅት ስለነበር ልጄ ቀድሞ ት/ቤት ባይገባ ኖሮ ወደዚህ ለመሀል አቋርጦ ለመምያት ያስቸግረን ነበር፡፡

ቁም ነገር፡- ፕሬዝዳንት ሆነው በፓርላማ ከተመረጡ በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ በስልክ “እንኳን ደስ ያልዎት” የሚል መልዕክት የመጣው ከማን ነው

ፕሬዝዳንት ሙላቱ፡- በጣም ብዙ ስልክ ነበር በዕለቱ የተደወለልኝ የመጀመሪያው ማን እንደሆነ ግን ለማስታወስ ያስቸግረኛል፡፡ አብዛኛው ከቱርክ ካሉ ወዳጆቼ እንደነበር ግን መናገር እችላለሁ፡፡ አብዛኛዎቹ ከቱርክ ይደውሉ እንጂ ከቻይና ከአሜሪካም ብዙ ሰዎች ደውለውልኛል፡፡ ከቱርክ የሪፐብሊኩ ፕሬዝዳንት ጠቅላይ ሚኒስትሩና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሪም ደውለዋል፡፡

ቁም ነገር፡- ከሀገር ቤትስ

ፕሬዝዳንት ሙላቱ፡- ከሀገር ቤትም ብዙ ስልክ ነበረኝበእርግጥ በሀገር ውስጥ እንደዚህ አይነት እንኳን ደስ ያለህ በሚል መደወል አልተለመደም፡፡ ግን ብዙ ሰዎች ደውለውልኛል፡፡ ኢሜልም ተጨናንቋል፡፡

ቁም ነገር፡- የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ መለስ ዜናዊን ደሞዛቸው ስንት እንደነበር የተጠየቁት በቁም ነገር መጽሄት ነበር አሁንም ተመሳሳይ ጥያቄ ለእርስዎ ልናቀርብ ነው፡፡ በአሁን ወቅት የፕሬዝዳንትነት ደሞዝዎ ምን ያህል ነው

ፕሬዝዳንት ሙላቱ፡- /ሳቅ/ ገና ሙሉ ወር ሆኖኝ ደሞዝ አልተቀበልኩም ስለዚህ ስንት እንደሚደርሰኝ ገና አላወቅኩም/ሳቅ/ እስካሁን ያለሁት በአምባሳደር ደሞዝ ነው በእርግጥ ከአምባሳደር ደሞዝ ጋር የሚቀራረብ እንደማይሆን ተስፋ አደርጋለሁ፡፡

ቁም ነገር፡- እሺ አምባሳደርነትዎ የሚያገኙት ደሞዝ ምን ያህል ነበር

ፕሬዝዳንት ሙላቱ፡- ምን ያደርግላቸሀዋል/ሳቅ/

ቁም ነገር፡ ኢትዮጵያ ለአምባሳደሮች ምን ያህል እንደምትከፍል ለማወቅ ያህል ነው

ፕሬዝዳንት ሙላቱ፡- ሳቅ/ የአምባሳደር ደሞዝ የሚነገር አይደለም ንገር ስላልተባልኩ አልነግራችሁም አሁን ካለሁበት ቦታ እንደሚበልጥ ግን መናገር እችላለሁ፡፡

ቁም ነገር፡- ቤተሰብም ወንድም እህት ስንት አሉ

ፕሬዝዳንት ሙላቱ፡- የእኛ ቤተሰብ ብዙ ነው 10 ልጆች ከአንድ እናትና አባት የተወለድነው፡፡ ሁሉም ራሳቸውን ችለዋል፡፡ በአብዛኛው የመንግስት ሠራተኞች ናቸው ውጪ ሀገር የሉም አለ፡፡

