ስልክዎን ቻርጅ በሚያደርጉበት ጊዜ ምናልባት ያላስተዋሏቸው ነገሮች ይኖ

 

በርካቶች የዘመናዊ ተንቀሳቃሽ ስልክ ተጠቃሚዎች መሆናቸው ይታመናል።

የmobaile charege ምስል ውጤት

ዘመናዊ ስልኮች ከስሪታቸው አንጻር ባትሪያቸው ቶሎ የሚያልቅና አጭር ጊዜን የሚያስጠቅሙ ናቸው።

ከዚህ አንጻርም ተጠቃሚዎች ባትሪውን ቶሎ ቶሎ ሃይል ለመሙላት (ቻርጅ ለማድረግ) ሲሞክሩ ይስተዋላል።

ይህ ሁኔታ ደግሞ ምናልባትም የባትሪን እድሜ ሊያሳጥሩ እና ሙሉ በሙሉ ሊያበላሸውም ይችላል።

ስልክን ከመጠቀም ባለፈ ግን የባትሪ እድሜን ማራዘምና በአግባቡ ቻርጅ በማድረግ መጠቀም ቅድሚያ የሚሰጠው ጉዳይ ነው።

እርስዎ ከእነዚህ ተጠቃሚዎች አንዱ ከሆኑ ስልክዎን ቻርጅ በሚያደርጉበት ጊዜ ምናልባት ያላስተዋሏቸው ነገሮች ይኖራሉና እነዚህን የባለሙያ ምክረ ሃሳቦች እናካፍልዎ።

#ቻርጅ እያደረጉ ስልክን በጭራሽ አለመጠቀም፦ አንዳንድ ጊዜ አስቸኳይ ጉዳይ ቢያጋጥም እንኳን ስልክን ቻርጅ እያደረጉ ባይጠቀሙ ይመረጣል።

ምናልባት የግድ ከሆነ ደግሞ ስልኩ ከተሰራበት ኩባንያ አብሮ የተዘጋጀን ቻርጀር እየተጠቀሙ ቢሆን ይመረጣል ይላሉ ባለሙያዎች።

#ጥራት ያላቸውን ባለማራዘሚያ ቻርጀሮች መጠቀም፦ ባለማራዘሚያና በአብዛኛው በነጭ መደብ የተሰሩ እውነተኛ ቻርጀሮችን መጠቀም የባትሪን እድሜ ለማራዘም ይረዳልና ይጠቀሙበት።

#ሌሊቱን ሙሉ ቻርጅ ከማድረግ መቆጠብ፦ ወደ መኝታ ሲያመሩ ስልክዎን ቻርጀር ላይ ሰክቶ መተው አደጋ አለው።

ይህም ባትሪው ከመጠን በላይ ቻርጅ በማድረግ ማዳከም ይጀምራል፥ በአብዛኛው ስልክን በ40 እና በ80 ፐርሰንት መካከል ቻርጅ ማድረግ መልካም መሆኑንም ይመክራሉ።

ምክንያታቸው ደግሞ 40 ፐርሰንት ከደረሰ ቻርጅ ማድረጉ ግዴታ ሲሆን 80 ከሆነ በኋላ ነቅለው ቢገለገሉበት ችግር የለውም የሚል ነው።

#ስልክን ለተወሰነ ጊዜ ማጥፋት፦ ሰው ሰርቶ ማረፍ እንደሚፈልገው ሁሉ ስልክን ማጥፋትም ለባትሪው መልካም እንደሆነ ነው ባለሙያዎች የሚገልጹት።

ለዚህ ደግሞ ቢያንስ በሳምንት አንድ ቀን በተለይም ወደ መኝታ ሲያመሩ በማጥፋት እረፍት መስጠት።

ይህ ሲሆን ደግሞ የስልኩ ባትሪ እድሜ እንዳያጥርና ረዘም ላለ ጊዜ እንዲያገለግልዎ ይረዳል።

#ባትሪው እስከሚያልቅ ጠብቆ ቻርጅ አለማድረግ፦ ሌላውና በብዙ ሰዎች የተለመደው ጉዳይ ደግሞ የስልክ ባትሪ እስከሚያልቅ ጠብቆ ቻርጅ ማድረግ ነው።

ይህ ደግሞ ለባትሪ እድሜ የመጀመሪያውና ዋናው ጠር ነውና፥ ባትሪው 40 ፐርሰንት ላይ ሲደርስ ቻርጅ ማድረጉን ይመክራሉ።

ይህ ባይሆን እና በጣም ከወረደ በኋላ ቻርጅ ለማድረግ መሞከሩ ግን ባትሪን በመግደል ከፍተኛ ጉዳት ያስከትላልና ይህን ልማድ ያስወግዱም ይላሉ።

ከዚህ ባለፈም ቻርጀሩን ከቀጥተኛው ሶኬት ላይ አለመሰካት እና ከፍተኛ ሙቀት ባላቸው ቻርጀሮች አለመጠቀም መልካም ነው።

እርስዎም ከላይ የተጠቀሱትን የባለሙያ ምክረ ሃሳቦች በመተግበር የስልክዎን ባትሪ እድሜ ያራዝሙ።

 

ምንጭ፡- Eagle Technologies Ethiopia!!

 

 

  

Related Topics