Notice: Undefined index: title in /home/hawassao/public_html/subpage_articles.php on line 174

Notice: Undefined index: title in /home/hawassao/public_html/subpage_articles.php on line 176

Notice: Undefined index: title in /home/hawassao/public_html/subpage_articles.php on line 216

Notice: Undefined index: title in /home/hawassao/public_html/subpage_articles.php on line 218

የሰውን ልጅ በቅዝቃዜ አድርቆ ወደ ህይወት መመለስ ይቻላልን?

 በቅዝቃዜ አድርቆ ወደ ህይወት መመለስ ይቻላልን?

(Can a Human be Frozen and Brought Back to Life?)

 

 Image result for ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ

 

አንዳንዴ ፊልም ስንመለከት አንድ ሰው በቅዝቃዜ ደርቆ (Cryosleep) ከጊዜያት በኋላ ያለምንም ማርጀት ወይም በሸታ ሲነሳ እናያለን፡፡ የደረቀበት ምክንያት ተፈልጎ ወይም በአጋጣሚ ሊሆን ይችላል፡፡ ለምሳሌ ፈውስ ያልተገኘለት በሽታ አንድ ሰው ከያዘው ፈውሱ እስኪገኝለት ድረስ ፈልጎ ለዓመታት ደርቆ ይሆናል፡፡ ወይም ደግሞ ሳይታሰብ በበረዶ ግግር ውስጥ ደርቆ ቆይቶ ይሆናል፡፡

የዚህ አድርቆ ወደ ህይወት የመመለስ ሳይንሳዊ ተግባር ‹‹ክራዮኒክስ›› (Cryonics) ተብሎ ሲጠራ ስለ እርሱ የሚያጠናው ዘርፍ ደግሞ ‹‹ክራዮጀኒክስ›› (Cryogenics) ተብሎ ይጠራል፡፡

 

ከክራዮኒክስ ጀርባ ያለው ሳይንሳዊ ትንታኔ

 

ክራዮኒክስ የአንድን ሰው አካል በከፍተኛ ቅዝቃዜ በማስቀመጥ ወደፊት አንድ ቀን ወደ ህይወት ለመመለስ የሚደረግ ቴክኒክ ነው፡፡ ይህ ቴክኒክ በአሁኑ ጊዜ በአለማችን እየተፈፀመ ያለ ቢሆንም ነገር ግን ገና በጨቅላነት ደረጃ ላይ ያለ ነው፡፡ አንድ ሰው በዚህ ሁኔታ ሲቀመጥ በ‹‹ክራዮኒክ ሰስፔንሽን›› (Cryonic Suspension) ውስጥ ሆነ እንላለን፡፡ የዚህ መሰረታዊ ተስፋ የሆነው፣ አንድ ሰው ፈውስ ከሌለው በሽታ የሞተ ከሆነ ሰውየውን አድርቆ ወደፊት ፈውስ ሲገኝለት ወደ ህይወት መመለስ ነው፡፡

‹‹ለምን እስኪሞት እንጠብቃለን?›› ለሚለው ጥያቄ ደግሞ መልስ አለ፡፡ በአሁኑ ወቅት በአለማችን በህይወት ያለ ሰው ላይ ይህን ተግባር መፈፀም ህገ-ወጥ ነው፡፡ በክራዮኒክስ መድረቅ የሚፈልጉ ሰዎች በመጀመሪያ መሞት አለባቸው፤ ይህም ማለት ልባቸው መምታት ማቆም አለበት ማለት ነው፡፡

 

ህይወታቸው ካለፈ እንዴት ብለው ሊነሱ ይችላሉ?

 

በዚህ አድርቆ ወደ ህይወት የመመለስ ተግባር ላይ የተሰማሩ ኩባንያዎች እንደሚሉት ከሆነ ህጋዊ ሞት እና ሙሉ በሙሉ ሞተ ልዩነት አላቸው፡፡ ህጋዊ ሞት የልብ ምት ሲያቆም ማለት ሲሆን ሙሉ በሙሉ ሞት ግን የአንጎል ስራ ሙሉ በሙሉ ሲያቆም ማለት ነው፡፡ እነሱ እንደሚሉት ከሆነ ልብ መምታቱን ከአቆመ በኋላም አንጎል ስራውን ለተወሰነ ደቂቃት ይቀጥላል፡፡ ስለሆነም ክራዮኒክስ ይህን የአንጎል ስራ ክፍል አቀዝቅዞ በማስቀመጥ ሰውየው ወደፊት እንዲነሳ ያደርጋል (ምንም እንኳን በተግባር ባይረጋገጥም)፡፡

 

የክራዮኒክስ አተገባበር

 

የሰውየው የልብ ምት ካቆመ እና መሞቱ ከተረጋገጠ በኋላ የተፈረመለት ኩባንያ ስራውን ይጀምራል፡፡ የኩባንያው የድንገተኛ አደጋ ቡድን ወዲያውኑ አስከሬኑን ይረከባል፡፡ የአስከሬኑን አንጎል በቂ ኦክስጅን እና ደም በመለገስ ስራውን እስከ ክራዮኒክስ ተቋሙ ድረስ ለማስቀጠል ይሞከራል፡፡ ከዛም አስከሬኑን በበረዶ ውስጥ አስቀምጠው በጉዞው ወቅት የደም መርጋትን ለመከላከል anticoagulant (ደም እንዳይረጋ የሚያደርግ ኬሚካል) ይወጉታል፡፡ በተቋሙ ተጠባባቂ ቡድን አስከሬኑን ለመረከብ በተጠንቀቅ ይጠብቃል፡፡ በተቋሙ ከደረሱ በኋላ ትክክለኛው የማድረቅ ስነ-ስርዓት ይጀምራል፡፡

