Job Type:Government

 

Fields of Education: በላይብረሪ ሳይንስ ወይም በኢንፎርሜሽን ማኔጅመንት ሲስተም የኮሌጅ ዲፕ??

 

Organization: የኢትዮጲያ የግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት

 

Salary : 3425

 

Posted:2016-02-01

 

Application Dead line:2016-02-05

 

 

 

የሥራ መደቡ መጠሪያ          የቤተ-መጽሃፍት ኃላፊ (ለግብርና ባዮቴክኖሎጂ ምርምር ማዕከል-ሆለታ)

 

ተፈላጊ ችሎታ                   በላይብረሪ ሳይንስ ወይም በኢንፎርሜሽን ማኔጅመንት ሲስተም የኮሌጅ ዲፕሎማና 9 ዓመት                                       አግባብ ያለው የሥራ ልምድ ያለው/ያላት፣

 

ደረጃ                            መፕ-12

 

ደመወዝ                       3425

 

ማሳሰቢያ ለተዝጋቢዎች፡-

  1. የምዝገባ ጊዜ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ8(ስምንት) ተከታታይ የሥራ ቀናት ነው፡፡

  2. የምዝገባው ቦታ ከተራ ቁጥር 01 እስከ 18 ለተጠቀሱት የሥራ መደቦች በብሔራዊ የግብርና ባዮቴክኖሎጂ ምርምር ማዕከል (ሆለታ) እና በኢንስቲትዩቱ ዋና መሥሪያ ቤት፣ ከተራ ቁጥር 38 እስከ 39 ለተጠቀሱት የሥራ መደቦች በፎገራ ብሔራዊ ሩዝ ምርምርና ስልጠና ማዕከል (ወረታ) እና በኢንስቲትዩቱ ዋና መሥሪያ ቤት የሰው ሀብት ሥራ አመራርና ልማት ቢሮ ነው፣

  3. ለተመራማሪነት የሚወዳደሩ የመጀመሪያ ዲግሪ የመመረቂያ ነጥባቸው (CGPA) ለወንድ 3.00 እና በላይ ለሴት ተወዳዳሪ 2.75 መሆን አለበት፣

  4. ከተመራማሪ የሥራ መደቦች ውጪ ላሉ የሥራ መደቦች የዲግሪ ወይም የዲፕሎማ የመመረቂያ ነጥብ (CGPA) የግድ አስፈላጊ አይደለም፡፡

  5. ተመዝጋቢዎች ከዝቅተኛ የተፈላጊ ችሎታ በላይ የትምህርትና አግባብ የሆነ የሥራ ልምድ ያላቸው ሊያመለክቱ ይችላሉ፡፡

  6. ተነዝጋቢዎች ማሟላት ያለባቸው፣ ለሚወዳደሩበት የሥራ መደብ ማመልከቻ፣ ካሪኩለም ቪቴ (CV)፣ የተሟላ የትምህርትና የሥራ ልምድ ማስረጃ ለማይመለስ ፎቶ ኮፒ ጋር ተያይዞ መቅረብ አለበት፣ በቂ የስልክ ቁጥር ወይም አማራጭ የስልክ ቁጥሮች በማመልከቻው ላይ መግለጽ ይኖርባቸዋል፡፡

  7. ለሁሉም የሥራ መደቦች የኮምፒውተር መሰረታዊ ዕውቀት አሰስፈላጊ ነው፡፡

  8. በደረጃ (LEVEL) ለተፈጸመ የትምህርት ማስረጃ የብቃት ማረጋገጫ ማስረጃ (COC) ማስረጃ መቅረብ አለበት፡፡

  9. የሚቀርቡት የሥራ ልምድ ማስረጃዎች ከሚወዳደሩበት የሥራ መደብ ጋር አግባብ ያለው ሆኖ የደመወዝ መጠኑ የተገለጸና የስራ ግብር የተከፈለበት መሆን አለበት፡፡

ሴት ተወዳዳሪዎች እንዲያመለክቱ ይበረታታሉ፡፡

ለበለጠ መረጃ የኢንስቲትዩቱ ድረ-ገጽ www.eiar.gov.et መመልከት ይችላሉ፡፡

በስልክ ቁጥር፡- ለብሔራዊ ግብርና ባዮቴክኖሎጂ ምርምር ማዕከል 0112-37-09-09

በፖስታ ሳጥን ቁጥር 31 (ሆለታ) ለፎገራ 05 84 46 07 09 ወይም በኢንስቲትዩቱ የፖስታ ሳጥን ቁጥር 2003 (አዲስ    አበባ) በመላክ መመዝገብ ይችላሉ፡፡ እንዲሁም በዋናው መሥሪያ ቤት ስልክ ቁጥር 0116 46 07 74 ወይም 0116 45 44 41 ደውሎ መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡

የመምረጫ ፈተና የሚሰጥበት ጊዜና ቦታ በተመዘገቡበት ቦታ በውስጥ ማስታወቂያ የሚገለጽ ይሆናል፡፡

 

 

 

Please Click here
to move back to job lists