ቁም ነገር፡- እርስዎ ስንተኛ ልጅ ነዎት

ፕሬዝዳንት ሙላቱ፡- አሁን በሕይወት የሉም ሁለቱም ያጣኋቸው ቱርክ ሆኜ ነው፡፡

ቁም ነገር፡- ቀደም ሲል ወደዚህ የሥራ ኃላፊነት ከመምጣትዎ በፊት በኦህዴድ አባልነትዎ የተለያዩ የመንግስት ስልጣን ላይ እንደነበሩ ይታወቃል አሁን ፕሬዝዳንት ሲሆኑ ግን ፕሬዝዳንትነትዎን ለገዢው ፓርቲ አባላት ብቻ  ሳይሆን ለተቃዋሚዎችም መሆኑ ይጠበቅብዎታልና በዚህ ረገድ ምን ያህል ከፖለቲካ ወገንተኝነት ነፃ ሆነው ስራዎን ሲሰሩ ይችላሉ

ፕሬዝዳንት ሙላቱ፡- ብዙ የሚያስቸግረኝ አይመስለኝም፤ ዋናው ነገር ፕሬዝዳንቱ ለፌደራል ስርዓቱና ለሕገ-መንግስቱ ተገዢ እስከሆነ ጊዜ ድረስ የሚያስቸግር ነገር ይኖራል ብሔ አላስብም፡፡ ሕገ-መንግስታ ችን በዚህ በኩል በግልጽ ያስቀመጠው ነገር አለ፤ የሪፐብሊኩ ፕሬዝዳንት ከፓርላማ አባላት መሀከል ከተመረጠ ወንበሩን ይለቃል ይላል፡፡ ወንበሩን ብቻ ይለቃል መልቀቅ ሳይ የፖለቲካ ወገ ከነበረም ከፓርቲው ወገንተኝነቱን ይለቃል፣ ኢህአዴግ አባልነቱም ይለቃል ማለት ነው፡፡ የአንድነት ፓርቲ አባል ከነበረም ከፓርቲው ይለቃል፡፡ የግል ተመራጭም ከሆነ የፓርላማ ወንበሩን ለቆ ነው ፕሬዝዳንት የሚሆነው እኔም በፓርላማው ፕሬዝዳንት ሆኜ ቃለ መሀላ እስከሚፈፀም ጊዜ ድረስ የኦህዴድ አባል ብሆን ችግር የለውም፡፡ ከዛ በኋላ ግን መቀጠል ስለማልችል ከድርጅት አባልነቴም ለቅቄያለሁ፡፡ የፓርላማ አባል ብሆን ኖሮም ደግሞ ወንበሬን እለቅ ነበር፡፡

ቁም ነገር፡- ሕገ-መንግስቱ ግን ፕሬዝዳንቱ የፓርላማ ወንበሩን ስለመልቀቅ እንጂ ከድርጅት አባልነት ለመልቀቅ አይገልጽም፡፡

ፕሬዝዳንት ሙላቱ፡- ትክክል ነው ነገር ግን ሕገ-መንግስት መሰረት አድርጎ የወጣው የፕሬዝዳንቱ ማቋቋሚያ አዋጅ ላይ ይሄ በግልጽ ሰፍሯል፡፡ ስለዞህ ፕሬዝዳንቱ ወገንተኛ የሚሆንበት ሁኔታ የለም፡፡

ለሁሉም ዜጎች በእኩልነት ነው ማገልገል ያለበት፡፡ ከህግ አንፃር ይሄ ነው፤ ከሞራል አንፃርም የኢትዮጵያ ፕሬዝዳንት ከሆንኩ በኋላ ለአንድ ‹የፖለቲካ ፓርቲ ወይም ብሔር የምወግንበት ምክንያት የለም፡፡

ለምሳል እኔ ኦሮሞ ነኝ ግን ፕሬዝዳትነቴ ለኦሮሞ ሕዝብ ብቻ አይደለም ለሁሉም የኢትዮጵያ ሕዝብ ነው፡፡ ከሀይማኖት አንፃርም ለአንድ ኃይማኖት ተቋም ብቻ ሳይሆን ለሁሉም ኃይማኖቶች ርዕሰ ብሔር ሆኜ ነው የምሰራው፡፡ በእኩልነት ሁሉንም ልታገለግል ትችላለህ ወይ ላልከው “አዎ” ነው መልሴ፡፡

