ለጸጉር እድገት የሚጠቅሙ በቤት ውስጥ የሚዘጋጁ 9 ተፈጥሯዊ ዘዴዎች»

 

ለጸጉር እድገት የሚጠቅሙ በቤት ውስጥ የሚዘጋጁ 9 ተፈጥሯዊ ዘዴዎች»

 

Image result for nice hair

ጸጉርዎት ከጤንነቱም ባሻገር በቁመቱ እንዲያድግ የሚፈልጉ ከሆነ በቤትዎት ብዙ ሊያደርጉት የሚችሉ ነገሮች አሉ፡፡ እነዚህን ዘዴዎች ከዛሬ በመጀመር መፍትሔ ያገኛሉ፡፡

 

1. ከአልኮል ነጻ የሆነ የአፕል ጭማቂ - የአፕል አቺቶ ለምግብ መብላላት እና ለሳይንስ ችግሮች መድሀኒት ነው፡፡ ነገር ግን ጥሩ መአዛ ያለው ይሄ ፈሳሽ ለፀጉራችን እድገትም ወሳኝ ነው፡፡ የአፕሉን ጭማቂ በፀጉራችን ላይ በማድረግ ማሸት ከዛም በቀላሉ መለቃለቅ፡፡

 

2. እንቁላል - ለብዙ አመታት እንቁላል ለፀጉር ብዛት ሰዎች ይጠቀሙበት ነበር፡፡ በፕሮቲን መበልጸጉም ፀጉርን ጥሩ እንዲሆን ያደርገዋል፡፡ እንቁላልን መብላትም ለጸጉር እድገት አስተዋጽኦ አለው፡፡ የእንቁላሉን ፈሳሹን ክፍል በወይራዘይት እና ማር በመደባለቅ አንደ ኮንዲሽነር መጠቀም እንችላለን፡፡

 

3. አብሽ - ይሄ ተፈጥሮአዊ መንከባከቢያ ፀጉርን በፍጥነት እንዲያድግ ያደርገዋል፡፡ የአብሽን ዱቄት ከ ኮኮናት ወተት ጋር በመደባለቅ በጸጉር እና በጭንቅላት ቆዳችን ላይ መቀባት፡፡ የተዋሀዱት ነገሮች ለጥቂት ደቂቃ ከቆዩ በኋላ በሻምፖ ይታጠቡ፡፡

 

4. በርበሬ- በርበሬ ከተፈጥሮ የፀጉር ማሳደጊያዎች አንዱ ሲሆን በአካላቶቻችን ያሉ ዝውውሮችንም እንዲስተካከሉ ያደርግልናል፡፡ የደም ዝውውራችን መስተካከል ደግሞ ጸጉራችን በፍጥነት እንዲያድግ ይረዳናል፡፡ በምግባችን ውስጥ በርበሬ መጨመር ለጸጉራችን እድገት አስተዋጾ ያደርጋል፡፡

 

5. የኮኮናት ወተት- የኮኮናት ወተት በውስጡ ፀረ-ባክቴርያ ንጥረ ነገር የያዘ ሲሆን ይህም ምግቦችን እንዳይብላላ የሚየያደርጉትን ተህዋህሲያንን ያጠፋልናል፡፡ ወተቱንም ብንጠጣው በተለይም ከስራ በኋላ ጥማችንን ያረካልናል፡፡ በኮከናት ወተት ውስጥ ያሉ ፕሮቲን እና ቅባትም ለፀጉር እድገት ከፍተኛ ቦታ አላቸው፡፡ ማድረግ ያለባቹ ነገር ቢኖር የኮኮናት ወተትን ፀጉራችሁን በመቀባት ሌሊቱን ሙሉ አቆዩት ከዛም በሙቅ ውሀ ታጠቡት፡፡ ይሄንን ደጋግሞ መጠቀም ፀጉራችሁ ባጭር ጊዜ ውስጥ እንዲያድግ ይረዳዋል፡፡

 

6. አረንጓዴ ሻይ - አረንጓዴ ሻይ በውስጡ ጸረ-ኦክሲዳንትን ስለያዘ ብርድ እና ጉንፋንን ሊከላከል ይችላል፡፡ ሻዩ ከዛ ባሻገር የፀጉር እድገትን በማፋጠን ፀጉርን እንዳይጎዳ ያደርጋል፡፡ በቀን አንድ ስኒ አረንጓዴ ሻይ መጠጣት ለጸጉር ጤንነት ይረዳል፡፡ በተጨማሪም ለብ ያለ አረንጓዴ ሻይ በፀጉር እና በቆዳችን ላይ ማድረግ ጤናማ እድገት እንዲኖረው ያደርጋል፡፡

7. የቫይታሚን ኢ ዘይት - ቫይታሚን ኢ ዘይት በሽታ አምጪ ተዋህሲያኖችን በመከላከል ጤናማ ፀጉር እና ቆዳ እንዲኖረን ያደርጋል፡፡ የቫይታሚን ኢ ዘይትን በመቀባት ለአንድ ሌሊት ከቆዩ በኋላ በተፈጥሮ ሻምፖ መታጠብ፡፡ ይሄን ፀጉራችንን ያጠነክርልናል እንዲሁም ፎሮፎርን ያስወግዳልናል፡፡

 

8. የስጋ መጥበሻ ዘይት ፡- የስጋ መጥበሻ ወይም የሮዝመሪ ዘይት ብዙ ጊዜ በመካከለኛው ዘይቱን በሻይ ወይም በወይራ ዘይት በመደባለቅ እንደ ሻምፖ ወይም ኮንዲሽነር መጠቀም ለፀጉርዎ እድገት ከፍተኛ ሚና አለው፡፡

 

9. ከፍተኛ ፕሮቲን ያላቸው ምግቦች፡- በፕሮቲን የበለፀጉ ምግቦች ፀጉራችን ከስር ጀምሮ እንዲጠነክር ያደርግልናል፡፡ የፀጉርም እድገት ጤናማ እና ጠንካራ እንዲሆን ከፈለጉ እንደ ቱና፣ እርጎ፣ አሳ፣ ቀይ ስጋ እና ዶሮ ያሉ በፕሮቲን የበለጸጉ ምግቦችን መብላት ይጠቅሞታል፡፡

ምንጭ፡-.yegara