Quick Links

 

 

 

 

የኢትዮጵያ መድን ድርጅት በዓመቱ ውስጥ ግማሽ ቢሊየን ብር ማትረፉን ገለፀ

 

 

Insurance

አዲስ አበባ ፣ ነሃሴ 28፣ 2008 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ መድን ድርጅት በተጠናቀቀው በጀት አመት የ2 ነጥብ 3 ቢሊየን ብር የአርቦን ገቢ አስመዝግቤለው አለ።ድርጅቱ ለኤፍ ቢ ሲ በላከው መረጃው ከታክስ በፊት አጠቃላይ ትርፉም 522 ነጥብ 3 ሚሊየን ብር ደርሷል ።

በእንጥልጥል የቆዩና በህይወትና በንብረት ላይ ለደረሰ ጉዳት እንዲሁም ከ3ኛ ወገን ለቀረበ ጥያቄ ድርጅቱ የ1 ቢሊየን ብር የካሳ ክፍያ ፈጽሟል። ከተከፈለው የካሳ ክፍያ ውስጥም 95 በመቶው በጠቅላላ መድን የተከፈለ ሲሆን፥ ከእዚህ ውስጥም 71 በመቶ የሚሆነው ለተሽከርካሪ ጉዳት የተከፈለ ነው።

 

ድርጅቱ በበጀት አመቱ ከኢንቨስትመንት ስራዎች የ190 ሚሊየን ብር ገቢ ማግኘቱንም ጠቁሟል። የኢትዮጵያ መድን ድርጅት አሰራሩን ዘመናዊ ለማድረግና የደንበኞቹን እርካታ ለመጨመር አዲስ የአደረጃጀት ጥናት በአለም አቀፍ አማካሪዎች አስጠንቶ ማጠናቀቁንም በመግለጫው ገልጿል።

 

Source: http://www.fanabc.com/