ቁም ነገር፡- ከዚህ ጋር ተያይዞ በፓርላማ ሲመረጡ የፓርላማው ብቸኛው የተቃዋሚ ፓርቲ አባል አቶ ግርማ ሰይፉ ፕሬዝዳንቱ በስልጣን ቆይታቸው ገዢውን ፓርቲ ተቃዋሚዎችን በሀገራዊ ጉዳይ ላይ ተነጋግረን የተሻለ ሥራ እንድንሰራ ጥረት ያደርጋል “በሚል ተስፋ ድምፃችንን እንሰጣቸዋለን” ነበር ያሉትና በዚህ ረገድ በቀጣዮቹ 6 ዓመታት ምን ለመስራት ሀሳብ አለዎት

ፕሬዝዳንት ሙላቱ፡- ፕሬዝዳንት አስታራቂ አይደለም፡፡ የዚህ አይነት ሚና እንዲኖረውም መጠበቅ የለበትም፡፡ ግን ሀገራችን ካለችበት ተጨባጭ ሁኔታ ተነስቶ በገዢው ፓርቲም ሆነ ለተቃዋሚዎች እንዲህ ብታደርጉ ጥሩ አይደለም ወይ በሚል ምክር ሊለግስ ይችላል፤ ያንን ለማድረግ እችላለሁ፡፡ ለሀገራችን ልማት ዲሞክራሲና ሰላም የማይጠቅም ከሆነም አረ ተው ብሎ መምከሩ ይኖራል፡፡ በሌሎችሀገሮችን እንደሚታየውም የጋራ ሀገራዊ በሆነ ጉዳዮች ላይም የፓርቲዎቹ ፈቃደኛነት እስካለድረስ በጋራ ቁጭ ብሎ ለመወያየት ይችላል፡፡

ቁም ነገር፡- ብዙ ጊዜዎን በውጪ ሀገር ከማሳለፍዎ ጋር በተያያዘ በነፃነት እንደ አንድ ግለሰብ የፈለጉበት ቦታ ይሄዱ ነበር አሁን ግን ከፕሮቶኮልም ይሁን ከደህንነት አንፃር የሚቻል አይሆንም ከዚህ አንፃር በምን ነበር የሚዝናኑት

ፕሬዝዳንት ሙላቱ፡- እንግዲህ በተወሰነ ደረጃ እነዚያን አይነት ሕይወቶች ላይኖሩ ይችላሉ፡፡ እኔ ውጪ በነበርኩበት ጊዜ የባህር ዳርቻ ላይ ሄጄ መዝናናት ነበር የሚያስደስተኝ፡፡ በተለይ የበጋውን ሙቀት ነጭ አሸዋ ላይ በጀርባ ተንጋሎ መዝናናት ነው የሚያስደስተኝ፡፡ የባህር አከባቢ ላይ መቆየት  ደስ ይለኛል፡፡ የሚገርማችሁ የኤቪያ ሱናሚ አደጋ ጊዜ በ2004 ልጄ 4 ዓመቱ ነበር፡፡ ከልጄ ጋር ደቡብ ቻይና ባህር ዳርቻ ላይ ሆነን ነው ያ ሁሉ ህዝብ በሱናሚው አደጋ የደረሰበት፡፡ ፊሊፒንስና ኢንዶኔዢያ ላይ ከባድ ጉዳት አድርሷል፡፡ እኛ ሆቴላችን ከተመለስን በኋላ ነው በሰበር ዜና በቴሌዥን ላይ ያ ሁሉ አደጋ መድረሱን የተመለከትኩት ነው፡፡ ያም ሆኖ ከባህር ዳርቻ ከዛም በኋላ አልተለየሁም ግን ኮታዬን ስለወሰድኩ ከዚህ በኋላ ባይኖርም ችግር የለውም፡፡

