የሪህ ህመም ምልክቶች እና መከላከያ መንገዶች…

 

 

የሪህ ህመም ምልክቶች እና መከላከያ መንገዶች…

የሪህ ህመም ምልክቶች እና መከላከያ መንገዶች…

 

 የሪህ ህመም መገጣጠሚያዎችን በተለይም በእግር አውራ ጣት አካባቢ ከፍተኛ የሆነ የህመም ስሜት እንዲሰማን የሚያደርግ ነው

የሪህ ህመም ሰውነታችን ዩሪክ አሲድን በተገቢው መንገድ ማስወገድ ባለመቻሉ ምክንያት የሚከሰት ሲሆን፥ ዩሪክ አሲድ የተባለው ኬሚካል በአጥንት መገጣጠሚያዎች ውስጥ በሚከማችበት ወቅት ህመሙ እንዲከሰትብን ያደርጋል።

ፕሮቲንን በውስጣቸዉ ከያዙ ምግቦች ውስጥ የሚገኘው ዩሪክ አሲድ የአጥንት መገጣጠሚያዎች በተለይም በእግራችን የአውራ ጣት፣ በቁርጭምጭሚት፣ በጉልበት፣ በእጃችን የክንድ እና የእጅ መገጣጠሚያዎች ላይ ተከማችቶ ይገኛል።

የሪህ ህመም ምልክቶች…

የሪህ ህመም በመገጣጠሚያዎች ላይ የሚከሰት የሕመም ስሜትሲሆን፥ የህመም ስሜቱ ከአንድ ወይንም ከዛ በላይ በሆኑ መገጣጠሚያዎች ላይ የሚከሰት ነው።

እንዲሁም የመገጣጠሚያ አካላችን ላይ አብጠት ምልክት፣ መቅላት እና የሙቀት መጠን መጨመር፣ ከፍተኛ የሆነ የሰውነት ግለት (ትኩሳት)እና ብርድ ብርድ ማለት ስሜቶች ይገኙበታል።

Gout-Foot-and-Ankle-Clinic-Blog.jpg

ሪህን ለመከላከል…

የፕሮቲን አወሳሰዳችን ማስተካካል፦ የሪህ ህመም ተደጋግሞ እንዳይከሰትብን በፕሮቲን የበለጸጉ እንደ ቀይ የበሬ ሥጋ፣ አሳ፣ እንቁላል፣ የመሳሰሉት ምግቦች መቀነስ ወይንም ለጊዜው ማስወገድ ይኖርብናል ተብሏል።

ውሃ መጠጣት፦ የሪህ ህመም ደጋግሞ እንዳይከሰትብን ውሃን አብዝቶ መጠጣት መልካም እንዶነም ይመከራል።

የአልኮል አለመውሰድ፦ የሪህ ህመም እንዳይከሰትብን የአልኮም መጠጥ አወሳሰዳችንን ማስተካካል ወይም አልኮም መጠጣት ማቆም መልካም ነው።

የሪህ ህመም ስሜቶች በሚስተዋልብን ጊዜ ወደ ጤና ተቋም በመሄድ የህክምና ባለሙያዎችን ማማከርም ይኖርብናል።

ምንጭ፦ www.arthritis.org

 

  

Related Topics