Notice: Undefined index: title in /home/hawassao/public_html/subpage_articles.php on line 174

Notice: Undefined index: title in /home/hawassao/public_html/subpage_articles.php on line 176

Notice: Undefined index: title in /home/hawassao/public_html/subpage_articles.php on line 216

Notice: Undefined index: title in /home/hawassao/public_html/subpage_articles.php on line 218

ፌስቡክ በሜሴንጀር የቀጥታ ቪዲዮ አገልግሎት መጀመሩን አስታወቀ

 

ፌስቡክ በሜሴንጀር የቀጥታ ቪዲዮ አገልግሎት መጀመሩን አስታወቀ

 

ፌስቡክ በሜሴንጀር ላይ የቀጥታ የቪዲዮ ማሰራጨት የሚያስችል አገልግሎት መጀመሩን አስታውቋል።

ግዙፉ የማህበራዊ ትስስር ድረ ገጽ ኩባንያ የሆነው ፌስቡክ እንደገለጸው፥ ተጠቃሚዎች ከጓደኞቻቻው ጋር በሜሴንጀር መልእክት በመለዋወጥ ላይ ባሉብት ጊዜ ለጓደኞቻቻው ማጋራት የሚፈልጉት ነገር ካጋጠማቸው በቀጥታ ለማስተላላፍ ይረዳል።

አገልግሎቱ ከቪዲዮ ጥሪ ጋር ይለያል ያለው ኩባንያው፥ የሜሴንጀር የቀጥታ ቪዲዮ ስርጭት ለየት ያሉ ነገሮች ሲያጋጥሙን ብቻ የምንጠቀምበት ነው ብሏል።

ፊት ለፊታችን የምንመለከተው ነገር ላይ ጓደኞቻችን አስተያየት እንዲሰጡ ከፈለግን የቀጥታ ቪዲዮ አገልግሎቱን በመጠቀም እንዲመለከቱ ማድረግ ያስችለናል።

እንዲሁም እንደ ጫማ፣ ልብስ እና ሌሎች ቁሶችን ለመግዛት ጎራ ብለን ለምርጫ ብንቸገር እንኳ ኦን ላይን ላሉ ጓደኞቻችን በቀጥታ የቪዲዮ አገልግሎቱ እንዲመለከቱ በማድረግ ማስመረጥ ያስችለናል።

ፌስቡክ በሜሴንጀር ላይ እንዲህ አይነት አገልግሎት መጀመሩ ከዚህ ቀደም በርካታ ተጠቃሚዎች ያለውን ስናፕ ቻት የማህበራዊ ትስስር ድረ ገጽ ለመፎካካር ይረዳዋል ተብሏል።

ስናፕ ቻት የተለያዩ የቪዲዮ መልእክት ለመለዋወጥ የሚረዳ ማህበራዊ ትስስር ድረ ገጽ ነው። 

ፌስቡክ እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጣር በ2013 ስናፕ ቻትን በ3 ቢሊየን የአሜሪካ ዶላር ለመግዛት ፍላጎት ቢያሳይም ሳይሳካለት ቀርቷል።

ምንጭ፦ www.huffingtonpost.co.uk