ቁም ነገር፡- እዚህ ቢሮ ከገቡ በኋላ የግል ጋዜጦችን የመከታተል ዕድል አልዎት

ፕሬዝዳንት ሙላቱ፡- አዎ የሚያመልጡኝን አነባለሁ፡፡

ቁም ነገር፡- የተቃዋሚ ፓርቲ አባል የሆኑት አቶ ቡልቻ ደመቅሳ በአዲስ አድማስ ጋዜጣ ላይ ስለእርስዎ “አቅም ያለው ሰው እሺ ብሎ ይሄን ቦታ አይቀበልም፡፡ የሚል አስተያየት ሰጥተው ነበር በዚህ ላይ የእርስዎ አስተያየት ምንድነው

ፕሬዝዳንት ሙላቱ፡- እኔ ሁኔታውን የማየው የሪፐብሊኩ ፕሬዝዳንት የሚሆን ሰው እንደውም አቅም ያለው ሰው መሆን አለበት ብዬ ነው፡፡ እኔም ሆንኩ ሌላ ሰው እዚህ ቦታ ላይ መምጣት ያለበት ሰው ለምልክት ብቻ የሚቀመጥ ሰው መሆን የለበትም፡፡ የሚገርማችሁ ባለፈው አንድ ወር እዚህ ቦታ ከመጣሁ ቀን ጀምሮ አንድም ቀን ያለስራ እያከኩ የተቀመጥኩበት ቀን የለም፡፡ ለምሳሌ ሰዎቹ ከውጭ  ሀገር ይመጣሉ፡፡ ሰዎቹ ሲመጡ በሀገራችን ቁልፍ ቁልፍ የልማት አጀንዳዎች ላይ ማብራሪያ እሰጣለሁ፣ መንግስት የሚያበረታታቸውን የሥራ ዘርፎች በመለየት ወደዚህ ዘርፍ እንዲገቡ አደርጋለሁ፡፡ አንድም ቀን ስራ ፈትቼ ራሴን እያከኩ የተቀመጥኩበት ቀን የለም፤ ከዚህ አንፃር አቶ ቡልቻ የሰጡትን አስተያየት የግላቸው አስተያየት አድርጎ መውሰድ ነው የሚሻለው፡፡ በኔ በኩል ግን ውጪ ሆኜ በአምባሳደርነቱ የሚሰራውን ሥራ እነዚህም ሆኜ ልሰራው እችላለሁ፡፡ ምናልባት ይህንን ቦታ ልዩ የሚያደርገው ተሰፍሮና ተለክቶ የሚሰጥ ስራ የለም፡፡ ግን እንደማንኛውም  የሀገሪቱን ልማት ለማፋጠን እምደ፣ቶጋ ሰው የራሴን ጥረት አደርጋለሁ፡፡ አስረዘምኩባችሁ መሰለኝ/ሳቅ/

ቁም ነገር፡- በሕገ-መንግስቱ ላይ በግልጽ ለፕሬዝዳንቱ ከተሰጡት ስልጣኞች መሀከል የሞት ፍርድን የማጽናት ወይም ይቅርታ የማድረግ ጉዳይ ነው ብዙ ሀገሮች የሞት ፍርድን ከሕጎቻቸው ውስጥ እያለወጡ ነው በዚህ ረገድ የሞት ፍርድ ፤ እርስወፐ አቋም ምንድነው

