Job Type:Government Organization

 

Fields of Education: Multiple

 

Organization: የኢትዮጵያ የግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት

 

Salary : multiple

 

Posted:2016-08-16

 

Application Dead line:2016-08-26

 




የኢትዮጵያ የግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት ከዚህ ቀጥሎ በተጠቀሱት የሙያ ዓይነትና የሥራ መደቦች አመልካቾችን አወዳድሮ ለመቅጠር ይፈልጋል፡፡በኢንስቲትዩቱ ለመቀጠር የሚፈልጉ ብቃት ያላቸው ባለሙያዎች ማመልከት ይችላሉ፡፡

1  የሥራ መደቡ መጠሪያ ተመራማሪ   (ለግብርና መካናይዜሽን ምርምር ዳይሬክቶሬት)፣

   ተፈላጊ ችሎታ:- ኤም.ኤስ.ሲ ዲግሪ በAgricultural Engineering ወይም በMachinery Engineering ወይም በSustainable   Energy Engineering፣


2. የሥራ መደቡ መጠሪያ   ጀማሪ ተመራማሪ

 ተፈላጊ ችሎታ:- በAgricultural engineering, ወይም በMechanization engineering ወይም mechanical Engineering ወይም በBio-resources engineering, ወይም በBio-system engineering በmanufacturing engineering ቢ.ኤስ.ሲ   ዲግሪና 0 ዓመት የሥራ ልምድ  


3. የሥራ መደቡ መጠሪያ   ተመራማሪ  (ለአየር ጠባይና ጂኦስፓሻል ምርምር ዳይሬክቶሬት)፣

   ተፈላጊ ችሎታ:-ኤም.ኤስ.ሲ ዲግሪ በMeteorology ወይም በ Agro-meteorology ወይም Atmospheric Science፣ ወይምበ GIS & Remote Sensing ፣


4. የሥራ መደቡ መጠሪያ    ጀማሪ ተመራማሪ  ለ (አየር ጠባይና ጂኦስፓሻል ምርምር ዳይሬክቶሬት)፣

   ተፈላጊ ችሎታ:-ቢኤስ.ሲ ዲግሪ በMeteorology እና 0 ዓመት ልምድ፣



5. የሥራ መደቡ መጠሪያ  ተመራማሪ  (ለግብርናና ሥነ-ምግብ ላቦራቶሪዎች ዳይሬክቶሬት)፣

   ተፈላጊ ችሎታ:-ኤም.ኤስ.ሲ ዲግሪ በምግብ ሣይንስ ወይም ወይም ስነ-ምግብ ወይም በምግብ ቴክኖሎጂ ወይም በአፕላይድ ማይክሮባዮሎጂ ወይም በሞሊኩላር ባዮሎጂ ወይም በአናላይቲካል ኬሚስትሪ የሙያ መስክ፣ በኬሚስትሪ ወይም በቫይሮሎጂ ወይም  በማይኮሎጂ እና በተመሳሳይ የሙያ መስኮች፣


6. የሥራ መደቡ መጠሪያ   ተመራማሪ  (ለግብርናና ሥነ-ምግብ ላቦራቶሪዎች ዳይሬክቶሬት)፣

   ተፈላጊ ችሎታ:-ቢ.ኤስ.ሲ ዲግሪ በባዮሜዲካል ኢንጂነሪንግ ተመርቆ/ቃ ቢያንስ 2 ዓመት እና በላይ አግባብ   የሆነ የሥራ ልምድ ያለው/ያላት፣ወይም በምግብ ሣይንስ ወይም በምግብ ቴክኖሎጂ ተመርቆ/ቃ ቢያንስ 2 ዓመት እና በላይ አግባብ የሆነ የሥራ ልምድ ያለው/ያላት፣ ወይም በባዮሎጂ የትምህርት ዘርፍ ቢ.ኤስ.ሲ ዲግሪና በሞሉክላርና መሰል   ላቦራቶሪዎች ላይ ቢያንሰ 2 እና በላይ ዓመት የሠራ/ች ወይም በኬሚስትሪ የትምህርት ዘርፍ ቢ.ኤስ.ሲ ዲግሪና በኬሚካል ትንተና (InstrumentalAnalysis)ቢያንስ ለ2 ዓመት እና በላይ የሠራ/ች፣


