የአለማችን የመጀመሪያው ስማርት ሻማ ይፋ ሆኗል።

የአለማችን የመጀመሪያው ስማርት ሻማ ይፋ ሆኗል።

 በስማርት ስልክ አካማኝነት የሚበራ እና የሚጠፋው ሻማ በ2017 ለገበያ ይቀርባል

 

ሉደላ በተባለ ኩባንያ የተሰራው ሻማ ትክክለኛ የእሳት ነበልባል ያለው ሲሆን፥ በስማርት ስልክ አማካኝነት የሚበራ እና የሚጠፋ ነው ተብሏል።

“ዋይ ፋየር” በተሰኘ ቴክኖሎጂ የተሰራው ስማርት ሻማ ክብሪት አልያም ሌሎች እሳት አስነሺዎችን ሳንጠቀም ልናበራው እና ልናጠፋው የምንችል መሆኑም ተገልጿል።

የ44 አመቱ የሉደላ መስራች ጃሚ ቢያንቺኒ እንደገለጹት፥ ሻማው 10 ሴንሰሮች የተገጠሙለት ሲሆን፥ በኤሌክትሪክ ሀይል ነው የሚሰራው።

ስማርት ሻማውን በመረጥነው አኳኋን (ለሻማ ራት ግብዣ አልያም ለፍቅር ምሽት) እንዲሆን ማድረግ እንችላለንም ብለዋል።

ከዚህም በተጨማሪ ከዚህ ቀደም የተለመደው ሻማ ጥሎት የሚያልፈው ቆሻሻ እና ሽታ ከማስቀረት ባሻገር በኤሌክትሪክ ሀይል ስለሚሰራ የቆይታ ጊዜው ገደብ የለሽ መሆኑን ነው ቢያንቺኒ የገለጹት።

ሻማውን ከስማርት ስልካችን ጋር በማገናኘት ብርሃኑን መጨመር ወይም መቀነስ እንችላለንም ነው ያሉት።

የሉደላ ሻማ ለቅድመ ትዕዛዝ 99 የአሜሪካ ዶላር ዋጋ የተተመነለት ሲሆን፥ በችርቻሮ ግን እስከ 149 ዶላር ድረስ ሊሸጥ እንደሚችል ተጠቁሟል።

ስማርት ሻማው በመጪው የፈረንጆቹ 2017 ለገበያ እንደሚቀርብ ይጠበቃል።

ምንጭ፦ www.techworm.net/

 

  

Related Topics