ፕሬዝዳንት ሙላቱ፡- የሞት ፍርድን ይቅርታ በተመለከተ በቀጥታ ለኔ ሳይሆን የሚቀርበው የራሴ የሆነ አካሄድ አለው፡፡ በፍትህ ሚኒስትሩ ሰብሳቢነት የሚመራ የይቅርታ ቦርድ አለ፡፡ ለዚህ ስርዓት ውጪ በፍ/ቤቱ የተያዘን ጉዳይ እነደዚህ አድርጉ ልል አልችልም፡፡ ይሄ የፍትህ ስርዓቱን ያዛባዋል ብዬ ነው  የማምነው፤ የሞት ፍርድን በተመለከተ የግሌ አቋም ምንድነው የሞት ፍርድ የተፈረደበትሰ ሰው ታርመሞ ተፀፅቶ ወደ ህብረተሰቡ ተመልሶ ሰላማዊ ሰው ሊሆን የሚችል ከሆነ በሕጉ መሰረት የሞት ፍርድ ይቀለልለት የሚል ጥያቄ በይቅርታ ቦርዱ በኩል ታይቶ ከመጣ እቀበላለሁ፡፡ እደግፋለሁ፡፡ እንደሚታወቀው ደግሞ የሞት ፍርድ በኢትዮጵያ ሕግ ውስጥ በግልጽ አለ፡፡ ይህንን የሚቃሙ የፀረ-ሞት ፍርድ ተቃዋሚዎችም በውጪ ሀገር እንዳሉ ይታወቃል፡፡ የአውሮፓ ሕብረት አባል ሀገር ለመሆን እንደ አንድ መስፈርት ከሚጠየቀው ውስጥ የሞት ፍርድ በሕጓ የሌለ ሀገር መሆን ነው፡፡ በኛ ሀገር ግን በሕግ ላይ ሰፍሯል፡፡ ስለዚህ አንድ ሰው በግል አቋሙ የሚያስፈጽም ወይም የሚተወው አይደለም፡፡ ከግለሰብ አቋም ጋር ብዙ የሚያያዝ አይመስለኝም፡፡ እኔ ባለሁበት የኃላፊነት ቦታ ላይ ሆኜ የሞት ፍርድ ይቅር ወይም ይኑር ማለቴ ጠቃሚ አይመስለኝም፡፡ ጠቃሚ የሚሆነው ሕብረተሰቡ ተወያይቶበት አንድ አቋም ላይ ቢደርስ ነው፡፡ ይህም በፓርላማው በኩል ሊገለጽ ይችላል፡፡

ቁም ነገር፡- እንደ አጋጣሚ ይሁን ወይም ሆን ተብሎ ከእርስዎ በፊት የነበሩት ሁለቱም ፕሬዝዳንቶች የኦሮሞ ተወላጅ ናቸው፡፡ እርስዎም የኦሮሞ ብሔር ተወላጅ ነዎት ከዚህ አንፃር ቦታው ለኦሮሞ ብቻ የተተወ ነው የሚሉ ሰዎች አሉና በዚህ ላይ የእርስዎ አስተያየት ምንድነው፡፡

ፕሬዝዳንት ሙላቱ፡- እንግዲህ ጉዳዩ በአጋጣሚ የሆነ ነው ወይስ የፓርላማው የጋራ መግባባት ውጤት ነው የሚለውን ለመመለስ ያስቸግረኛል፡፡ ያው ፕሬዝዳንት እጩ አድርጎ የሚያቀርበው ፓርላማው ነው፡፡ ፓርላማው ደግሞ የኦሮሞ ብቻ ነው የተከለለ ወደሚል የሚወስድ አይመስለኝም፡፡ በዚህ መልኩ የተፃፈ ሕግ መኖሩንም አላውቅም፡፡ ማንም ኢትዮጵያዊ ዜጋ ሊሳተፍበት ሊያገኘው የሚችለው ቦታ አድርጌ ነው የምወስደው፡፡ የረሀረነረነረ ጥያቄ ከዚህ በፊት ራሴን ጠይቄው አላውቅም ለብሔር ብሔረሰቦች አንድነትና ልማት እስከተጠቀመ ጊዜ ድረስ ማንም ሰው ቢቀመጥበት ችግር ያለው አይመስለኝም፡፡

ቁም ነገር፡- ውጪ ሀገር ለብዙ ዓመታት ከመኖርዎ አንፃር ምግብ ማብሰል ይችላሉ

ፕሬዝዳንት ሙላቱ፡- ተማሪ በነበርኩበት ጊዜ ተማሪዎች የራሳቸውን ባህል የሚያሳዩበት በዓል ስላለ በተለይመ በልደት በዓላት ሲሆን የየሀገራችን ምግብ፣