Notice: Undefined index: title in /home/hawassao/public_html/subpage_articles.php on line 174

Notice: Undefined index: title in /home/hawassao/public_html/subpage_articles.php on line 176

Notice: Undefined index: title in /home/hawassao/public_html/subpage_articles.php on line 216

Notice: Undefined index: title in /home/hawassao/public_html/subpage_articles.php on line 218

ለኮምፒዩተሬ የትኛዉን አንቲ ቫይረስ ልጠቀም?

ለኮምፒዩተሬ የትኛዉን አንቲ ቫይረስ ልጠቀም?

የcomputer ምስል ውጤት


የአንቲ ቫይረስ ፕሮግራም ወይም ሶፍትዌር ማለት ኮምፒዩተራችንን ከተለያዩ የቫይረስ አይነቶች ለመከላከልና አስቀድመዉ ሲስተማችንን ያጠቁ ቫይረሶችን ለማጥፋት ዲዛይን የተደረገ ሶፍትዌር ሲሆን በአሁኑ ጊዜ ኮምፒዩተርን ያለ አንቲ ቫይረስ መጠቀም የአለም ዋንጫ ጨዋታን ያለበረኛ እንደመጫወት ማለት ነዉ፡፡ 
የአንቲ ቫይረስ ሶፍትዌር ለኮምፒዩተራችን ይሄን ያህል አስፈላጊ ቢሆንም የትኛዉን መርጠን መጠቀም እንዳለብን መወሰኑ አስቸጋሪና ወሳኝ ጉዳይ ነዉ፡፡ ምክንያቱም በኢንተርኔት ላይ ያሉ አንቲ ቫይረሶች ሁሉም እኛ የምንፈልገዉን አይነት ጥበቃ ይሰጡናል ማለት አይደለም፡፡ አብዛኞቹ አዳዲስ ቫይረሶችን መቋቋም አይችሉም ወይም እዉነተኛ የአንቲ ቫይረስ ሶፍትዌር አይደሉም፡፡ 
ከዚህ በታች ለኮምፒዩተራችን አስተማማኝ ጥበቃ የሚሰጡ አንቲ ቫይረሶችን ዝርዝር አቅርበንላችኋል ተከታተሉን፡፡

1. Kaspersky Anti-Virus (2016)

መቀመጫውን ሩስያ ባደረገው Kaspersky Lab የተፈጠረው ይህ አንቲ ቫይረስ የኮምፒዩተር ቫይረሶችን በመለየትና በማጥፋት ረገድ ከሌሎች የአንቲ ቫይረስ ሶፍትዌሮች የተሻለ ውጤት ማስመዝገብ ችሏል። ከአመት አመት ልምድ እያካበተ የመጣው ይህ አንቲ ቫይረስ ለአጠቃቀም ቀላል እና ውጤታማ ጥበቃ ለኮምፒዩተሮች በመስጠት አንደኛ ደረጃን አግኝቷል።
AV-Test Institute = 18/20

2. McAfee AntiVirus Plus (2016)
በሀገራችን ብዙም ያልተለመደው ይህ የአንቲ ቫይረስ ሶፍትዌር የአስተማማኝ ጥበቃ ለደንበኞቹ በመስጠትና በየሳምንቱ የአንቲ ቫይረሱን ዴፍኒሽን አፕዴት በማድረግ ይታወቃል። ቫይረስ ዴፍኒሽኑን ቶሎ ቶሎ አፕዴት የማድረጉ ዋነኛ ጥቅም ሶፍትዌሩ ከተሰራ በኋላ የተለቀቁ አዳዲስ ባህሪ ያላቸውን ቫይረሶች ለመለየት እንዲያስችለው ነው።
AV-Test Institute = 17.4/20

3. Bitdefender Antivirus Plus 2015

ከተሻለ የቫይረስ ጥበቃው ላይ እንደተጨማሪ ግልጋሎት የተሰራለት Autopilot Mode አንድ ጊዜ ከተጫነ በኋላ ያለ ተጠቃሚው እርዳታ ማንኛውንም አይነት ግልጋሎትና ስካን በራሱ እንዲያከናውን ስለሚረዳው የ2016 ምርቱ Bitdefender 3ተኛ ደረጃን ለመያዝ በቅቷል። የአንቲ ፊሺንግ ጥበቃው ከሁሉም አንቲ ቫይረሶች አስተማማኝ በመሆኑ Bitdefender የምንጠቀም ከሆነ የተጭበረበረ ዌብሳይት ላይ የመግባት እድላችን የጠበበ ነው።
AV-Test Institute = 17.2/20

4. Avast Pro Antivirus 2016
በሀገራችን ብዙዎች የሚጠቀሙበት Avast በታዋቂው AV-Test Institute የደረጃ ምደባ መሰረት የአራተኛ ደረጃን ማግኘት ችሏል። የ2016 ምርቱ Avast ቫይረሶችን ከተጠቃሚው ፋይሎች የሚለይበት መንገድና ኮምፒዩተሩን ፉል ስካን የሚያደርግበት ፋጥነት በእጅጉ የተሻሻለ ሲሆን አምና ከነበረበት አምስተኛ ደረጃ ወደ አራት ከፍ ማለት ችሏል።
AV-Test Institute = 16.9/20

5. ESET NOD32 Antivirus 9
በጥንታዊቷ ግብጽ የጤንነት የለምነትና የሰዎች ጠባቂዋ ጣኦት ኢሴት ስም የተሰየመው ይህ አንቲ ቫይረስ እንደስያሜው ሰዎችን ባይሆንም ኮምፒዩተሮችን በአስተማማኝ ሁኔታ መጠበቅን ችሏል። በተለይም ለኔትዎርክና ሲስተም ፋይል ቫይረሶች ፍቱን መድሀኒት ሲሆን ችግሮችን በጸጥታ ለተጠቃሚው መጠቃቱን እንኳን ሳያሳውቅ ስለሚፈታ የሌሎች አንቲ" ቫይረሶች ቫይረስ ሊኖር ይችላል የሚል ማስጠንቀቂያ ለሰለቸው ጥሩ ምርጫ ነው።
AV-Test Institute = 16.5/20

ምንጭ፦ አቢሲንያ ኮምፒውቴክ