ከዚህ ቀጥሎ የሚኖረው ሂደት ጥንቃቄ ያስፈልገዋል፡፡ እንዲሁ ዝምብለው በቀዝቃዛ የናይትሮጅን ፈሳሽ ውስጥ አስከሬኑን አይጥሉትም፡፡ ምክንያቱም በሰውነት ውስጥ ያሉ ሕዋሳት ተሰባብረው ይሞታሉ፡፡

ውሃ ወደ በረዶነት ሲቀየር እየተለጠጠና እየሰፋ ይመጣል፡፡ የሰውነት ሕዋሳት ደግሞ በአብዛኛው ከውሃ ስለተሰሩ ውስጥ ያለው ንጥረ-ነገር እየሰፋ ሕዋሱን ያፈርሰዋል፡፡ ስለዚህ ኩባንያው ውሃውን Cryoprotectant በተባለ ሌላ ፈሳሽ ይተካዋል፡፡ ይህ ከግላይሴሮል (Glycerol) የተመሰረተ ውህድ፣ በረዶ እንዳይመሰረት በማገድ የሰውነት ሕዋሳትን ይከላከላል፡፡ ይህ ሂደት Vitrification በመባል ይጠራል፡፡

ከዚህ ሂደት በኋላ አስከሬኑ በካርቦንዳይኦክሳይድ በረዶ እስከ -202 ዲግሪ ፋረንሃይት ድረስ እንዲቀዘቅዝ ይደረጋል፡፡ ከቅድመ ማቀዝቀዙ በኋላ ወደ ዋናው የማድረቁ ስነ-ስርዓት ይገባል፡፡ አስከሬኑ በፈሳሽ ናይትሮጅን ወደ ተሞላ የብረት ኮንቴነር ውስጥ ይገባል፡፡ በዚህን ጊዜ አስከሬኑ እስከ -320 ዲግሪ ፋረንሃይት ድረስ ይቀዘቅዛል፡፡

የክራዮኒክስ ሂደት በገንዘብ ርካሽ አይደለም፡፡ እስከ 200,000 ዶላር ድረስ ሊያስወጣ ይችላል፡፡

 

ክራዮኒክስ በትክክል ይሰራል?

 

ብዙ ተቺዎች እንደሚሉት እነዚህ የክራዮኒክስ ተግባር ሰጪ የሆኑትን ኩባንያዎች ‹‹ሰዎችን ዘላለማዊ ኑሮ ታገኛላችሁ በማለት ገንዘባቸውን ይቀማሉ፡፡›› ሲሉ ይተቻሉ፡፡ ደግሞም ክራዮኒክስ የሚተገብሩ ሳይንቲስቶች እስካሁን ማንንም ወደ ህይወት አለመመለሳቸውና በቅርቡም እንደማይመልሱ መናገራቸው ለክራዮኒክስ ድጋፍ አይሰጥም፡፡ ትልቁ መሰናክል ደግሞ አስከሬኑን ለማስነሳት ሙቀት በሚሰጥበት ወቅት በትክክለኛው ሙቀትና ፍጥነት ካልተካሄደ ሕዋሳቱ በረዶ ሰርተው ተሰባብረው ሊሞቱ ይችላሉ፡፡

በእርግጥ በክራዮኒክ ሰስፔንሽን ውስጥ የተቀመጠ አንድም ሰው ወደ ህይወት ባይመለስም ሌሎች እንስሳት ግን ከሞት ሊነሱ ይችላሉም ተነስተዋልም፡፡ አንዳንድ እንቁራሪቶች እና ሌሎች መሰል እንስሳቶች በውስጣቸው በረዶ እንዳይሰራ የሚከላከል ፕሮቲን ስለሚያመነጩ ሙሉ በሙሉ በቅዝቃዜ ቢደርቁም ወደፊት ይነሳሉ፡፡ ሌላ ምሳሌ ለመጥቀስ፣ የሰው ልጅ ፅንስ በክሊኒኮች ውስጥ ደርቆ ከቆየ በኋላ ወደ እናትየው ማህፀን ተጨምሮ ጤነኛ የሰው ልጅ ሆኖ ማደግ ይችላል፡፡

ክራዮባዮሎጂስት (Cryobiologist) ወደፊት ናኖ ቴክኖሎጂ (Nanotechnology) ላይ ተስፋቸውን ጥለዋል፡፡ እነሱ እንደሚሉት ከሆነ ናኖ ቴክኖሎጂ ወደ ህይወት የማምጣቱ ሂደት ላይ የሚሞቱትን ሕዋሳት ብቻ ሳይሆን በእርጅና እና በበሽታ የሚበላሹትን ሕዋሳት ጭምር መጠገን ያስችላል፡፡ አንዳንድ Cryobiologist እንደተነበዩት ከሆነ በ2045 እ.ኤ.አ. የመጀመሪያው በክራዮኒክስ የደረቀ ሰው ወደ ህይወት ይመለሳል፡፡

በአጭሩ ክራዮኒክስ በተስፋ ላይ የተመሰረተ ነው፡፡

ምንጭ፡--frozen-human-bringtolife