የሰውነት ጠረን እንዴት ይፈጠራል ?

የሰውነት ጠረን

 

 Image result for የሰዉነት ጠረን

 

ብዙቻችን በላብ አመንጭ እጢዎች የሚፈጠር የራሳችን የሆነ የተለየ የሰውነት ጠረን አለን ።ይህ የሰውነት ጠረን ጤናማ ቢሆንም በአንዳንድ ሰዎች ላይ ግን ከመጠን ያለፈ ይሆንና ሌሎችንም ሲረብሽ ይታያል

 

   የሰውነት ጠረን እንዴት ይፈጠራል ?

ሰውነታችን ኤክሶክራይን (exocrine) እና አፖክራይን (apocrine) የተሰኙ ሁለት አይነት ላብ አመንጪ እጢዎች ያሉት በመሆኑ ከነዚህ የሚፈጠረው ላብ በግዴለሽነት ወደ ጠረን የመቀየር አቅም አለው ።

ኤክሶክራይን የተባሉት እጢዎች በሁሉም የሰውነታችን ክፍል የሚገኙ ሲሆን፥ የአፖክራይን እጢዎች ደግሞ ጉርምስናን በሚያመላክቱና ፀጉር በሚወጣባቸው አካባቢዎች የሚገኙ ናቸው።

የአፖክራይን እጢዎች ፕሮቲንና ስባማ ንጥረ ነገሮችን ያመነጫሉ፤ ይህም ነው ለሰውነት ጠረን መፈጠር ምክንያት የሚሆነው ።

  

ማድረግ የሚገባን ጥንቃቄ

ዘወትር ውሃን እነደመዳኛነት ተጠቀሙ፣ ንፅህናችሁን ጠብቁ

በሙቀት ወቅት የአየር ማቀዝቀዣዎችን/ቬንቲሌተር/ ተጠቀሙ

እንደ አየር ሁኔታው ስስ ልብሶችን መልበስ ይገባል ፣

ልብሶቻችንን በአጭር ጊዜ ልዩነት መቀየር፣

ቅመም የበዛባቸው ምግቦችን ከመመገብ መቆጠብ፣

ፀረ ባክቴሪያ የሆኑ ሳሙናዎችን መጠቀም

ዲዮድራንት ወይም የላብ ማጥፊያ ከመጠቀማችን በፊት ብብታችን ደረቅ መሆኑን ማረጋገጥ ለችግሩ በመፍትሄነት ይነሳሉ።

ምንጭ፡- ሜዲካል መጽሄት