የጨጓራ በሽታ አለብዎ? እንግዲውስ መፍትሄዎቹን እነሆ ...

የጨጓራ በሽታ አለብዎ? እንግዲውስ መፍትሄዎቹን እነሆ ...

 

የgastric pain ምስል ውጤት

 

የጨጓራ በሽታ መፍትሄ ወይም ህክምና የሚሆነው በመጀመሪያ የጨጓራ ህመማችን ምን ዓይነት ምግቦች ስንመገብ ወይም ምን ዓይነት ተግባሮች ስናደርግ ሊነሳብን እንደሚችል ለይተን ማወቅ ተገቢ ነው፡፡

የጨጓራ ግድግዳ መድከም ወይም መሳሳት በቀላሉ ግድግዳው ለምግብ መፍጫ አሲዶች እንዲጋለጥ ስለሚደርገው ለቁስለት ይዳረጋል በዚህ አማካይነት የጨጓራ በሽታ ይከሰታል፡፡

የተጐዳና ስስ የጨጓራ ግድግዳ ካለዎት በጨጓራ በሽታ የመያዝ ዕድልዎ ይጨምራል፡፡ በተጨማሪም ሌሎች የጨጓራ በሽታ መነሻ ምክንያቶች አሉ፡፡የጨጓራ ባክቴሪያ በመባል የሚጠራው ኤች. ፓይሎሪ አንዱ የጨጓራ በሽታ መነሻ ነው ይህ ባክቴሪያ የጨጓራ ግድግዳን የሚያጠቃ ሲሆን በቀላሉ ከሰው ወደ ሰው ይተላለፋል በተጨማሪም በተበከለ ውሃ እና ምግብ ይተላለፋል፡፡

✔ሌሎች ለጨጓራ ሊያጋልጡ ከሚችሉ ምክንያቶች መካከል፦

∵ከመጠን ያለፈ አልኮል መጠጣት

∵በመደበኛ ሁኔታ የህመም ማስታገሻ መድሃኒቴች መጠቀም ለምሳሌ፦ ኢቡፕሮፊን፣ አስፕሪንኮኬይን መጠቀም

∵ዕድሜ (የጨጓራ ግድግዳ ዕድሜ በጨመረ ቁጥር እየሳሳ ይመጣል፡፡

ሌሎች ዝቅተኛ አስተዋጽኦ ያላቸው የጨጓራ ህመም መነሻ ምክንያቶች መካከል በህመም፣ አደጋ ወይም በቀዶጥገና ጊዜ በሚፈጠር ጭንቀት፣ በቫይረስ ኢንፌክሽን እና በምግብ ስልቀጣ ችግር ሊከሰት ይችላል፡፡

✔ጨጓራን በቤት ውስጥ እንዴት ልንከላከለው ወይም ልናክመው እንችላለን?

∴ሲጋራ ማጨስዎን ያቁሙ።

∴ከመጠን ያለፈ አልኮል አይጠጡ።

∴ካፌይን ያላቸው መጠጦችን አይጠጡ ለምሳሌ ቡና፣ ሻይ።

∴ሲትሪክ አሲድ ያላቸውን የፍራፍሬ ጭማቆዎችን አይጠጡ ለምሳሌ፦ ብርቱካን፣ ሎሚ፣ ወይን ወዘተ

∴ከፍተኛ የቅባት/ፋት ይዘት ያላቸውን ምግቦች አይመገቡ፡፡

∴በፋይበር እና ፍላቮኖይድ የበለፀጉ ምግቦች ኤች. ፓይሎሪ የተባለውን የጨጓራ ባክቴሪያ ዕድገት ስለሚገቱ በጣም ጠቃሚ ናቸው ከነዚህ ምግቦች መካከል፦ ቀይ ሽንኩርት፣ ነጭ ሽንኩርት፣ አበባ ጐመን፣ የምግብ ማጣፈጫ ተክል፣ ጦስኝ፣ ሽምብራ እና አንዳንድ የሻይ ዓይነቶች ይጠቀሳሉ፡፡

 ምንጭ፡-©ኢትዮጤና

 

  

Related Topics