Job Type:Health Facility / Hospital

 

Fields of Education: በሳይኮሎጂ ወይም በሶሾሎጂ ወይም በካውንስሊንግ ሳይኮሎጂ

 

Organization: የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር

 

Salary : 5583

 

Posted:2016-08-07

 

Application Dead line:2016-08-20

 




የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር
 ከዚህ በታች በተመለከቱት ክፍት የሥራ መደቦች ላይ የተጠቀሱትን መመዘኛዎች የሚያሟሉ አመልካቾችን አወዳድሮ መቅጠር ይፈልጋል፡፡

1. የስራ መደብ መጠሪያ፡ የጤና መረጃ ረዳት አማካሪ

 

የሥራ ደረጃ፡ ፕሣ 4/1

 

መነሻ ደመወዝ፡ 5583.00

 

ብዛት፡ 13

 

ተፈላጊ ችሎታ፡ በሳይኮሎጂ ወይም በሶሾሎጂ ወይም በካውንስሊንግ ሳይኮሎጂ ወይም በቢ.ኤስ.ሲ ነርሲንግ ወይም በሕብረተሰብ ጤና አጠባበቅ ወይም በተመሳሳይ የትምህርት ዘርፍ የተመረቀ/የተመረቀች

 

የስራ ልምድ፡ ለመጀመሪያ ዲግሪ 6 ዓመት የሥራ ልምድ፣ ለማስተርስ ዲግሪ 4 ዓመት የሥራ ልምድ 

ማሳሰቢያ፡-

952 ነጻ የጤና የስልክ ጥሪ ማዕከል ሲሆን ቀደመ ሲል ለበርካታ ዓመታት በኤች.አይ.ቪ፣ በአባላዘር በሽታ እና በቲቪ ላይ ጥራቱና ምስጢራዊነቱ የተጠበቀ የጤና መረጃ አገልግሎት፣ የምክር አገልግሎት እንዲሁም የሪፈራል አገልግሎት ሲሰጥ መቆየቱ ይታወቃል፡፡ በአሁኑ ጊዜ ማዕከሉ በጤና ጥበቃ ሚኒስቴር እንዲሆን ስለተደረገ ከዚህ በፊት ሲሰጣቸው ከነበረው አገልግሎት በተጨማሪ ቅድሚያ በተሰጣቸው የጤና ችግሮች ላይ ለመስራት በዝግጅት ላይ ይገኛል፡፡

ስለሆነም በዚህ የቅጥር ማስታወቂያ ላይ በተጠቀሱት የሥራ መደቦች ተመዝግበው የውድድሩ አሸናፊ የሚሆኑ ባለሙያዎች የሚያከናውኑት ሥራ በስልክ የጤና መረጃ፣ የምክርና የሪፈራል አገልግሎት መስጠት መሆኑን ተገንዝበው በተጠቀሱት የተፈላጊ ችሎታ ተመዝግባችሁ መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እናስታውቃለን፡፡

  1. የቅጥር ሁኔታ ፡ በቋሚነት

  2. ሴት አመልካቾች ይበረታታሉ

  3. የሥራ ቋንቋው፡- አማርኛ፣ ኦሮምኛ፣ አፋርኛ፣ ሲዳምኛ፣ ጉራግኛ፣ ሀድይኛ፣ ከምባትኛ፣ ወላይትኛ፣ ስልጥኛ፣ ሱማልኛ

  4. በተጠቀሱት የሥራ መደቦች ላይ የምትወዳደሩ መመዝገብ የምትችሉት ወቅታዊ የሙያ ምዝገባ ፈቃድ ስታቀርቡ ነው

  5. በጤና ሙያ በዲፕሎማ ከተሰጠ አገልግሎት ውስጥ ከፍተኛው የሚያዘው የአራት ዓመት አገልግሎት ብቻ ነው

  6. በተፈላጊ ችሎታው ከተገለፀው የትምህርትና የሥራ ልምድ በላይ ማስረጃ ያላቸው አመልካቾች መወዳደር ይችላሉ

  7. አመልካቾች ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ጠዋት ከ2፡30-6፡30 ሰዓት በኃላ ከ7፡30-11፡0 ሰዓተ የትምህርትና የሥራ ልምድ ማስረጃዎቻችሁን ዋናውንና የማይመለስ ፎቶ ኮፒ በመያዝ የመጀመሪያ ሕንፃ ሰው ሀብት ልማትና አስ/ዳይሬክቶሬት ቀርባችሁ ማመልከት ትችላላችሁ፡፡ የሚቀርበው የሥራ ልምድ ማስረጃ ወቅታዊ ያልተደለዘ፣ የሥራውን ዓይነት፣ የደመወዝ ልክ፣ ከመቼ እስከ መቼ እንደሰራ ጊዜውን ለይቶ የሚገልጽ የአሰሪውን ሙሉ ስም ፊርማና የሥራ ደረጃን ያካተተ መሆን ይኖርበታል፡፡ ከግል ድርጅት የሚቀርበው ማስረጃ ከፍ ብሎ ከተጠቀሰው በተጨማሪ ተገቢውን የሥራ ግብር ስለመክፈሉ የሚገልጽ መሆን አለበት፡፡ የክልል አመልካቾች በግንባር፣ በወኪል/በፖስታ በፋክስና በሌሎች የኤሌክትሮኒክስ መሳሪያዎች የሥራ መጠየቂያ ቅጽ ሞልተው በመላክ መመዝገብ የሚችሉ ሲሆን የሥራ መጠየቂያ ቅጽ ከሌለ ግን የማስረጃዎቻቸውን ፎቶ ኮፒ ከግል ሁኔታ መግለጫ /CV/ ጋር በማያያዝ በፖስታ ሳጥን ቁጥር 1234 መላክ ይችላሉ፡፡

አድራሻችን፡- በልደታ ክፍለ ከተማ ቀበሌ 07/14 የኢትዮጵያ ጎማ ቁጠባ አጠገብ

ስልክ ቁጥር፡ 0115 159869፣ 0911 159869፣ 0911417852፣ 0911 678454        

 

 

 

Please Click here
to move back to job lists