የራስዎን ኮከብ ይፈልጉ እና ምን ያህል ባህሪዎን እንደሚገልጽ ይመልከቱ።

አስትሮሎጂ እና ትንበያዎች

 

አስትሮሎጂ ኮከብ

የአስትሮሎጂ አሰራር ግልጽ ስላልሆነ አንዳንዶች እውነተኛነቱን ቢጠራጠሩትም ሌሎች ደግሞ አንድ አይነት ኮከብ ያላቸው ሰዎች ባህሪ መመሳስል በማየት ዋጋ ይሰጡታል። የራስዎን ኮከብ ይፈልጉ እና ምን ያህል ባህሪዎን እንደሚገልጽ ይመልከቱ።

 

አሪስ(መጋቢት 12 – ሚያዝያ 11)

እነዚህ በግል ሰራ ውጤታማነት እና ታታሪነት ይታወቃሉ። አሪሶች በድፍረታቸው፣ በጽናታቸው እና ለስፖርት ባላቸው ፍላጎት ይታወቃሉ። ወጣቶች በተለይ ግለኝነት እና ጉራ የሚታይባቸው ሲሆን ጎልማሶች ደሞ ምንም ያህል ተጫዋች ቢሆኑም ለብቻቸው ሆነው የግላቸውን ነገር መስራት ይመርጣሉ። አሪሶች አላማ ያላቸው፣ ፈጣን፣ ቀዳሚዎች እና አዲስ ነገር ለመሞከር የማይፈሩ ናቸው። ህይወት ትግል እንደሆነ የሚያስቡት አሪሶች የሚፈለጉትን በሙሉ ለማግኘት መታገልን የሚመርጡ ሲሆን ይህ የመሪ ብቃት ወይም ነጭናጫነት ያሳይባቸዋል።

 

ከፍቅር ጋር በተያያዘ ከተቃራኒ ጾታ ጋር መጨዋወት የሚወዱ ሲሆን በቀላሉ እጃቸው የሚያስገቡት ሰው ከታጋይነት ባህሪያቸው ጋር ሰለማይሄድ አይመቻቸውም።፡ትንሽ ኮራ የሚልባቸውን እና የሚያለፋቸውን ሰው ይወዳሉ። ፍቅር መስራት(ወሲብ) የሚወዱት አሪሶች ይሄን ስሜታቸውን ቀዝቀዝ የሚያረግ ግንኙነት ይሸሻሉ።

 

 

 

ታውረስ (ሚያዝያ 12 – ግንቦት 12) ፦

ከዚህ ክፍል ጋር በመጀመሪያ የሚነሳው ነገር ስሜታዊነት እና ለነገሮች ጠንቃቃ እና ቁጥብነት ነው። ታውረሶች በብዛት የሚታወቁት በግትርነታቸው፣ በሚታይ ነገር ማመናቸው እና እነሱ ካልተቀበሉት ማንም የማይነቀንቃቸው መሆናቸው ነው። ለሰው ንብረት መጠንቀቅ፣ እዳ ውስጥ መሆንን መጥላት፣ ለውጥን በመፍራት ያላቸው ነገር ላይ ጥብቅ ማለት የሚታይባቸው ታውረሶች አለኝን በጣም የሚወዱ ናቸው። ከሰው ጋር ባላቸው ቅርርብ በጥንቃቄ መታየት ያለባቸው መሬቶች ነገር ገንፍሎ እስኪወጣ ታግሰው በውስጣቸው የሚይዙ ናቸው።

 

ከፍቅር ጋር በተያያዘ ጥሩ አፍቃሪዎች እና የሚመቹ ሲሆኑ ፍቅር መስራት (ወሲብ) ላይ ቁጥብ እና የተገደቡ ናው። ታማኝ እና ቤተሰብ አፍቃሪ መሆን እና ትንሽ ተቆጣጣሪ ወይም ፍቅረኛን የራስ ብቻ እንደሆነ በማሰብ ከሌላ ሰው ጋር ግዜ እንዳያሳልፍ መከልከል የታውረሶች ባህሪዎች ናቸው።

 

 

ጀሚኒ (ግንቦት 13 – ሰኔ 13) ፦

ስለጀሚኒዎች ሲታሰብ መጀመሪያ የሚመጣው ነገር ፈጣን፣ ንቁነት፣ ቅብጥብጥነት እና የራስ ግሄ ፈላጊነት ነው። የጀሚኒዎች አእመሮ እረፍት ሰለማይኖረው ትንሽ ደንጋራ ሊያስመሰላቸው ቢችልም ከሰው ጋር ሲጫወቱ የማይደብሩ ወይም እስኪደበሩ የማይቆዩ ይሆናሉ። ከህጻን ልጅ ጋር በሚያቀራርብ ሁኔታ አንድን ነገር ጠበቅ አርጎ ያለመያዝ እና አዲስ ነገሮችን ለማግኘት የሚሞክር ሆነውም ይታያሉ።

