ጤናዎን ስጋት ላይ የሚጥሉ 5 የስራ መስኮች

 ጤናዎን ስጋት ላይ የሚጥሉ 5 የስራ መስኮች 

 

 


1.የእሳት አደጋ ሰራተኞች የፖሊስ አባላት
እነዚህ ሁለቱ የስራ መስኮች በስራ ላይ አደጋ የተጋለጡ ሲሆኑ የአካል ጉዳት እክሎች ተደጋግመዉ የሚደርሱባቸዉ ናቸዉ፡፡ ከዚህ በላይ ግን እነዚህ ስራዎች ለጤና አደጋ የሚሆኑት ከፍተኛ ውጥረት ያለባቸዉ መሆናቸዉ እንደሆነ በስራ ላይ አደጋዎች በርካታ ምርምሮችን የሰሩት አሜሪካን ምሁር ዶ/ር ዳንኤል ቾስዉድ ያስረዳሉ፡፡ በተለይ የእስት አደጋ 
ያሳያሉ፡፡ በተለይም የእሳት ቃጠሎዉ አሰቃቂ የሚሆንበት ግዜ ድንጋጤ እና ውጥረት አጠቃላይ የሰውነት ስርአታችን በተለይም የልባችን ስራ ከዜሮ ወደ መቶ ያዘልለዋል፡፡ በዚህም ምክንያት ሁል ግዜ በንቃት አደጋዎች መጠበቅ የእለት ተእለት ስራ ይሆናል፡፡ በዝያም ላይ የእንቅልፍ እጦት፤ ሰአቱ ስለማይመች ሰአት ተብቆ ምግብ በደንብ አለመብላት ተጨምሮበት እንጀራቸዉ ፈተና አለበት፡፡

2.የህግ ጠበቃዎች 
ምናልባት የህግ ጠበቆች ቦርሳቸዉ አንጠልጥለዉ ሙሉ ልብስና ከረባት ለብሰዉ የፍርድ ቤትን ውሎ ሲያደምቁ እና ህጎችን እየሰነጠቁ ሲያስረዱ ሙሉ ልባቸዉ ያየ በሰአት የሚያስከፍሉትን በተለይ በውጪ አገር የሰማ ድግሞ የህግ ጠበቃ ምን ጎደለበት ማለቱ አይቀርም፡፡ ኬርየርካስት የተባለዉ ድረገጽ ያጠናዉ ጥናት ግን የሚያሳየዉ ተቃራኒዉን ነዉ፡፡ ይሀዉም እ.ኤ.አ 2007 በጠበቆች ላይ የተደረገ ጥናት እንደገለጠዉ አሁን በጥብቅና ስራ ካሉ ባለሙያዎች ወጣት ተማሪዎች ወደ ጥብቅና ሞያ እንዲገቡ የሚመክሩት የአስር ጠበቆች አራቱ ብቻ ናቸዉ፡፡ ስራቸዉ ምቾት የለዉም ፤በውጥረት የተሞላ ነዉ ይላሉ ጠበቆቹ፡፡ እኛ አገር ብዙ ግዜ በአንድ ኬዝ ተምነዉ የሚያስከፍሉትን ነዉ በብዛት የምናውቀዉ፡፡ የውጪ አገር ትምህርት የቀመሱት በሰአት ይፍን ያህል ክፈሉኝ ይላሉ፡፡ ይህም ብዙ ሰአት ለደንበኛዉ ጉዳይ ባጠፉ ቁጥር ብዙ ብዙ ብር ስለሚመጣ ሁሉን ነግረ ትተዉ ለረጅም ሰአታት ዶክመንቶችን እቤት ወስደዉ ሳይቀይሩ ይመረምራሉ ‹‹እረፍት የለሽ መሆናቸዉ በበሽታ መከላከላቸዉን በማዳከም በቀላሉ በበሽታ ተሸናፊ ያደርጋቸዋል፡፡

3.የትራንስፖርት ሰራተኞች 
የትራንስፖርት ሰራተኞች ሲባል ሌሊት ዘጠኝ ሰአት ተነስተዉ በሚኒባስ ወደ ክልል የሚከንፉት የሚኒባስ ሽፌርና ረዳት ጀምሮ እስከ አውሮፕላን አብራሪ እና የአስተናጋጆች ድረስ ይዘልቃል፡፡ በአውቶቢሱ እና በባቡር ሹፌሮችም ከዚህ ስር ይጠቃለላሉ፡፡ በተለይም የትራፊክ ሪፖርቶች ስንሰማ ሹፎሮች ግንባር ቀደም ሟች ሆነዉ ይገኛሉ፡፡ በአደጋዉ በተጨማሪ ለረጅም ሰአታት መሪ ላይ መቀመጣቸዉ የመውለድ ብቃትን እስከ ማጣት የሚያደርስ ጉዳት ላይ ይጥላቸዋል፡፡ የወንዶች ዘር ምርት በሙቀት በከፍተኛ ሁኔታ ተጽኖ የሚደርስበት በመሆኑ በየተወሰነ ርቀት መኪናውን እያቆመ እረፍት እንዲወስዱ እና እንዲቀዘቅዙ የሚመከረዉ ለዚህ ነዉ፡፡ እንቅልፍ ዕጦት የተለያዩ የተበጣጠሱ ምግቦች ፤ ዳቦና ፓስቲ እና ሌሎችም ሆድ ገብተዉ እጅግም ጉልበት እና ጤና የማይሆን ምግቦችንም በመብላት የትራንስፖርት ሰራተኞች ይታወቃሉ፡፡ ይህ ለጤና ጠንቅ ነዉ፡፡ ምግብን እና መጠጥን በተመለከተ ከሰማይ ላይ ሾፌሩቹንና አተናጋጆች አይጨምሩም፡፡

