ኢንጂነር ኦታመር ኽርማን አማን በ1879 ማርች 26 ተወለደ

እናስተዋዉቃችዉ

 

ኦትማር አማን

በትዉልድ ስዊዘርላንዳዊ የሆነዉ አሜሪካ እስትራክቸር ኢንጂነር ኦታመር ኽርማን አማን በ1879 ማርች  26 ተወለደ በመስከረም 22 ቀን 1965 ከዚህ አለም በሞት ሲለይ  በዘመኑ ካበረከተቻቸዉ ስራዎች ውስጥ ብርቅዬዎቹ የጆርጅ ዋሽንግተን ድልድይ፤ ቬራዞን -ኖሮዉስ ድልድይ እና ባዬኔ ድልድይ ይገኝባቸዋል፡፡

የኢንጂነሪንግ ዲግሪዉን በስዊዘር ላንድ  ያገኘዉ ኦትማር 1904 ወደ አሜሪካ በመምጣት በርካታ የስራ ጊዜዉን በኒዮርክ አሳልፏል፡፡ ኦቶማር 1905 ሊሊ ስልማ የተባለች ባለቤቱን አግብቶ ሶስት ልጆች ያፈራ ሲሆን በ1933 በሞት ከተለየችዉ በኋላ ሌላ የሀገሩ ልጅ ዜርሊ ቨሞትን በ1935 አግብቷል፡፡ ኦትማር አማን በወደቁ ሁለት ድልድይ ላይ ያቀረበዉ ሙያዊ ትንትና እና ሪፖርቶች በዘርፍ ያለዉ እዉቀት  ስላየባቸዉ ታዋቂነቱ እየጨመረ በ1925  የኒወርክ ወደብ አስተዳደር ኢንጂነሮች ሹም አድርጎ ቀጠረዉ፡፡በወደብ አገልግሎት ውስጥም የጆርጅ ዋሽንግተን ድልድይ ዲዛይነር የማድረግ እና የመቆጣጠር ስራ እድሉን አገኘ  ሀላፊነቱን ሁሉ በሱ ትከሻ ላይ ሆነ በዚህ ወቅት ባሳየዉ ቁርጠኝነት ድልድይ ይጠናቀቃል ከተባለበት ከስድስት ወር ቀድሞ  የተጠናቀቀ ሲሆን ከተያዘለት የ75 ሚሊዮን ዶላር በጀት በ60 ሚሊዮን ብቻ በመጨረስ እዲጠናቀቅ አድርዋል ፡፡ የይህ ጥረቱ ባስገኘለት ከፍተኛ ተቃዋሚነት ከጓደኛዉ ቻርልስ ዊትኒ ጋር በመሆን በ1946 አማን እና ዊትኒ የሚል ድርጅት አቋቁመዉ በርካታ ስራዎች ሰሩ፡፡

ኦትማር አማን በ1964 በሱ ዘመን በ1300 ሜትር የአማችን ከባድ እና እረጅሙን የሰስፔንሽን ድልድይ በኒዉ ዩርክ ለማስመረቅ በቅቷል፡፡ አማን የሚሰራቸዉ ድልድዮች ቀላል እና ርካሽ መሆናቸዉ ባስገኘለት ዝና የኒዉ ዩርክን ከተማ ከሌሎች የአሜሪካ ክፍል የሚያገናኙት 11 ድልድዮች ውስጥ ከግማሽ በላይ የሚሆኑት የእርሱ ስራዎች ናቸዉ፡፡

አማን በሰራቸዉ ስራዎች የተለያዩ ሽልማቶች ያገኘ ሲሆን በ1964 ናሽናል ሽልማቶች ያገኘ  ሲሆን በ1964 ናሽናል ሜዳል ኦፍ ሳይንስ (National  medal of science) ተሸላሚ ለመሆን ሲበቃ በ1968 በስቶኒ በሩክ ዩኒቨርስቲ ደርሚተር በስሙ ተሰይሞለታል፡፡ በተጨማሪም የመቶቸ ዓመት ልደቱን አስመልክቶ የማሰቢያ ሀዉልት በሼራንዛን ናሮዉስ ድልድይ አጠገብ 1979  ቆሞሎታል፡፡

ምንጭ፡- ናሽናል ኮንስትራክሽን መጽሄት

 

  

Related Topics