Notice: Undefined index: title in /home/hawassao/public_html/subpage_articles.php on line 174

Notice: Undefined index: title in /home/hawassao/public_html/subpage_articles.php on line 176

Notice: Undefined index: title in /home/hawassao/public_html/subpage_articles.php on line 216

Notice: Undefined index: title in /home/hawassao/public_html/subpage_articles.php on line 218

በሲጋራ የተጎዳ ሳንባ እንዲያገግም የሚያግዙ ምግቦች

በሲጋራ የተጎዳ ሳንባ እንዲያገግም የሚያግዙ ምግቦች

 

በሲጋራ የተጎዳ ሳንባ እንዲያገግም የሚያግዙ ምግቦች

 

ሲጋራ ማጨስ ስናቆም ሰውነታችን ራሱን መጠገን ይጀምራል።

የብሪታንያ የበሽታ መከላከል እና መቆጣጠር ማዕከል (ሲዲሲ) መረጃ እንደሚያመለክተው፥ ሲጋራ ማጨስ ካቆምን ከሶስት ወራት በኋላ የሳንባችን ተግባር ለውጥ ማሳየት ይጀምራል።

ለአስር አመታት ሲጋራ ማጨስን ካቆምን ደግሞ ከአጫሾቹ ጋር ሲነፃፀር ለሳንባ ካንሰር የመጋለጥ እድላችን በግማሽ ይቀንሳል ይላል ሲዲሲ።

ሲጋራ ማጨስ ስናቆም ሳንባችን ራሱን በራሱ ለመጠገን ቢሞክርም እኛም የተለያዩ ምግቦችን እየተመገብን ልናግዘው ይገባል።

 

ከዚህ በታች የተዘረዘሩት ምግቦችም በሲጋራ የተጎዳ ሳንባን ጤንነት ወደነበረበት ለመመለስ ይረዳሉ ተብሏል።

1. የፍሌቨኖይድ ይዘት ያላቸው ምግቦች

ፍሌቨኖይድ ካትቺን፣ ኢፒቻትቺን፣ ኩረስቲን እና ኬምፕፌሮል የያዙ ምግቦች ለአጫሾችም ሆነ ማጨስ ያቆሙ ሰዎችን ሳንባ ጤንነት ለመጠበቅ ይረዳሉ።

ፍሌቨኖይድስ የሚባሉት በእፅዋት ውስጥ የሚገኙ ቀለማት የካንሰር ህዋሳትን እድገት በመቆጣጠር እና በማጨስ ምክንያት የሚከሰት የዲ ኤን ኤ ጉዳት በማጥፋት የሳንባ ካንሰርን ለመከላከል ይጠቅማሉ።

ካትቺን ከእንጆሪ፣ አረንጓዶ ሻይ እና ጥቁር ሻይ ማግኘት እንችላለን።

ጥራጥሬዎች፣ ሽንኩርት እና አፕል ደግሞ የኩረስቲን ይዘት አላቸው።

በመሆኑም ማንኛውንም የፍሌቨኖይድ ይዘት ያለው ምግብ መውሰድ የተጎዳ ሳንባን ለማዳን ድርሻው ላቅ ያለ ነው።

2. አትክልት እና ፍራፍሬዎች

በካንሰር ኢፒዲሚዮሎጂ፣ ባዮማርከርስ እና ፕረቨንሽን የታተመው ጥናት የተለያዩ ፍራፍሬዎችን እና አትክልቶችን መመገብ አጫሾች በሳንባ ካንሰር እንዳይጋለጡ ያግዛል ይላል።

አጥኚዎቹ ነጥቡ ከምንወስዳቸው የፍራፍሬም ሆነ አትክልቶች ብዛት ሳይሆን የተለያዩ አይነቶች መሆናቸው ላይ ነው ብለዋል።

ይህ ጥናት በቀጣይም በተለያዩ ምርምሮች ሊደገፍ እንደሚገባ ተጠቅሷል።

3. ቫይታሚን ኤ

በቫይታሚን ኤ የበለፀጉ ምግቦች እንደ አስም ያሉ የሳንባ በሽታዎችን ለመከላከል ይረዳሉ ተብሏል።

በካንሳስ ዩኒቨርሲቲ በሪቻርድ ባይቡት መሪነት በተደረገ ጥናት፥ ለሲጋራ ጭስ ተጋላጭ የሆኑ አይጦች የቫይታሚን ኤ እጥረት አጋጥሟቸው ተገኝተዋል።

በዚህ ጥናት እነዚህ የቫይታሚን ኤ እጥረት ያጋጠማቸው አይጦች ለአስም በሽታ የተጋለጡ መሆናቸው ተደርሶበታል።

በጆርናል ኦፍ ኒዩትሪሽን ላይ በታተመው በዚህ የጥናት ውጤት በሲጋራ ውስጥ የሚገኘው ካንሰር አመንጪ ቤንዝዮፓይረን ለቫይታሚን ኤ እጥረት እንደሚያጋልጥ ነው የተረጋገጠው።

በመሆኑም እንደ ፓፓያ፣ ጎመን፣ ዱባ፣ ስኳር ድንች፣ ካሮት፣ ጥቅል ጎመን፣ ኮክ፣ አሳ፣ ቃሪያ እና ጉበት ያሉ ምግቦችን መውሰድ በሲጋራ የተጎዳ ሳንባን ብቻ ሳይሆን ያልተጎዳውንም ጤንነት ለመጠበቅ በጣም ይረዳል።

ምንጭ፦ www.livestrong.com/