ሲኪዞፍሬኒያ

 

ሲኪዞፍሬኒያ

ሲኪዞፍሬኒያ፡- እየተባባሰ የመጣው የአዕምሮ መቃወስ አደገኛ የዕድሜ ልክ ከፍተኛ ስቃይ የሚያስከትል የአዕምሮ ህመም ሲሆን፣ በሽታው በተለይ ከሌሎች የአዕምሮ ህመሞች ለየት የሚያደርገው በወጣትነት ዕድሜ ክልል የሚከሰት፣ ተገቢውን ህክምና ካልተከታተሉ ዕድሜ ሙሉ ሰላም እየነሳ የሚያሰቃይ መሆኑ ነው፡፡

 

መለያ ባህሪያቶቹና መፍትሄዎች

 

  • ራስን የመጣል ምልክት ይታይባቸዋል፡፡ ይህም ማለት ለሚለብሱት ልብስ፣ ለንፅህናቸው፣ ለፀጉራቸው፣ ከሰዎች ጋር ላላቸው አቀራረብ ግድ ማጣት፣ ለዘመድ ወዳጅ ደንታ ቢስ መሆን፣ ለስራም ሆነ ለትምህርት ፍላጎት ማጣት ይከሰታል፡፡

  • የሀሳብ ንግግር መዛባት ይህም አንድን ሀሳብ ከሌላ ሀሳብ ጋር ማያያዝ ይሳናቸዋል ከዚህም የተነሳ የሚናገሩት ንግግር ለሰዎች የማይገባ ይሆናል፡፡ ሀሳባቸውን ሳይጨርሱ በመሃል ያቋርጣሉ፡፡

  • ስሜተ ቀዝቃዛ ናቸው፡፡ የሚያስደስት ነገር አያስደስታቸውም፣ የሚሳዝን ነገር አያሳዝናቸውም፡፡ በአጠቃላይ ከሰዎች ተቃራኒ ሆነው ይታያሉ፡፡ ነገሮችን ለይቶ የማወቅ ችሎታ መቀነስ ይከሰትባቸዋል፡፡ አንድን ነገር ደጋግመው ማውራት ወይም መስራት ያበዛሉ፡፡ ለምሳሌ ያህል ቀኑን ሙሉ ጭንቅላታቸውን መነቅነቅ ወይም በአንድ ቦታ  ሳይንቀሳቀሱ ለብዙ ሰዓት መቀመጥ የመሳሰሉት ይስተዋልባቸዋል፡፡

 

በአካባቢው የሚገኙ ዶክተሮችን ማማከር እንዲሁም የስነ.ዓምሮ ባለሙያዎችን በማማከር መፍታት ይቻላል፡፡

 

በሀኪሞች ከሚሰጡ መድሀኒቶች አና ህክምናዎች ጎን ለጎን የዚህ ህመም ተጠቂዎች እና ቤተሰቦቻቸው ልብ ሊሉቸው የሚገቡ ነጥቦች ሲኖሩ እነዚህም በሚከተሉት አርእስቶች ተካተዋል፡፡

 

  • የራስ በራስ/ የግል እንክብካቤ፡ ይህም ጭቀትን እዴት መቋቋም እደሚቻልና ወደተባባሰ ደረጃ የሚያደርሱ ምልቶችን ወይም ስሜቶችን ማጤን፡፡

  • የማበራዊ ክህሎት ልምምድ፡ ይህም ከሰዎች ጋር እንዴት መቀራረብ እና መግባባት እዳለብን ማወቅ እ መተግበር::

  • የቤተሰብ እክብካቤ፡ የዚህ ህመም ተጠቂ የሆኑ የቤተሰብ አባላት ምን ምን አይነት እንክብካቤዎችን ማድረግ እዳለባቸው ማስገንዘብ እና

  • የማህበራዊ እና ስነልቦናዊ ድጋፍ እና እንክብካቤ የበጎ ፍቃድ አገልግሎትንና የባለሙዎችን አገልግሎት በክፍያም ቢሆን የሚገኝበትን ሁኔታ ማመቻቸት ጠቃሚ ነው፡፡

ለማጠቃለልልም፤ በሀገራችን አብዛዎቹ የስነልቦና ጤና እክሎች ትኩረት የማይሰጣቸው እና ከሌሎች የአካል ህመሞች በማይተናነስ መልኩ ለቤተሰብ እና ግለሰብ ህይወት መቃወስ ከፍተኛ ሚናን እየተጫወቱ የሚገኝ ሲሆን ይህም ከመጠን ያለፈ የአልኮል ተጠቃሚነትን፤ የቤተሰብ መፍረስን፤ ወደተሟላ የህይወት ስኬት ግብ አለመድረስ እና ለሌሎች ወንጀሎች እና አካላዊ ህመሞች መንስኤ ሊሆን ይችላል፡፡ ስለሆነም ራስዎንም ሆነ በአቅራቢያዎ ያለ ሰው የአስተሳሰብም ሆነ የማህበራዊ ግኑኝነት እክል በሚያስተውሉበት ሰአት ሳይባባስ አስፈላጊው የምክር ወይም የህክምና አገልግሎት ማግኘት ቢቻል ሰላማዊ ኑሮን ማዝለቅ ይቻላል፡፡


መልካም የእረፍት ጊዜ፣

ከደመላሽ ዱባለ

 

  

Related Topics