የአእምሮ አኑሪዝም አጠቃላይ ግንዛቤ

የአእምሮ አኑሪዝም አጠቃላይ ግንዛቤ

(Brain Aneurysm Overview)

Image result for brain aneurysm

 

የጭንቅላት አኑሪዝም ወይም የጭንቅላት የደም ቧንቧ ግድግዳ መነፋት የሴረብሮቫስኩላር( Cerebrovascular) በሽታ አይነት ሲሆን በደም ቧንቧ ግድግዳ ድክመት ምክንያት የደም ቧንቧ መተለቅና መነፋት ሲከሰት የሚደርስ እስከ ሞት የሚያደርስ በሽታ ነው።

 

ይህ በሽታ ብዙ ጊዜ የሚፈጠረው በጭንቅላታችን መሰረት ላይ በሚገኘው የዊሊስ ክብ ውስጥ በሚገኙት የደም ቧንቧ መስመሮች ላይ ነው። ብዙ ጊዜ የዚህ በሽታ ምልክቶች ላይታዩና  በሽታውም ላይታወቅ ይችላል። የጭንቅላት አኔዩሪዝሙ ከፈነዳ ደም በጭንቅላታችን ሊፈስና ስትሮክ ሊያጋጥም ይችላል። በጭንቅላችን ውስጥ ደም ሲፈስ ሰብአራክኖይድ ሄሞርሄጅ (Subarachnoid Hemorrhage) ተብሎ ይጠራል።

የአእምሮ አኑሪዝም መንስኤ

(Brain Aneurysm Cause)

 

የጭንቅላት አኑሪዝም በዘር ወይም በኑሮአችን በሚከሰቱ ችግሮች ሊፈጠር ይችላል። በእድሜ ወይም በደም ቧንቧ መጠጠር ምክንያት የጭንቅላት አኑሪዝም በሽታ ከተወለድን በኋላ ሊይዘን ይችላል። የሚከተሉት ነገሮች የጭንቅላት አኑሪዝም በሽታን ሊያባብሱ ይችላሉ።

 

የቤተሰብ የዘር ታሪክ: ቤተሰቡ ውስጥ የጭንቅላት አኑሪዝም በሽታ የነበረበት ሰው ካለ ለበሽታው ይበልጥ ተጋላጭ ይሆናል።

ፆታ፡ ሴቶች ለበሽታው ይበልጥ ተጋላጭ ናቸው።

የአኑሪዝም በሽታ ታሪክ፡ የጭንቅላት አኑሪዝም በሽታ ይዞን የሚያቅ ከሆነ እንደገና በሽታው ሊይዘን የሚችልበት እድል ሰፊ ነው።

ብሔር፡ ጥቁር አሜሪካያኖች ከነጮች ይልቅ የሰብአራክኖይድ ሄሞርሄጅ ችግር ያጋጥማችዋል።

የደም ግፊት፡ የሰብአራክኖይድ ሄሞርሄጅ የደም ግፊት ያለባቸውን ሰዎች ላይ ይበልጥ ሊያጠቃ ይችላል።

ማጨስ፡ ሲጋራ ማጨስ በከፍተኛ ሁኔታ ለጭንቅላት አኑሪዝም ተጋላጭ ሊያደርግ ይችላል።

የአኗኗር ዘይቤ፡ መጠጥ ማብዛት፣ ከልክ ያለፈ ውፍረት እና የኮኬን ተጠቃሚ መሆን ለጭንቅላት አኑሪዝም መምጫ መንስኤ ሊሆኑ ይችላሉ።

የአእምሮ አኑሪዝም ምልክቶች

(Brain Aneurysm Symptoms)

በአለማችን ከሚገኙ ህዝቦች ውስጥ 1%ቱ ያህል የጭንቅላት አኑሪዝም በሽታ አለባቸው ተብሎ ይገመታል። አብዛኞቹ የጭንቅላት አኑሪዝም በሽታዎች ምንም አይነት ምልክት ወይም ህመም አያስከትሉም፥በቶሎ ሊድኑና ሊታከሙም ይቻላሉ። ነገር ግን በጣም ከተለቁ በአከባቢው ባሉ የጭንቅላት ህዋሶችና ነርቮች ላይ ጫናና ጉዳት ሊያደርሱ ይችላሉ። በዚህ ጊዜም የሚከተሉት ምልክቶች ሊያጋጥሙ ይችላሉ።

 

ለቀናቶችና ለሰዓታቶች የሚቆይ ድንገተኛ የራስ ምታት

የመደናገር እና በአንድ የፊት ጎን ብቻ የድካም ስሜት መሰማት

የአይን ፑፒል መስፋት

የእይታ መቀየር

ማስመለስ

የአንገት ህመም

ንዛሬ (Seizures)

ራስን መሳት

 

የጭንቅላት አኑሪዝም በሽታ ከከፋ የሰብአራክኖይድ ሄሞርሄጅ ወይም የደም መፍሰስ ስለሚያስከስት ስትሮክ ብሎም ሞት ሊያስከትል ይችላል።

የአእምሮ አኑሪዝም ምርመራ

(Brain Aneurysm Diagnosis)

