Notice: Undefined index: title in /home/hawassao/public_html/subpage_articles.php on line 174

Notice: Undefined index: title in /home/hawassao/public_html/subpage_articles.php on line 176

Notice: Undefined index: title in /home/hawassao/public_html/subpage_articles.php on line 216

Notice: Undefined index: title in /home/hawassao/public_html/subpage_articles.php on line 218

በአብዛኛው ለከፋ አደጋ የማይዳርግ የሕመም ዓይነት ነው፡፡

ነስር (Nose bleeds)

 

nosebleeds

 

በአፍንጫ ደም መፍሰስ (ነስር) የምንለው አስደንጋጭ የሆነ፤ነገር ግን በአብዛኛው ለከፋ አደጋ የማይዳርግ የሕመም ዓይነት ነው፡፡

ነስር በሁለት ዓይነት ይከፈላል፡፡

1) ከፊተኛው የአፍንጫችን ክፍል የሚመጣ ነስር (Anterior Nosebleeds)

• ይህ ዓይነቱ የነስር ዓይነት ከ90 በመቶ በላይ ለሚከሰት የነስር ዓይነት ምክንያት ነው፡፡ ከፍተኛው የአፍንጫችን ክፍል የሚመጣን ነስር በቀላሉ መቆጣጠር ወይንም ማቆም ይቻላል፡፡

2) ከኋለኛው የአፍንጫችን ክፍል የሚመጣ ነስር (Posterior Nosebleeds)

• ይህ ዓይነቱ የነስር ዓይንት በአብዛኘው በዕድሜ በገፉ ሰዎች ላይ የሚከሰት ሲሆን ከሌላኛው የተለየ ሕክምና የሚያስፈልገው እና ውስብስብ ነው፡፡

ነስር በአብዛኛው በቅዝቃዜ ወቅት የሚከሰት ሲሆን ከ2 - 10 ዓመትና ከ50 - 80 ዓመት ዕድሜ ክልል ውስጥ ያሉትንም ያጠቃል፡፡

✔ ነስርን የሚያስከትሉ ምክንያቶች ምንድን ናቸው?

• በአፍንጫ ላይ ከውጭ የሚከሰት አደጋ ወይንም አፍንጫ በመጎርጎር ምክንያት

• በተለያዩ የሕመም ወይንም መድኃኒቶች ምክንያት ደም መርጋት አለመቻል

• የደም ግፊት መጨመር ጋር በተያያዘ የሚመጣ ነስር ነው፡፡

✔ የነስር ምልክቶች ምንድን ናቸው?

• በአብዛኛው ደም የሚፈሰው በአንደኛው የአፍንጫ ቀዳዳ ነው፡፡ ነገር ግን ከፍተኛ የሆነ የደም መፍሰስ ካለ በሁለቱም የአፍንጫ ቀዳዳዎች ደም ሊፈስ ይችላል፡፡ እጅግ ከፍተኛ ደም መፍሰስ ካለ ደግሞ በጉሮሮ አድርጎ በአፍ በኩል ሊመጣ ይችላል፡፡

• ከፍተኛ የሆነ ድም መፍሰስ ሲኖር ራስ ማዞር፣ግራ የመጋባት እና ራስ መሳት ሊያስከትል ይችላል፡፡

✔ ነስርን እንዴት ማቆም ይቻላል?

• በመጀመሪያ ራስዎን ማረጋጋት

• ቀጥ ብለው መቀመጥ

• ከጭንቅላትዎ ጎንበስ ማለት (ጭንቅላትን ወደ ላይ ቀና ማድረግ የሚፈሰውን ደም ወደ ጉሮሮ ከማምጣት ባለፈ ጥቅም የለውም)

• ሁለቱም የአፍንጫ ቀዳዳዎች በአውራ ጣትዎ እና በጠቋሚ ታትም ግጥም አድርጎ ለአስር ደቂቃ ይዞ ማቆየት

• በአፍ የሚመጣን ደም መትፋት

• ነስሩ ካቆመ በኋላ አፍንጫዎን አለመነካካት ናቸው፡፡

✔ ነስር ከተከሰተ በኋላ ወደ ሐኪም መሄድ የሚያስፈልገው መቼ ነው?

• አፍንጫዎን ለ10 ደቂቃ ያህል ይዘው ቆይተው ነስሩ የሚያቆም ካልሆነ

• በአጭር ጊዜ ልዩነት በተደጋጋሚ የሚነስርዎ ከሆነ

• ራስ ማዞር ወይንም ራስዎን የሚስቱ ከመሰለዎት

• የልብ ምትዎ የሚጨምር ከሆነ እና ለመተንፈስ ከተቸገሩ

• ደም የሚያስመልስዎ ከሆነ

• በሰውነትዎ ላይ ሽፍታ ከኖረ

• ትኩሳት ካለዎት ናቸው፡፡

✔ ሐኪምዎን ማማከር የሚያስፈልገው መቼ ነው?

• በተደጋጋሚ ነስር የሚያስቸግርዎ ከሆነ

• ከነስር ሌላ ከሌሎች የሰውነት ክፍሎች መድማት የሚኖር ከሆነ

• በቀላሉ የመበለዝ ምልክቶች በሰውነትዎ ላይ ከተገኙ

• ደምን ለማቅጠን የሚጠቅሙ መድኃኒቶችን የሚወሰዱ ከሆነ

• የደም መርጋትን የሚያስተጓጉሉ ማንኛውንም ዓይንት ሕመም ካለዎት

• የኬሞቴራፒ ሕክምና በቅርቡ ወስደው ከነበረ ነው፡፡

✔ነስርን እንዴት መከላከል ይቻላል?

• በአብዛኛው ነስር የሚከሰተው በቀዘቀዘ እና በደረቅ የአየር ንብረት ጊዜ ነው፡፡ ለነስር ተጋላጭ የሆኑ ከሆነ አፍንጫዎ እንዳይደርቅ ቫዝሊን (Petroleum jelly) በመጠቀም ማለስለስ ይችላል፡፡

• አፍንጫዎን በጣትዎ አለመነካካት

• የነስርዎ መነስዔ ከሌላ የጤና ችግር ጋር ተያያዥነት ካለው ሐኪምዎን ማማከር የሚሰጥዎን የጤና ምክር መተግበር

• ሲጋራ ማጤስ አፍንጫን በማድረቅ ለነስር ስለሚዳርግ ማስወገድ ናቸዉ፡፡

ምንጭ፡- በዶ/ር ሆነሊያት ኤፍሬም ቱፈር