Biography Catagories

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

ጥሩነሽ ዲባባ ቀነኔ

 

ጥሩነሽ ዲባባ ቀነኔ

የአለም ሻምፒዮና አትሌት የንግድ ባለሙያ

Tirunesh Dibaba Biography“ስኬታማ አትሌት ለመሆን ጥንካሬ፣ ዲሲፕሊን እና የማሸነፍ ጥልቅ ፍላጎት መላበስን ይጠይቃል፡፡”

ሩጫ ነፍሴ ነው፡፡ በሕይወቴም ደስታ ይሰጠኛል፡፡ እንደ ሥራ ሳይሆን እንደ መዝናኛ ነው የምቆጥረው፡፡ ሩጫ በቃኝ ከአሁን በኋላ አልሮጥም እላለሁ ብዬ ከቶውንም ላስብ አልችልም፡፡ አሸንፌ የወርቅሰ ሜዳሊያዎችን ማጥለቅና በብርታት የሚሞላኝን የኢትዮጵያ ሕዝብ ማስደሰት ታላቅ እርካታ ያጎናጽፈኛል፡፡

የተወለድኩት አርሲ በቆጂ ከተማ በ1977 ዓ.ም ሲሆን አንድ ወንድና ሰባት ሴት ልጆችን ላፈሩት ወላጆቼ ሶስተኛ ልጅ ነኝ፡፡ ቤተሰቦቼ ገበሬዎች ነበሩ፣ ከት/ቤት መልስ በሥራ እያገዝኳት ነው ያደግሁት፡፡ ሩጫ የጀመርኩት በአንደኛ ደረጃ ትምህርት ክፍለ ጊዜ ነው፡፡ መምህር ስንታየሁ የምንላቸው አሰልጣኛችን በጣም ጥሩ ተወዳዳሪ እንደምሆን ዘወትር ይነግሩኝ ነበር፡፡ ስለ አትሌቲክስ በሚያውቅና ሩጫን በሚያበረታታ ቤተሰብ ውስጥ በመወለዴ እድለኛ ነኝ፡፡ በእኛ አከባቢ የሚኖሩ በርካታ ልጃገረዶች ሩጫ ለመለማመድና ለመወዳደር ቀርቶ ትምህርት ቤት ለመሄድም አይፈቀድላቸውም ነበር፡፡ እኛ ቤት ግን ከእኔ በፊት አትሌት የሆኑ የቤተሰብ አባላት ስለነበሩ ተቃውሞ አልገጠመኝም፡፡ በተለይ እናቴ ከሩጫ ስመለስ በቤት ውስጥ ሥራ ብዙ እንዳልጠመድ ከማድረጓም በላይ በብዙ መንገዶች ትደግፈኝ ነበር፡፡

አክስቴ ደራርቱ ቱሉና እህቴ እጅጋየሁ ዲባባ አርአያዎች ናቸው፡፡ አክስቴ የኦሎምፒክ የወርቅ ሜዳሊያ ለአፍሪካና ለኢትዮጵያ ያስገኘት የመጀመሪያዋ ሴት አትሌት ናት፡፡ ስኬቷና ጥንካሬዋ አነቃቅቶኛል፡፡ እንደሷ ምርጥ አትሌት ለመሆን ጥልቅ ፍላጎት ነበረኝ፡፡ እህቴ ደግሞ በቤተሰባችን ውስጥ ሩጫ በመጀመር ፈርቀዳጅ ናት፡፡ አባቴ መጀመር አከባቢ በሩጫው ደስተኛ አልነበረምና እርሷ አዲስ አበባ መጥታ አትሌት ለመሆን በግሏ ብዙ ጥረት ማድረግ ነበረባት፡፡ የእህቴ ብርታት ለእኔ መነቃቂያ ሆኖኛል፡፡ ማለት እችላለለሁ፡፡ እንዲያም ሆኖ ግን እንዲህ በርካታ የወርቅ ሜዳልያዎችን እስከ ማግኘት አደርሳለሁ፡፡ ብዬ አስቤ አላውቅም፡፡ አንዳንዴ እነዚህን ሁሉ የወርቅ ሜዳሊያዎች ለማግኘት የቻልኩት እንዴት ነው፡፡ በማለት ያለፍኩትን መንገድ ዞር ብዬ እያየሁ ራሴን እጠይቃለሁ፡፡ እናም በራሴ እገረማለሁ፡፡

የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርቴን ከጨረስኩ በኋላ ሰባተኛ ስምንተኛን ክፍል ለመማር እህቶቼ እጅጋየሁና በቀሉ ዘንድ ወደ አዲስ አበባ መጣሁ፡፡ ክፋቱ ግን የትምህርት ቤት ምዝገሰባ ስድስት ቀን አልፎት ነበር፡፡ በሁኔታው ክፉኛ ባዝንም ተመልሼ ላለመሄድ ቆርጬ ነበርና እግሬን ወደ በቆጂ አላነሳሁም፡፡ እዚያ እንዳሉት እኩዮቼ በለጋ እድሜዬ ትዳር ውስጥ መግባትን አልፈልግሁም፡፡ ቀጣዩ ጉዞዬ በስፖርት የምታቀፍበትን ክለብ ማፈሰላለግ ሆነ፡፡ እናም እህቴ በቀሉ በረዥም ርቀት ውድድር ጥሩ ውጤት ማምጣት የጀመረችበትን የማረሚያ ቤቶች ስፖርት ክለብ ተቀላቀልኩ፡፡ በፖሊስ ክለብ አባልነቴ ኢትዮጵያን በመወከል የመጀመሪያዬን ዓለም አቀፍ ውድድር ያደረግሁት በቤልጂዬም ነበር፡፡ በ15 ዓመት ዕድሜዬ በባዶ እግሬ ሮጬ በአገር አቋራጭ ውድድር 5ኛ ወጣሁ፡፡ በባዶ እግሬ የሮጥኩበት ግን ጫማ ሳይኖረኝ ቀርቶ ሳይሆን ለውድድሩ የተሻለ ይሆናል ብዬ በማሰብ ነበር፡፡

የኦሎምፒክ ይሁን የዓለም አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ወይም ሌላ ማንኛውም ውድድር ማሸነፍ በእጅጉ ያስደስተኛል፡፡ በ19 ዓመቴ በፓሪስ በተካሄደው ዘጠነኛው የIAAF የዓለም ሻምፒዮን ውድድር፣ በ5ሺ ሜትር ተወዳድሬ የወርቅ ሜዳልያ ማሸነፌ በእጅጉ ነበር ያስደሰተኝ፡፡ ይህ ድል የወደፊት ተስፋዬን ከወዲሁ እንድመለከትና በራሴ ላይ እምነት እንዲያድርብኝ አድርጎኛል፡፡ ይሄንን ሜዳልያ አሸንፋለሁ ብዬ አልጠበቅሁም ነበር፡፡ ከእኔ የላቀ ብዙ ልምድ ያላቸው በርካታ አትሌቶች በውድድር ላይ ተሳትፈው ስለነበር ማንም ታሸንፋለች ብሎ የጠበቀ አይመስለኝም፡፡ በዚያ ላይ ደግሞ ከሁሉ አትሌቶች በዕድሜ ትንሷ እኔ ነበርኩ፡፡ ውድድሩን ማሸነፌና የኢትዮጵያ ሕዝብ የሰጠኝ ድጋፍ የበለጠ መስራት እችላለሁ ብዬ እንዳምን አደረገኝ፡

ሁሌም ከእኔ የላቀ ልምድ ካላቸው አትሌቶች ጋር ስለምሆን፣ ለውድድር ለመላው ዓለም መጓዝ ለእኔ አስቸጋሪ አልነበረም፡፡ እንዲያም ሆኖ ለመጀመሪያ ጊዜ ኒውዮርክ ስሄድ፣ ከተማዋን አይቼ ማመን አቃተኝ፡፡ ትንግርት ሆነብኝ ብል ይቀላል፡፡ በመደነቅ ስሜት እጅጉን ተጥለቅልቄ ነበር፡፡ ያ ልዩ ስሜት አሁን ድረስ የምዘነጋው አይደለም፡፡