7. የሥራ መደቡ መጠሪያ   የክምችትና ክፍፍል ሠራተኛ  (በድጋሚ የወጣ)፣

   ተፈላጊ ችሎታ:-በቀድሞ ሥርዓተ-ትምህርት 12ኛ ወይም በአዲሱ ሥርዓተ-ትምህርት 10ኛ ክፍል ትምህርት የፈጸመ/ችና  8 ዓመት   አግባብ የሆነ የሥራ ልምድ ፣ወይም ዲፕሎማ ( 10+3) እና 2 ዓመት የሥራ ልምድ፣ 

    ደረጃ:- ጽሂ-8

   ደመወዝ :-1743.00

   ብዛት:-2 (ሁለት)

   የምዝገባና የሥራ ቦታ     በኢንስቲትዩቱ  ዋና መሥሪያ ቤት አዲስ አበባ፣


8. የሥራ መደቡ መጠሪያ   አካውንታንት (በኮንትራት)

   ተፈላጊ ችሎታ:-በአካውንቲንግ ቢኤ.ዲግሪ እና ቢያንስ 2 ዓመት አግባብ የሆነ የሥራ ልምድ ያለው/ ያላት፣የኤክሴልና የፒችትሪ አካውንቲንግ በቂ ዕውቀት ኖሮት/ኖሯት፣ፕሮግራሙን በመጠቀም  መሥራት የሚችል/የምትችል፣ 

   ደመወዝ:-7‚000.00 (ሰባት ሺህ ብር)

   የምዝገባና የሥራ ቦታ   በኢንስቲትዩቱ  ዋና መሥሪያ ቤት አዲስ አበባ፣


9. የሥራ መደቡ መጠሪያ   የሪኮርድና ማኅደር ሠራተኛ V

   ተፈላጊ ችሎታ:-በቀድሞ ሥርዓተትምህርት 12ኛ ከፍል ወይም አዲሱ ሥርዓተ-ትምህርት 10ኛ ክፍል የፈጸም/ችና 8 ዓመት ልምድ ያለው/ያላት፣ወይም በሰው ሀብት ማኔጅመንት ወይም በማኔጅመንት 10+3 ወይም ደረጃ III   እና 2   ዓመት ልምድ ያለው ያላት፣

   ደረጃ:-ጽሂ-8

   ደመወዝ:-1743.00

  የምዝገባና የሥራ ቦታ:-ፎገራ ብሄራዊ ሩዝ  ምርምርና ስልጠና ማዕከል ( ወረታ)


10. የሥራ መደቡ መጠሪያ:- መካከለኛ የሂሳብ ምዝገባ አካውንታንት II

     ተፈላጊ ችሎታ:-በአካውንቲንግ ወይም በቢዝነስ ማኔጅመንት ቢኤ.ዲግሪ እና 6 ዓመት አግባብ የሆነ የሥራ ልምድ ያለው/ያላት፣

     ደረጃ :- ፕሣ-5

    ደመወዝ:- 3425.00

   የምዝገባና የሥራ ቦታ:-ጭሮ ብሄራዊ ማሽላ ምርምርና ስልጠና ማዕከል ( ጭሮ)


11. የሥራ መደቡ መጠሪያ የውስጥ  ኦዲት ሠራተኛ

    ተፈላጊ ችሎታ:-በአካውንቲንግ ወይም በተመሳሳይ የሙያ መስክ 10+1 ወይም ደረጃ I እና10 ዓመት የሥራ ልምድ 

    ደረጃ:- መፕ-9

    ደመወዝ:--2298.00

 የምዝገባና የሥራ ቦታ:-ጭሮ ብሄራዊ ማሽላ ምርምርና ስልጠና ማዕከል ( ጭሮ)


12. የሥራ መደቡ መጠሪያ      ገንዘብ ያዥ፣ክምችትና ክፍፍል ኦፊሰር

    ተፈላጊ ችሎታ:-በአካውንቲነግ፣ ወይም በግዥና አቅርቦት፣ወይም በማርኬቲንግ ወይም በቢዝነስ ማኔጅመንት 10+1 እና 10 ዓመት አግባብ የሆነ የሥራ ልምድ ያለው/ያላት፣ወይም 10+3 ወይም ደረጃ -III እና 6 ዓመት ልምድ፣ 