 

ብዙ ጊዜ የጭንቅላት አኑሪዝም ምልክቶች ስለማይታዩ በሽታው ያለባቸው ሰዎች እንዳለባቸው የሚያውቁት ለሌላ በሽታ ሲመረመሩ ነው። የህክምና ባለሙያዎ የጭንቅላት አኑሪዝም አለበዎት ብሎ ካሰበ የሚከትሉትን ምርመራ ሊያደርግ ይችላል።

 

በኮምፒውተር የታገዘ ቶሞግራፊ ስካን (Computed Tomography (Ct) Scan)፡ ሲቲ ስካን የውስጥ ጭንቅላት መድማት ለማሳየት ይረዳል። ሰብአራክኖይድ ሄሞርሄጅ ነው ተብሎ ከተጠረጠረ የሉምባር ፓንክቸር ህክምና ጋር የCt ስካን ምርመራ ይደረጋል።

 ኮምፒውትድ ቶሞግራፊ አንጅዮ ግራም ስካን (Computed Tomography Angiogram (Cta) Scan) ፡ Cta ይበልጥ አስተማማኝ ሲሆን በመርፌ በሚሰጥ የደም ማቅለሚያ መድሃኒት እርዳታ የተሻለ የምርመራ ውጤት ያስገኛል።

ማግኔቲክ ሬዞናንስ አኒጅዮግራፊ (Mra) ፡ ይህ ዘዴ ከCt ስካን ጋር ተመሳሳይ ሲሆን የማግኔቲክ ፊልድና የራዲዮ ዌቭ ሃይልን በመጠቀም የሰውነታችንን የደም ቧንቧዎችን ምስል ያሳያል። ይህ ሊሆን የሚችለው ልክ እንደ Cta ስካን የደም ማቅለሚያዎችን በመጠቀም እና የተለየዩ የህክምና ቴክኒኮችን በመጠቀም ነው።

የአእምሮ አኑሪዝም መከላከያው

(Brain Aneurysm Prevention)

የተስተካከለ ክብደትን መያዝና መጠበቅ

በምግብ ላይ የጨው መጠንን መቀንስ

የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግ

አለማጨስ

የስብ ያላቸው ምግቦችን በመቀነስ ፍራፍሬዎችን መጠቀም

መጠጥ አለማብዛት

በቀን ለጥቂት ደቂቃዎች እራስን ማረጋጋት

ስለምንወስደው መድሃኒቶች የህክምና ባለሙያችንን ማማከር

 

የአእምሮ አኑሪዝም ህክምናው

(Brain Aneurysm Medication)

ከ10ሚሊ ሜትር በታች የሆነ የጭንቅላት አኑሪዝም ብዙ ለከፋ ጉዳት ሰለማያደርስና የጭንቅላት ቀዶ ጥገና በጣም ለአደጋ ስለሚያጋልጥ የህክምና ማለሙያዎች ብዙ ጊዜ በሽታውን በቅርበት መከታተል እና እንዳያድግ የሚረዱ ዘዴዎችን እንድንጠቀም ያደርጋሉ።

 

ከ10ሚሊ ሜትር በላይ ከሆነ ወይም ከዚህ በፊት ቀደም ብሎ ፈንድቶ ከሆነ እና ስቃይ ካለው የህክምና ባለሙያዎ የቀዶ ህክምና ሊያዝልዎ ይችላል። የሚከተሉት ቀዶ ጥገናዎች ለፈነዳ እና ላልፈነዳ የጭንቅላት አኑሪዝም ይደረጋሉ።

 

ኮይል ኢምቦላይዜሽን (Coil Embolization): በዚህ ቀዶ ጥገና በጣም ትንሽ ቧንቧ ወደተጠቃው የደም ቧንቧ ይላክና በአኑሪዝሙ አከባቢ የደረጋል። ከዛም በጣም ደቃቅ የብረት ኮይሎች በትንሹ ቧንቧ ይገቡና የአኑሪዝም ግፊት እንዲቀንስ ይደረጋል። ይህ ዘዴ ምንም እንኳን ሙሉ በሙሉ በሽታውን ባያስቆመውም ከሰርጂካል ክሊፒንግ በተሻለ ሁኔታ ለአደጋ አያጋልጥም። ይህ ቀዶ ጥገና በትልቅ ሆስፒታል መካሄድ አለበት።

 

ሰርጂካል ክሊፒንግ (Surgical Clipping)፡ ይህ ቀዶ ጥገና በአኑሪዝሙ መሰረት አከባቢ ትንሽ የብረት ክሊፕ በመጠቀም የደም ዝውውር በአኔዩሪዝሙ አከባቢ እንዳይኖር ያደርጋል። በዚህም አኑሪዝሙ እንዳይነፋ እና ግፊት እንዳይበዛበት ያደርጋል። ይህ ቀዶ ጥገና እንደ ታካሚው አኑሪዝሙ ግዝፈት፣ቦታ እና አጠቃላይ ጤና ሁኔታ ሊካሄድና ላይካሄድ ይችላል።

ምንጭ፡--overview

 

 

  

Related Topics