 

ከፍቅር ጋር በተያያዘ የፍቅር ጓደኛ በደንብ እስኪጀመር ድረስ ያለው ልብ ሰቀላ እና ሁሉን ነገር ተመስጠው ያሳልፉ እና ከሰለቹ በኋላ ሌላ ፍለጋ የሚያዩ ናቸው። ጀሚኒዎች እራሳቸው ደብሯቸው እንኳን ቢሆን ሌላ ሰው የሚያዝናኑት ስለሆነ ከፍቅረኛነት ይልቅ አብሮ የሚዝናኑት ጓደኛ  ለመሆን ይመረጣሉ።

 

 

ካንሰር (ሰኔ 14 – ሃምሌ 15) ፦

ካንሰሮች (በሌላ ስማቸው ውሃዎች) ጋር መጀመሪያ የሚነሳው ተንከባካቢ፣ ጥሩ ወዳጅ እና ለሰው አሳቢነት ነው። ቤተሰብ አፍቃሪ የሆኑት ካንሰሮች ከኑሮ ውጣ ውረድ ትንሽ ገለል ለማለት ቤታቸ አረፍ ማለት ይወዳሉ። ካንሰሮችን የሚገልጽ ቃል ቢኖር “ይሰማኛል” ነው ምክንያቱም ስሜታዊ ተንከባካቢ እና ለሰው አዛኝ ጸባይ ይታይባቸዋልና። አንድ ነገር ትክክል መስሎ ከተሰማቸው ሌላ ሰው ምን አለ አላለ ያማያስጨንቃቸው ካንሰሮች የሚረብሻቸውን ጎሸም ማድረግ ያውቁበታል።

 

ከእጮኛቸው ጋር ጠንካራም ለስላሳም አፍቃሪ እየሆኑ የሚቆዩት ውሃዎች ከትዳር በኋላ ቀዝቀዝ እያሉ ቢመጡም ለተዳር ታማኝ እና ቤተሰብ ጠባቂ ናቸው። ከፍቅረኛቸው ጋር ያሳለፉትን እያንዳንዷን ነገር በጭንቅላታቸው በመያዝም የታወቃሉ ካንሰሮች።

 

ሊዮ (ሃምሌ 16 – ነሃሴ 16) ፦

ከአንበሳ ጋር የሚመሳሰሉ ሲሆኑ በግርማ ሞገሳቸው፣ በጥሩ ነገር አሳቢነታቸው፣ በድፈረታቸው እና በራስመተማመናቸው ይታወቃሉ። መሪ መሆን የሚችሉ እና ትክክለኛ ታማኝ ተከታዮችን ማፍራት አይከብዳቸውም። በኑሮአቸው ላይ በበዛት የነሱን አመራር፣ አስተያየት እና ስምምነት የሚጠቁ ጉዳዮች ያጋጥማቸዋል።

 

ታማኝነት በራስ መተማምን በፍቅር ላይ የሚታዩ ጸባዮች ሲሆኑ ለቤተሰብ ትዳር እና ልጅ ትልቅ ቦታ በልባቸው ይተዋሉ። ክፍቅረኛ ጋር ጥሩ ግዜ ማሳለፍን፣ ተለቅ ያለ ሰርግ ወይም ስጦታ እና በስነስረአት የተዋብ ቤት እንደ ማረፊያ ማዘጋጅት ይታይባቸዋል።

 

 

ቪርጎ (ነሃሴ 17 – መስከረም 12) ፦

ቪርጎዎች የሚገልጻቸው አንድ ቃል “ትክክለኛነት” ነው። ምክንያቱም ቪርጎዎች ትልልቅ ውሳኔ ከመወሰናቸው በፊት መረጃ ሰብስበው፣ አገናዝበው ትክክለኛነቱን መቀበል እና እርገጠኛ መሆን አለባቸው። ዋና አላማቸው እራሳቸው ከዛም አልፎ የሚያቋቸው ሰዎች ትልቅ እና የራሳቸው ቦታ እንዲደርሱ መጣር ነው። ነገሮችን በጥልቀት መርመረው ትክክል እንዲሆን ሰለሚፈልጉ እና አለም ደግሞ ሁሌ ትክክል ሰለማትሆን የሚጎድላቸው ነገር ያለ መስሎ ይሰማቸዋል።

 