    ደረጃ:-አስ-4

    ደመወዝ:-2298.00

 የምዝገባና የሥራ ቦታ:- ጭሮ ብሄራዊ ማሽላ ምርምርና ስልጠና ማዕከል ( ጭሮ)


13. የሥራ መደቡ መጠሪያ      ሾፌር መካኒክ II

    ተፈላጊ ችሎታ:-የ4ኛ ክፍል የፈጸመና የ4ኛ ደረጃ መንጃ ፈቃድ ወይም በአዲሱ መነጃ ፈቃድ ተመጣጣኝ ደረጃ እና የመካኒክነት ችሎታ የምስክር ወረቀት እና 4 ዓመት የሥራ ልምድ ያለው/ያላት፣ 

    ደረጃ:- እጥ-9

    ደመወዝ:-2008.00

  የምዝገባና የሥራ ቦታ:-ጭሮ ብሄራዊ ማሽላ ምርምርና ስልጠና ማዕከል ( ጭሮ)


14. የሥራ መደቡ መጠሪያ      ሾፌር መካኒክ I

    ተፈላጊ ችሎታ:-የ4ኛ ክፍል ትምህርት የፈጸመና የ3ኛ ደረጃ መንጃ ፈቃድ ወይም በአዲሱ መንጃ ፈቃድ ተመጣጣኝ ደረጃ እና የመካኒክነት ችሎታ ማስረጃ ያለውና 4 ዓመት የሥራ ልምድ ያለው/ላት 

    ደረጃ:- እጥ-8

    ደመወዝ:-1743.00

    የምዝገባና የሥራ ቦታ:-ጭሮ ብሄራዊ ማሽላ ምርምርና ስልጠና ማዕከል ( ጭሮ)


15. የሥራ መደቡ መጠሪያ ጀማሪ  የሰው ሀብት ሥራ አመራርና ልማት ባለሙያ I

    ተፈላጊ ችሎታ:- በሰው ሀብት ሥራ አመራር፣ ወይም በማኔጅመንት ወይም በቢዝነስ ማኔጅመንት ወይም በሕዝብ አስተዳደር  ቢ.ኤ.ዲግሪ እና 0 ዓመት ልምድ፣

   ደረጃ:-ፕሣ-1

    ደመወዝ:-2008.00

    የምዝገባና የሥራ ቦታ:-ፓዌ ግብርና ምርምር ማዕከል፤


16. የሥራ መደቡ መጠሪያ:- ጀማሪ የሂሳብ ምዝገባ አካውንታንት  

    ተፈላጊ ችሎታ:-በአካውንቲንግ ወይም በቢዝነስ ማኔጅመንት ቢ.ኤ.ዲግሪ እና 0 ዓመት ልምድ፤

    ደረጃ:- ፕሣ-1

    ደመወዝ:-2008.00

    የምዝገባና የሥራ ቦታ:-ፓዌ ግብርና ምርምር ማዕከል፤

 

ማሳሰቢያ ለተመዝጋቢዎች፡-

1. የምዝገባ ጊዜ ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ8 (ስምንት) ተከታታይ የሥራ ቀናት ነው፡፡

2. የምዝገባው ቦታ ከተራ ቁጥር 1-8 ለተጠቀሱት የሥራ መደቦች በኢንስቲትዩቱ ዋና መሥሪያ ቤት የሰው ሀብትሥራ አመራር ቢሮ ነው፡፡

3. በተራ ቁጥር 9 ለተጠቀሰው የሥራ መደብ በፎገራ ብሄራዊ ሩዝ ምርምርና ሥልጠና ማዕከል (ወረታ) የሰው ሀብትሥራ አመራር ቢሮ ነው፡፡ ከተ. ቁጥር 10-14 ለተጠቀሱት የሥራ መደቦች  በጭሮ ብሄራዊ ማሽላ ምርምርና ሥልጠና ማዕከል(ጭሮ) የሰው ሀብትሥራ አመራር ቢሮ  ነው፡፡ ከተ. ቁጥር 15-16 ለተጠቀሱት የሥራ መደቦች  በፓዌ ግብርና ምርምር ማዕከል (ፓዌ) የሰው ሀብትሥራ አመራር ቢሮ  ነው፡፡

4. የተመራማሪዎች የሥራ ቦታ  በኢንስቲትዩቱ ሥር ባሉ የፌዴራል ግብርና ምርምር ማዕከላት ሲሆን፣ ብዛቱ በሂደት የሚወሰን ነው፡፡

