የጨጓራ ባክቴሪያ ምልክቶች

 

የጨጓራ ባክቴሪያ ምልክቶች

 

 

የጨጓራ ባክቴሪያ ያለባቸው አብዛኛዎቹ ሰዎች ምንም አይነት የበሽታው ምልክት አይታይባቸውም። ነገር ግን ይህ ባክቴሪያ ቁስል በሚፈጥርበት ወቅት የበሽታው ምልክቶች መታየት ይጀምራሉ በተለይ ሆድዎ ባዶ በሚሆንበትና ምግብ ከተመገቡ ከጥቂት ሰዓት በኋላ እንደ ሆድ ህመም ዓይነት ምልክቶች ሊታይ ይችላል። ይህ በሽታ ሄድ መጣ የሚል ህመም አለው። ምግብ መመገብ ወይም ፀረ አሲድ (AntiAcid) መድሃኒቶች መውሰድ ይህን ህመም ያስታግሰዋል።

✔ ከጨጓራ ባክቴሪያ (H.pylori) ኢንፌክሽን ጋር የተያያዙ ምልክቶች እነዚህን ይመስላሉ፦

• የሆድ መነፋት ስሜት

• ማቅለሽለሽ እና ማስመለስ

• ከመጠን ያለፈ ግሳት

• የምግብ ፍላጐት ማጣት/መቀነስ

• ያልተጠበቀ የሰውነት ክብደት መቀነስ ናቸው።

ነገር ግን እነዚህ የተለመድ ምልክቶች ስለሆኑ በሌሎች ሁኔታ/በሽታ የመታየት አጋጣሚ አላቸው። አንዳንድ የጨጓራ ባክቴሪያ ምልክቶች በጤናማ ሰው ላይ ሊታዮ/ሊከሰቱ ይችላሉ። እነዚህ ምልክቶች የተለመድ ናቸው ነገር ግን ከእነዚህ አንድ በቀጣይነት የሚታይብዎት ከሆነ ወደ ህክምና ተቋም በመሄድ አስፈላጊውን ምርመራና ህክምና ያድርጉ። ዓይነ ምድርዎ ጠቆር ካለ ወይም ደም የተቀላቀለበት ከሆነ (የሚያስመልስዎትም ጭምር) ሃኪምዎን በፍጥነት ያማክሩ።

ምንጭ፡-EthioTena

 

 

  

Related Topics