ሬት፤ ከምሬቱ ሌላ ጥቅሙ

ሬት፤ ከምሬቱ ሌላ ጥቅሙ

 

Aloe Vera Pflanze

 

ኢትዮጵያ ዉስጥ በየአካባቢዉ እንደሚነገረዉ ቋንቋ የየግል መጠሪያ ቢኖረዉም በአብዛኛዉ ግን ሬት በሚለዉ ስሙ ይታወቃል። ብዙዎችም ዛሬም ቢሆን ለጡት አስጣይነት ይጠቀሙበታል። ለመብቀል ብዙ ክብካቤና ዉሃ አይፈልግም፤ በዉስጡ ግን በርከት ያለ ዉሃ የማጠራቀም ባህሪ አለዉ።

 

ከእሬት ዘሮች በተለይ በእንግሊዝኛዉ አሎይ ቬራ በመባል የሚታወቀዉ ተክል ለተለያዩ የመዋቢያ ቅባቶችና ሳሙናዎች መሥሪያነት በመዋሉ በሰፊዉ ይታወቃል። በሌላ በኩል በምግብነቱ ደግሞ ለጤና በሚሰጠዉ ጥቅም ተዓምረኛዉ ተክል፤ ማለትም ዎንደር ፕላንት የሚል ቅፅል አትርፏል። እሬት በምሬቱ ነዉ የሚታወቀዉ፤ ለዚህም ነዉ እናቶች ጡት አልተዉ ያሉ ልጆችን ወደዚያ እንዳይመለሱ ለማድረግ የእዚህን ተክል ፈሳሽ ጡታቸዉ ላይ በመቀባት እንዲመራቸዉ የሚያደርጉት። ምሬቱን በዘዴ አለዝበዉ የሚመገቡት ደግሞ አሉ። ታዲያ ሁሉም የእሬት ዘር ወደአፍ አይገባም ለህይወት አደገኛ የሆነ ዓይነት አለዉና።

የእሬት ተክል ለመብቀል ምቹ አካባቢን አይፈልግም። በብዛት የዉሃ እጥረት ባለባቸዉ አካባቢዎች እንደመገኘቱ ደረቅ ሳይሆን በዉስጡ ከፍተኛ ዉሃ ማጠራቀም ይችላል።

 

Aloe Vera Pflanze

 

ከእሬት ዘሮች አሎይ ቬራ በመባል ከሚታወቀዉ ተክል የሚገኘዉ ዝልግልግ ፈሳሽም የቆዳን ድርቀት አስወግዶ በማዉዛት፣ ያረጀዉን የማደስ አቅም እንዳለዉ መረጃዎች ያመለክታሉ። ከአሎይ ቬራ የተዘጋጁ የፀጉር ሻምፑዎች፣ የእጅ፣ የፊትና የቆገላ ክሬሞች፣ የጸጉር ቅባቶችም በየገበያዉ ይገኛሉ። ከዚሁ ተክል የተዘጋጁ ጭማቂዎችም እንዲሁ፤ ምሬቱን በስልት እየቀነሱም የሚበሉትም አሉ።

ለመጀመሪያ ጊዜ የተጠቀሙበት ደግሞ አረቦች ሲሆኑ እንደመድሃኒት እንደተጠቀሙበትም አክለዉ ገልጸዋል። ኢትዮጵያ ዉስጥ ለዚሁ አገልግሎት የሚዉለዉ የሬት ዘር በተለይ ኅብረተሰቡ ሴት እሬት የሚለዉና እሾህ የሌለዉ የተክል አይነት እንደሆነም አመልክተዋል። ከእሬት ዘሮች አሎይ ቬራ የተባለዉ በመጀመሪያ ከየት እንደተገኘ እጅግም እንደማይታወቅ ነዉ እዕፀዋት ሳይንስ ተመራማሪዉ ያመለከቱት። የታሪክም ሆነ የእስጽዋት ሳይንስ ተመራማሪዎች በጋራ የሚስማሙበትን ግን ምናልባት ከደቡብ ምዕራብ የአረብ አካባቢዎች የተገኘ እንደሆነ ነዉ። በተለይም ስዑድ አረቢያና የመን ዉስጥ። በአሁኑ ጊዜም ከእሱ የሚገኘዉን ጥቅም በሚገባ ለማግኘት ሲባል በተፈጥሮ የሚገኝበት ሳይሆን በማሳደጊያ የአትክልት ስፍራ ክብካቤ እና ማሻሻያ እየተደረገለትም ዉስጡ የሚይዘዉ ፈሳሽ መጠን እንዲጨምር፤ እንደፍላጎቱ መጠን ደግሞ ምሬቱም እንዲቀንስ ተደርጎ እንደሚያድግ ገልጸዉልናል።

ምንጭ፡-.dw.com