5. ለተመራማሪነት የሚወዳደሩ የመጀመሪያ ዲግሪ የመመረቂያ ነጥብ (CGPA) ለወንድ 3.00 እና በላይ ለሴት ተወዳዳሪ 2.75 እና   በላይ፣ በኤም.ኤስ. ሲ ዲግሪ ለሚያመለክቱ በተመሳሳይ  የመጀመሪያ ዲግሪ የመመረቂያ ነጥባቸው በተመሳሳይ ለወንድ 3.00 እና በላይ ለሴት ተወዳዳሪ 2.75 እና  ማስረጃዎቹ ተሟልተው ተያይዘው መቅረብ አለባቸው፣ለተመራማሪነት ተመዝጋቢዎች መመዝገብ የሚችሉት በአንድ የሥራ መደብ ላይ ብቻ ነው፡፡

6. ከተመራማሪ የሥራ መደቦች ውጪ ለሚወዳደሩ ተመዝጋቢዎች ከዝቅተኛው የተፈላጊ ችሎታ በላይ የትምህርትና አግባብ የሆነ የሥራ ልምድ ያላቸው ሊያመለክቱ ይችላሉ፡፡ 

7. ተመዝጋቢዎች ማሟላት ያለባቸው፤ ለሚወዳደሩበት የሥራ መደብ ማመልከቻ ፣ ካሪኩለም ቪቴ(CV)፣ የተሟላ የትምህርትና የሥራ ልምድ ማስረጃ ከማይመለስ ፎቶ ኮፒ ጋር ተያይዞ መቅረብ አለበት፣በቂ የስልክ ወይም አማራጭ አድራሻ የስልክ ቁጥሮች በማመልከቻቸው ላይ መግለጽ ይኖርባቸዋል፣በደረጃ  በ(Level) ለተፈጸመ የትምህርት ማስረጃ የብቃት ማረጋገጫ ማስረጃ /COC)  መቅረብ አለበት፡፡

8. የኮምፒዩተር ችሎታ በሚጠይቁ የሥራ መደቦች ላይ የኮምፒዩተር መሠረታዊ ዕውቀት የግድ ያስፈልጋል፡፡

9. በደረጃ  በ(Level) ለተፈጸመ የትምህርት ማስረጃ የብቃት ማረጋገጫ ማስረጃ /COC)  መቅረብ አለበት ፡፡

10. የሚቀርቡት የሥራ ልምድ ማስረጃዎች ከሚወዳደሩበት የሥራ መደብ ጋር አግባብ ያለው ሆኖ የደመወዝ መጠኑ የተገለጸና የሥራ  ግብር የተከፈለበት መሆን አለበት፡፡

11. ለመወዳደር የሚፈልጉ ተወዳዳሪዎች በተጠቀሰው ጊዜና  ቦታ በግንባር እየቀረቡ ወይም በወኪል ወይም በፖስታ ልከው መመዝገብ ይችላሉ፡፡

12. ሴት ተወዳዳሪዎች እንዲያመለክቱ ይበረታታሉ፡፡

13. ለበለጠ መረጃ ድረ-ገጽ www.eiar.gov.et. መመልከት ይቻላል፡፡

14. በስ.ቁጥር ፣ለጭሮ ብሄራዊ ማሽላ ምርምር ማዕከል (0255) 51-15-07 ፖ.ሣ.ቁ 190 (ጭሮ)፣ፎገራ ብሄራዊ ሩዝ ምርምር ማዕከል 0584-46-07-02፣  ፖ.ሣ.ቁ.1937 (ባህርዳር)፣እና 058-119-00-84 (ፓዌ) ወይም በኢንስቲትዩቱ የፖስታ ሣጥን ቁጥር 2003 (አዲስ አበባ)  በመላክ መመዝገብ  ይችላሉ፤ ወይም በዋናው መሥሪያ ቤት ስልክ ቁጥር 0116-46-01-74/0116-45-44-41 መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡

15. የመምረጫ ፈተና የሚሰጥበት ጊዜና ቦታ በተመዘገቡበት ቦታ በውስጥ ማስታወቂያ የሚገለጽ ይሆናል፡፡

 

 

 

Please Click here
to move back to job lists