4. በፈረቃ የሚሰሩ የጤና ባለሙያዎች
ጤናችንን እንደንጠብቅ ይረዳሉ፤ ይንከባከባሉ ብለን የምናስባቸዉ የጤና ባለሙያዎች እራሳቸዉን ጤና በማይሰጥ የሞያ መስክ ውስጥ መሆናቸዉ ጥቂት ሊያስገርማቸዉ ይችላል፡፡ እንደ ጥረስሳቸዉ ጤና የማይሰጥ የሙያ መስክ ውስጥ መሆናቸዉ ጥቂት ሊያስገርም ይችላል እንደ ነርሶች እና ድንገተኛ ክፍል ሀኪሞች አሉት ባለሙያዎቹ ከፍተኛ በእንቅልፍ መዛባት ለሚመጣ የጤና ችግር ለውጥረት ሆርሞኖች መጨመር ከፍተኛ የሰውነት ክብደት መጨመር፤ እንዲሁም ለሆድ እና ለልብ ህመሞች የሚያጋልጥ አደጋ አለባቸዉ፡፡ በ2012 ዓ.ም በጆርናል ኦፍ ነርሲንግ አደሚንስትሪሽን ምርምር ጆርናል ላይ የወጣ ጥናት እንዳመለከተዉ በዚህ ጉዳይ በተሰራ ጥናት ተሳታፊ ነርሶች መካከል 55 ከመቶዎቹ ለጤናቸዉ አስጊ የሆነ ከፍተኛ ክብደት እንዳላቸዉ ታይቶዋል፡፡ በተለይ ስራቸዉ ብዙ እንቀስቃሴ የማይፈለገውና ለረጀም ሰአታት የሚቀመጡት የበለጠ የጤና ችግሮች ተጋላጭ መሆናቸዉ ፕሪቬንሽን መጽኄጽ ጨምሮ ጽፏል፡፡

5. የወንበር ዲጄዎች
ከጠዋት እስከ ማታ ወንበር ላይ ተቀምጠዉ ሲሰሩ የሚውሉ ሰዎች ለአደገኛ የስራ መስክ ከተካተቱ ሰዎች ይመደባሉ፡፡ እነዚህ በአንዳንድ ሰዎች ወንበር አጫዎች ወይም የወንበር ዲጄዎች የሚባሉት በስራ ጣቢያችን ረጅም ሰአታት በወንበር ላይ ቢሮዉ ወስጥ የሚያሳልፉ አንደ ሂሳብ ሰራተኞች፤ ማኔጀር ጻፊዎች እና ሌሎችም ናቸዉ እነዚህ ሰዎች በመቀመጥ ለሚመጣ ክበደት የነርቭ መዳከም፤ የጀርባ ህመም ተጋላጭነት እንቅስቃሴ ውስጥ ካሉ ሰዎች በብዙ እጥፍ የበለጡ መሆኑን በጥናቶች ተረጋግጠዋል፡፡

የመፍትሄ አሳቦች
ሙያቸዉ ለጤናቸዉ አደጋ የሚሆንባቸዉ እና አንዳንድ ማስተካኪያዎች እንዲያደርጉ የሚመክርዉት ከላይ ያነሳናቸዉ ባለሙያዎች ብቻ አይደሉም፡፡ የጉለበት ሰራተኞችም፤ ካሸሮች፤የካፌ እና የምግብ ቤት አስተናጋጆች ከፍተኛ አካላዊ ድካም ስለሚያጋጥማቸዉ በአጠቃላይ ጤናችን ላይ የመዳከም ተጽኖ ይታያል፡፡ ባለሙያዎች እየመከሩ ያሉት ሞያዎትን ጥለዉ እንዲወጡ ሳይሆን በሙያዎት መስክዎት ለጤና እንክብካቤ ማድረግን እንዲያስቡ እና የሚቻል ከሆነ ጥሩ የመዝናናት እና እንቅስቃሴ ውስጥ የሚትዎትን የፈጠራ ኢነርጂ አቅሞዎትን የሚጨምሩ የስራ መስኮች ላይ መሰማራትን ከግምት እንዲያስገቡ ነዉ፡፡ ሰራተኞቹ በላቀ ሁኔታ ግን አሰሪዎች በየትኛዉም ሞያ ቢሆን የስራ አካባቢ ጤናማ ማድረግ የቤት ስራቸዉን ቢሰሩ ሰራተኞቻቸዉ ጤናማ፤ ደስተኛና ምርታማ ይሆናሉና አሰሪዎች ለዚህ ጉዳይ ልቦናችሁን ብታበረቱት መልካም ነዉ ይላሉ ስራ ደህንነት አክስፐርትመንት ዶክተር ቾስወድ!


ምንጭ ሜዲካል መጽኄጽ መጋቢት -2008 ዓ.ም

 

  

Related Topics