የማሽተት ችግር ለአልዛይመር በሽታ መጋለጥን ሊያመላክት እንደሚችል ተጠ

 

የማሽተት ችግር ለአልዛይመር በሽታ መጋለጥን ሊያመላክት እንደሚችል ተጠቆመ

 
የማሽተት ችግር ለአልዛይመር በሽታ መጋለጥን ሊያመላክት እንደሚችል ተጠቆመ
 

 የማሽተት አቅም መዳከም የመርሳት በሽታ (አልዛይመር) መጋለጥ ቅድመ ማስጠንቀቂያ ደወል ነው ተባለ።

በጃማ ኒዮሮሎጊ ላይ በሰፈረው ጥናት ተመራማሪዎች የማሽተት ችግር ያለባቸው እድሜያቸው የገፋ ሰዎች እንደ አልዛይመር ላሉ የአዕምሮ ጤና እክሎች የመጋለጥ እድላቸው ከፍ ያለ መሆኑን አረጋግጠናል ብለዋል።

የማሽተት ብቃት ደረጃ ከአልዛይመር በሽታ በተጨማሪ የግንዛቤ ችግር እና የአዕምሮ መቃወስ ያለባቸውን ሰዎች ጤና ለመረዳት እንደሚያግዝ ነው ጥናቱ የሚጠቁመው።

አጥኝዎቹ 1 ሺህ 400 ከ79 አመት በላይ መካከለኛ የአዕምሮ ጤና ያላቸውን አዛውንቶች የማሽተት ብቃት ለመመልከት ሞክረዋል።

የጥናቱ ተሳታፊዎች ምግብ እና ምግብ ነክ ያልሆኑ ነገሮችን ነው እንዲያሸቱ የተደረገው።

ተሳታፊዎቹ ሙዝ፣ ሽንኩርት፣ የፅድ ቅጠል፣ ነዳጅ እና የቀለም ማቅጠኛዎችን እንዲያሸቱ ተደርጎ የሰጡት ምላሽ ተመዝግቧል።

በአዛውንቶቹ ላይ ለሶስት አመት ተኩል በተደረገው ተከታታይ የማሽተት ፈተና 250 የሚሆኑት የጥናቱ ተሳታፊዎች ቀላል የግንዛቤ እክል እንዳለባቸው ተረጋግጧል።

ቀላል የግንዛቤ ችግር (Mild cognitive impairment) ከእድሜ መግፋት ጋር ተያይዞ የሚመጣ የማስታወስ፣ የቋንቋ፣ አስተሳሰብ እና ውሳኔ ሰጪነት መዳከምን ያመላክታል።

ምንም እንኳን የቀን ተቀን ውሎን በከፋ ደረጃ ባያውክም ለአዕምሮ ጤና መቃወስ በር ሊከፍት ይችላል።

በጥናቱ ቀላል የግንዛቤ እክል ገጥሟቸዋል ከተባሉት 250 ሰዎች ውስጥ 64ቱ እንደ አልዛይመር ላሉ የአዕምሮ ህመሞች ተዳርገው ተገኝተዋል ነው የሚለው ጥናቱ።

የማሽተት አቅማቸው በጣም ዝቅተኛ የሆኑ ሰዎች ለአልዛይመር በሽታ የመጋለጥ እድላቸው በ2 ነጥብ 2 በመቶ እንደሚጨምር ነው የተጠቆመው።

የጥናቱ ዋና መሪ እና በአሜሪካ ሚኒሶታ በሚገኘው ማዮ ክሊኒክ የነርቭ ህክምና መምህሩ ሮስበድ ሮበርትስ እንዳሉት፥ ጥናቱ እድሜያቸው የገፋም ሆነ ጥሩ የአዕምሮ ጤና ያላቸው ሰዎችን የማሽተት ብቃት መረዳት ለአልዛይመር በሽታ ተጋላጭነታቸውን ቀድሞ ለመለየት እንደሚረዳ አመላክቷል።

በመሆኑም የማሽተት ብቃታችን በጣም የወረደ ከሆነ ወደ ህክምና ተቋማት በማምራት ሀኪሞችን ማማከር ይገባል ነው ያሉት ሮበርትስ።

ይሁን እንጂ አንዳንድ ሰዎች ስር በሰደደ ሳይነስ እና የመተንፈሻ አካላት ችግር የተነሳ የማሽተት ብቃታቸው አነስተኛ ሊሆን እንደሚችልም አስገንዝበዋል።

በጥናቱ የማሽተት አቅም መዳከም ለአልዛይመር በሽታ ያጋለጠበት ምክንያት ግን አልተብራራም።

በቀጣይም የማሽተት ችግር እና የአዕምሮ መቃወስ ያላቸውን ግንኙነት የተመለከቱ ጥናቶች መሰራት ይኖርባቸዋል ተብሏል።

 

 

ምንጭ፦ www.healthylifetricks.com/

 

 

  

Related Topics