በፍቅር ላይም የፍቅር ጓደቸው ትክክለኛ እንዲሆን በመፈለግ ብዙ መሟላት ያለባቸውን ነገሮች ስለሚያስቀምጡ ትንሽ ቀዝቀዝ ይላሉ። ከስሜት ይልቅ የፍቅር ጓደኛን እንደ ህይወታዊ ውሳኔ በመቁጠር  እና ትክክለኛነቱን እርግጠኛ ለመሆን ስለሚጥሩ ፍቅር ላይ ቀዝቀዝ ብለው ይጀምራሉ። ነገር ግን አንዴ ለነሱ እንደሆነ/ች እርግጠኛ ከሆኑ በጣም ከባድ አፍቃሪ ነው ሚሆኑት።

 

 

ሊብራ (መስከረም 13 – ጥቅምት 12) ፦

ሊብራዎች ነገሮችን በማመጣጠን ይታወቃሉ። በአካባቢያቸው ሰላማዊ አየር እንዲኖር ብዙ ሰለሚጥሩ ችግሮችን በሽምግልና መፍታት ላይ አትኩረው ይሰራሉ። ምልክታቸው ሚዛን በትክክል የሚገልጻቸው ሊብራዎች የአንድን ሰው ሃሳብ በመረዳት እና ነገሮችን በማመቻመች  መሃከል መንገድ ላይ መድረስ ይችሉበታል። አንዳንዴ ጥፋተኛ ሳይሆኑ እራሱ ጭቅጭቅ ለማብረድ ሃላፊነቱን በመውሰድ ነገር ያበርዳሉ።

 

ጥሩ አፍቃሪ እንደሆኑ የሚነገርላቸው ሊብራዎች ከወደዱት ሰው የተሻለ መቼም እንደማያገኙ ያምናሉ። ለፍቅረኛቸው ያላቸው ቅንነንት እና እንክብካቤ ትዳራቸውን ውጤታማ የሚያርግ ሲሆን ሰውን የማዳመጥ ችሎታቸው የትዳር ጓደኛቸውን ያስደስታል።

 

ስኮርፒዮ (ጥቅምት 13 – ህዳር 12) ፦

ስኮርፒዮ ቆራጥ፣ ቅናታም፣ ሃይለኛ እና ያላቸውን ነገር ተንከባካቢ በመሆን ይታወቃሉ። የሚገልጻቸው አንድ ቃል “እፈልጋለሁ” ነው። ምክንያቱም ይህ አንድን ነገር የመፈለግ ባህሪያቸው ነው ቆራጥ፣ ሃይለኛ እና ለተቃራኒ ጾታ ማራኪ የሚያረጋቸው። በተጨማሪም የለውጥ ምልክት የሆኑት ስኮርፒዮዎች ማንኛውንም ችግር እና ለሞት የሚያደርስ አደጋ እንኳን አልፈው ትልቅ ቦታ የሚደርሱ ናችው።

 

ክፍቅር ጋር በተያያዘ በጣም ቅብጥብጥ ወይም በጣም ረጋ የሚሉ ሲሆን በጣም ቢያፈቅሩ እንኳን ሳይሳካ ግንኙነቱ ቢያልቅ ምንም እንዳልተፈጠረ የሚረሱ ናቸው። የለውጥ ሰው በመሆናቸው ቅብጥብጥ ቢሆኑ እራሱ አንድ ቀን ረጋ ማለታቸው አይቀርም። ፍቅር መስራት (ወሲብ) በጣም የሚወዱ ሲሆን ክፍቅረኛቸው ጋር በሱ ካልተጣጣሙ መቀጠል ይከብዳቸዋል።

 

 

ሳጂታሪየስ (ህዳር 13 – ታህሳስ 12 ) ፡-

በህይወት ውጤታማ ለመሆን ጥሩ ተስፋ ያለው፣ ስፖርተኛ፣ መጓዝ፣ አግር መጎብኘት እና አዳዲስ ነገሮችን ማወቅ የሚወዱ ናቸው ሳጂታርየሶች። ተስፋ በሚያስቆርጡ ግዜዎች እንኳን መልካም የሚያስቡት ሳጂታሪየስ ሃቀኝነት፣ ለሌላው በጎ ማሰብ ይታይባቸዋል። በመሆኑም ነህግ እና ፖለቲካ ነክ ነገሮች ላይ መስራት ያዋጣቸዋል። እድለኛ ጋርም የሚገናኙ ሰለሆነ ሎተሪ መሞከር ያዋጣቸዋል።

 

ክፍቅር ጋር በተገናኝ ስሜታዊ፣ ግልጽ እና እውነተኛ ሲሆኑ የሚያጨናንቃቸው ግንኙነት ፈጽሞ አይመቻቸውም። ከራሳቸው የትምህርት እና የብስለት ደረጃ የሚስተካከል አጋር የሚመርጡ ሲሆን የራሳቸውን ነገር መፈለጋቸው እና ለሰራ ብዙ ግዜ መስጠታቸው ትዳራቸውን ሊያቀዘቅዝ ይችላል።

