ስለ ቡና አንዳንድ ነገሮች

 

ስለ ቡና አንዳንድ ነገሮች

 

Image result for ቡና

 

 

1) ቡና በመጀመሪያ ጊዜ የተገኘው(የታወቀው) በኢትዮጵያ እረኞች በ 800 ዓ/ም አካባቢ ሲሆን እረኞቹም ያስተዋሉት ፍየሎቻቸው ቡናውን በልተው የመቅነዝነዝና የመደነስ ስሜት ሲታይባቸው ነው።

2) ቡና በምድር ላይ በብዛት ከሚሸጡ ነገሮች ሁለተኛውን ደረጃ ይይዛል። Global Exchange በዘገበው መሰረት ቡና ከ 50 በሚበልጡ ሀገራት ከ 25 ሚሊዮን በሚበልጡ ገበሬዎች ይመረታል።

3) የቡና ዘር አይነቶች ሁለት ናቸው። እነሱም Arabica እና Robusta ይባላሉ። 70% የሚያክሉ የቡና ዘሮች Arabica ናቸው። Robusta የቡና ዘር እንደ Arabica ብዙም ተወዳጅነት የሌለው ሲሆን ከ Arabica ትንሽ መረር የሚልና የ caffeine መጠኑም ከ Arabica እጥፍ ነው።

4) በቡና ምርት በአለም አንደኛ ብራዚል ስትሆን የአለማችንን የቡና ምርት 40% ትሸፍናለች። ሁለተኛና ሶስተኛ ደግሞ ኮሎምቢያና ቬትናም ናቸው።

ኢትዮጵያ በቡና ምርት በአለም ሰባተኛ ስትሆን በአፍሪካም ደግሞ አንደኛ ነች።

5) በአለም ውዱ ቡና Kopi luwak ሲባል ግማሹ ኪሎ ከ 100 - 600 ዶላር ያወጣል።

አመራረቱም Luwak የሚባል እንስሳ ቡናውን እስከነቅርፊቱ ከበላው በኋላ እንስሳውም በተፈጥሮው የቡና ፍሬውን ሆዱ መፍጨት ስለማይችል ፍሬው በአሩ እንዳለ ይወጣል። ከዛ ፍሬው ከአሩ ተለቅሞ ታጥቦ ለጥቅም ይውላል።

6) በአለማችን ታሪክ ቡናን ህገወጥ ለማድረግ አምስት ጊዜ ተሞክሮ ነበር

1ኛ) በ 1511 AD በ Mecca 

2ኛ) በ 16ኛው ክፍለ ዘመን የጣልያን የካቶሊክ ቄሶች እና ዲያቆኖች ቡናን ስይጣናዊ ነው በማለት አስከልክለው ነበር። ቢሆንም ግን Pope Clement VII የሚባሉ የዚያን ጊዜ የካቶሊክ ዋና ጳጳስ ቡናን በጣም ይወዱ ስለነበር ቡናን አስጠምቀው ተመልሶ ህጋዊ እንዲሆን አድርገዋል።

3ኛ) በ 1623 AD Murad IV የሚባል የ Ottoman መሪ ለቡና መጠጥ የመጀመሪያውን ቅጣት ለዓለም አስተዋውቋል። ቡና ለጠጣ ሰው ቅጣቱም ግርፊያና ባህር ውስጥ መወርወር ነበር።

4ኛ) በ 1746 AD የ ስዊድን መንግስት እንደ ሲኒ ያሉ የቡና መጠጫ እቃዎች እራሱ ይዞ መገኘትን ህገወጥ አድርጎት ነበር።

5ኛ) 1777 AD የ የፕሩሺያው Frederick the Great ቡና ከቢራ መጠጥ ጋር እንዳይፎካከር ብሎ ህገወጥ አድርጎት ነበር።

7) ቡና ከልክ በላይ ከተጠጣ ሊገድል ይችላል። ግን ያንን መጠን ለመድረስ አንድ ሰው 100 ኩባያ መጠጣት አለበት።

8) ቡና Alzheimer's በሽታን፣  Parkinson's በሽታን፣ የተለያዩ የካንሰር በሽታዎችን እና የስኳር በሽታን የመከላከል አቅም አለው።

9) ቡና ላይ ክሬም ሲጨመር ቡናው ለበለጠ ጊዜ ትኩስ ሆኖ ይቆያል።

10) ቡና ላይ ወተት ሲጨመር የማነቃቃቱን ሃይል ይቀንሳል።

 

11) እስከአሁን ድረስ ከተፈሉት ትልልቅ ኩባያ ቡናዎች ከሁሉም ትልቁ በ ደቡብ ኮሪያ july 2014 ላይ የተፈላ ሲሆን እሱም 14 ሺህ ሊትር ነው።

12) ቡናን ማሽተቱ ብቻ ከእንቅልፍ ሊያነቃ ይችላል። ተመራማሪዎች እንደሚገልጹት ከሆነ ቡናን ማሽተቱ እራሱ አእምሮ ውስጥ ያሉትን የአንዳንድ genes እንቅስቃሴ በመቀየር የእንቅልፍ ስሜትን ሊቀንስ ይችላል። ያንን ያሸተቱትን ቡና ሲጠጡ ደግሞ ሳያሸቱ ከሚጠጡት ቡናው 10 ደቂቃ ቀድሞ ደም ውስጥ እንዲደርስ ያደርጋል።

13) በጣም ጠቁረው የተቆሉ የቡና ፍሬዎች ቀላ ካሉት በ caffeine መጠናቸው አነስ ይላሉ።

ምንጭ፦http://tekamii.blogspot.com/