ትልቅ ፈተኛ የገጠ ወስመኝ በ2ሺ የቤጂንግ ኦሎምፒክ፣ ድርብ የወርቅ ሜልዳልያ ካሸነፍኩ በኋላ ነው፡፡ ይሄንን ድሌን ተከትሎ ለአራት ወይም አምስት ወራት እረፍት ወስጄ ነበር፡፡ ዳግም ሩጫ ለመጀመር ስሞክር ታዲያ ክብደት ጨምሬአለሁ፡፡ እግሬም አብጧል መሮጥ አቃተኝ፡፡ ቀጣዮቼን ሶስት ዓመታት ያሳለፍኩት፣ አብዛኛው ከውድድር ርቄ ህክምና በመከታተል ብቻ ነበር፡፡ ያኔ ሩጫ በጣም ናፍቆኝ እንደነበር ትዝ ይለኛል፡፡ በዘዴ ልምምድ እንዳደርግና  ከሶስት ዓመት እረፍት በኋላ ወደ ውድድር ለመመለስ እንድችል ያገዘኝ በሕዳር 2000 ዓ.ም ያገባሁት ባለቤቴ ስለሺህ ሰህን ነበር፡፡ ባለቤቴ በዚያ አስቸጋሪ ወቅት ላደረገልኝ ድጋፍ ራሴን ልጆችን ፍ ምስጋናዬ ከፍ ያለ ነው፡፡

ስኬታማ አትሌት ለመሆን ጥንካሬ፣ ዲሲፕሊን እና የማሸነፍ ጥልቅ ፍላጎት መላበስን ይጠይቃል፡፡ በቀን ሁለቴ ልምምድ አደርጋለሁ፡፡ ጠዋት ከአንድ ሰዓት በላይ ምሽት ከግሞ ከ40-50 ደቂቃ፡፡ ለዛሬ ስኬቴ የራሴ ጥንካሬ ከፍተኛ ሚና አለው፡፡ የቤተሰቤ ድጋፍም ለስኬታማነቴ የማይናቅ አስተዋጽኦ አበርክቷል፡፡ በእኔ ውጤታማነት በማመኑና ተወዳድሬ እንዳሸንፍለት ሞራሌን በመገንባቱ የኢትዮጵያን ሕዝብ ከልብ አመሰግናለሁ፡፡

ሰዎች በአትሌትነቴ እንዲያስታውሱኝና እንዲኮሩብኝ እሻለሁ፡፡ በአትሌትነቴ ብቻ ግን አይደለም፡፡ ከዛም ውጭ ባስመዘገብኳቸው ስኬቶች መታወስ እፈልጋለሁ፡፡ በአትሌቲክስ የሰበሰብኩትን ገንዘብ በቅርብ ጊዜ ወዲህ በንግድ ሥራ ላይ ማዋል ጀምሪያለሁ፡፡ በአዲስ አበባ መገናኛ አከባቢ በቅርቡ ሥራ የሚጀምር ባለ 11 ፎቅ ሕንፃ ገንብቻለሁ፡፡ ቦሌ ላይ ባለ 5 ኮከብ ሆቴል እያስገነባሁ ሲሆን በለገጣፎም የመዝናኛ ስፍራ ግንባታ እያካሄድን እንገኛለን፡፡ በተሰማራሁባቸው የንግድ መስኮች ለበርካታ ሰዎች የሥራ ዕድል እንደምፈጥር ተስፋ አለኝ፡፡ ሴቶችን፣ ሕፃናትንና አዛውንቶችን ተጠቃሚ በሚያደርጉ ሥራዎች ላይ በስፋት መንቀሳቀስ እፈልጋለሁ፡፡ የራሴን ልጆችን ወልጄ መሳም እሻለሁ፡፡

ኢትዮጵያ የበለጠ እንትበለግጽና የሕዝቦቿን ፍላጎት ማሟላደት የምትችል አገር እንድትሆን እመኛለሁ፡፡ ቀጣዩ ትውልድ በሁሉም የሕይወት ዘርፌ የላቀ ደረጃ ላይ መድረስ እንደሚችል አምናለሁ፡፡ ስኬታማነትን ለሚሹ ወጣት ሴቶች የምለግሳቸው ምክር፣ ሥራቸውን በአግባቡ ተግተው እንዲሰሩ ነው፡፡ ተግተው እስኪሰሩ ድረስ የማታ ማታ የሚሹትንማሳካታቸው አይቀርምና ምንም ፈተኛ ቢገጥማቸው ተስፋ መቁረጥ የለባቸውም፡፡ ስራን ለወንዶች ብቻ ወይም ለሴቶች ብቻ ብሎ ማሰብ እንደማይገባ መገንዘብ አስፈላጊ ነው፡፡ ሥራ ወንዶች ወይንም ሴቴች ብሌ አይመርጥም፡፡ አንዳንድ ሥራ ለሴቶች አስቨጋሪ ሊሆን ቢችልም ጠንክራችሁ እስከሰራችሁ ድረስ ምም የማይቻል ነገር የለም፡፡