 

 

ካፕሪኮርን (ታህሳስ 13 – ጥር 10) ፦

ረጋ ያሉ፣ በራስ መተማመን ያላቸው፣ ጥንቁቅ ግን ታታሪ ሰራተኛ እና መድረስ ያሰቡት ለማሳካት ትስፋ ሳይቆርጡ ላይ ታች የሚሉ ናቸው። በጣም የሚገልጻቸው አባባል “እጠቀማለሁ” የሚለው ነው። ይህውም ማግኘት የሚችሉትን ማንኛውንም ነገር ተጠቅመው መስራት ሰለሚችሉ ነው። ይህ በእጅ ያሉ ነገሮችን ጥቅም ላይ ማዋል በንግድ እና የቤት ኑሮ አመራር ላይ ትልቅ ጥቅም የሰጣቸዋል። ደረቅ መሆን እና ከሰው ጋር ባለ ግንኙነት ቀዝቃዛ የሆኑት ካፕሪኮርኖች የአላቃነት ስሜት ያጠቃቸዋል።

 

ፍቅር ላይ ታማኝ እና ለተዳር የሚሆኑ ቢሆንም ፍቅርን በጠቃላይ ጠበቅ እና መረር አረገው ስለሚይዙት ደስታውን ይቀንሱታል።

 

 

አኳሪየስ (ጥር 11 – የካቲት 11) ፦

አኳሪየሶች ጎበዝ፣ ነጻ አሳቢ፣ አመጸኛ እና አዲስ ሃሳቦችን አብሳሪ ናቸው። የሚታወቁብት ቃል “አውቃለሁ” ሲሆን ይሀውም ሰለማንኛውም ነገር አቃለሁ የሚሉ እና የማያውቁት ከሆነ ደሞ ሰለዛ ሲያወሩ ንጭንጭ የሚሉ ናቸው። በአስተሳሰብ እጅግ ጎበዝ ሲሆኑ ሰልወደፊት በማሰብ ከሊላው ሰው ፈጠን ብለው ይታያሉ። ሲታዩ ዝምተኛ እና ሰው የማያቀርቡ ቢመስሉም አንዴ ሰው ካቀረቡ ጥሩ ጓደኛ ይሆናሉ።

 

ፍቅር ጋር ሲመጣ አኳሪየሶች ከፍቅረኛ ጋር ቢሆኑም የራሳቸውን ግዜ እና ነጻነት የሚፈልጉ ናቸው። መጀመሪያ እንደማንኛውም ጓደኛ ቀርቦ ከዛ ወደ ፍቅር ማምራት የሚሳካላቸው ሲሆን አንዳንድ ግዜ በፍቅር ውስጥ ያሉ ሰሜታዊ ነገሮችን በመርሳት ከፍቅረኛ ጋር ማሳለፍ የሚችሉት ጥሩ ግዜ ሳይዝናኑበት ያልፋል።

 

 

ፒሰስ (የካቲት 12 – መጋቢት 11) ፦

ፒሰሶችን የሚገልጻቸው ነገር ፍቅር ነው ፤ ምንም አይነት ቅድም ሁኔታ በሌለበት መልኩ ሰውን የሚወዱት ፒሰሶች “አምናለሁ” በሚልው ቃል ይታወቃሉ። ይህ ትልቅ ስጦታቸው ሲሆን ሰለ ህይውት እና በአካባቢያቸው ባሉ ነገሮች ጥሩ ነገር አለ ብለው ያምናሉ። ፒሰሶች በብዛት ትልቅ የሚያምር አይን ያላቸው ሲሆን በአብዛኛው ስሜታቸውን አይናቸው ያሳብቅባቸዋል። ግትር መሆን ፈጽሞ የሚከብዳቸው ቲሰሶች አንዳንዴ ቆራጥ ውሳኔ ለመወሰን ይቸገራሉ። ተግባቢ እና አሪፍ አጫዋች ስለሆኑ በሚውሉባቸው አካባቢዎች ታዋቂ ናቸው።

 

በጣም ጥሩ አፍቃሪ ሲሆኑ በጥሩ የፍቅር ግንኙነት ውስጥ በጣም የሚገርም እና አስደሳች ግዜ የሚያሳልፉ ሲሆን የማይሆን ግንኙነት ውስጥ ቢሆኑ ደግሞ በቀላሉ ስለማይለቁ አስቸጋሪ ግዜ ያሳልፋል። ለነሱ የሚሆን አንድ ሰው እንዳለ የሚያምኑ ሲሆን እሱን እስኪያገኙ ተስፋ ሳይቆርጡ ይፈለጋሉ።

Source:- Arada

 

  

Related Topics