Notice: Undefined index: title in /home/hawassao/public_html/subpage_articles.php on line 174

Notice: Undefined index: title in /home/hawassao/public_html/subpage_articles.php on line 176

Notice: Undefined index: title in /home/hawassao/public_html/subpage_articles.php on line 216

Notice: Undefined index: title in /home/hawassao/public_html/subpage_articles.php on line 218

ባለ ሥራብዙው ጉበትና በሽታው(ለሄፕታይተስ ቢ ቫይረስ የቀረበ)

ባለ ሥራብዙው ጉበትና በሽታው(ለሄፕታይተስ ቢ ቫይረስ የቀረበ)

 

Image result for ጉበት

 

ጉበት ከደም ውስጥ መርዛማ ነገሮችን የሚያጣራና ቢያንስ ቢያንስ 500 የሚሆኑ ሌሎች አስፈላጊ ተግባራትን የሚያከናውን ስራ ብዙ አባለ አካል እንደሆነ ይታወቃል። ሄፕታይተስ ወይም የጉበት ብግነት በሽታ የአንድን ሰው ጤንነት በእጅጉ ሊጎዳ የሚችለው እነዚህ ብዙ ስራዎችን ሊያስተጓጉል ስለሚችል። ሄፕታይተስ አልኮል አብዝቶ በመጠጣት ወይም መርዛማ ለሆኑ ነገሮች በመጋለጥ ሳቢያም ሊመጣ ይችላል። ይሁን እንጂ አብዛኛውን ጊዜ ለሄፕታይተስ መንስኤ የሚሆኑት ቫይረሶች ናቸው። ተመራማሪዎች ሄፕታይተስ አምጪ የሆኑ አምስት ቫይረሶችን መለየት የቻሉ ሲሆን ቢያንስ ሌሎች ሦስት ዓይነት ቫይረሶችም ሊኖሩ እንደሚችሉ ግምት አላቸው፡፡

==ሄፕታይተስ==

ሄፕታይተስ የሚያመጡ አምስት ዓይነት ቫይረሶች እንዳሉ የሚታወቅ ሲሆን በስፋት የታወቁት ሄፕታይተስ ኤ፣ ቢ እና ሲ የሚባሉት ሦስቱ የቫይረስ ዓይነቶች ናቸው። ሁሉም የሄፕታይተስ በሽታዎች እንደ ኢንፍሉዌንዛ ያለ የሕመም ምልክቶችን የሚያስከትሉ ሲሆኑ ዓይንን ቢጫ ሊያደርጉ ወይም ላያደርጉ ይችላሉ። ብዙ ሰዎች በተለይም ደግሞ ትናንሽ ልጆች ምንም ዓይነት የሕመም ምልክት አይታይባቸውም። በሽታው ሄፕታይተስ ቢ ወይም ሄፕታይተስ ሲ በሚሆንበት ጊዜ የሕመም ምልክቶች መታየት የሚጀምሩት ጉበት ላይ ከፍተኛ ጉዳት ከደረሰ በኋላ ሊሆን ይችላል።

==ሄፕታይተስ ቢ ቫይረስ==

ከአምስቱ ቫይረሶች አንዱ የሆነው ሄፕታይተስ ቢ ቫይረስ በየዓመቱ ቢያንስ 600,000 ሰዎችን እንደሚገድል መረጃዎች ያሳያሉ፤ ይህም በወባ ምክንያት ከሚሞቱ ሰዎች ጋር መስተካከል የሚችል ነው። ከሁለት ቢሊዮን የሚበልጡ ሰዎች ማለትም ከዓለም ሕዝብ አንድ ሦስተኛ በላይ የሚሆኑት በሄፕታይተስ ቢ ቫይረስ የተጠቁ ሲሆን አብዛኞቹ በወራት ጊዜ ውስጥ ከበሽታው ድነዋል። ይሁን እንጂ 350 ሚሊዮን በሚሆኑት ሰዎች ላይ በሽታው ሥር ሰዶባቸዋል። እነዚህ ሰዎች በቀሪ ሕይወት ዘመናቸው የበሽታው ምልክት ይኑራቸውም አይኑራቸው በሽታውን ወደ ሌሎች አስተላላፊ ይሆናሉ።

ሥር የሰደደ የሄፕታይተስ ቢ ቫይረስ ያለባቸው ሰዎች ገና ከጅምሩ ተገቢውን ሕክምና ካገኙ በጉበታቸው ላይ የሚደርሰውን ከባድ ጉዳት ማስቀረት ይችላሉ። ይሁን እንጂ ሄፕታይተስ ቢ ቫይረስ ለዚሁ ተብሎ በሚደረግ ልዩ የደም ምርመራ ካልሆነ በስተቀር ሊታወቅ ስለማይችል አብዛኞቹ ሰዎች በበሽታው እንደተያዙ እንኳ አያውቁም። በተለምዶ የሚደረገው የጉበት ምርመራ እንኳ የበሽታውን ምልክት ላያሳይ ይችላል። በመሆኑም ሄፕታይተስ ቢ ቫይረስ ያለምንም ማስጠንቀቂያ ለከፋ ጉዳት የሚዳርግ ድምጽ አልባ ገዳይ በሽታ ሊባል ይችላል። በአንድ ሰው ላይ ግልጽ የሆኑ የሕመም ምልክቶች የሚታዩት በቫይረሱ ከተያዘ ከአሥርተ ዓመታት በኋላ ሁሉ ሊሆን ይችላል። በዚህ ወቅት ግን ሕመሙ ተባብሶ ስሮሲስ የተባለ የጉበት በሽታ ወይም ካንሰር ወደ መሆን ደረጃ ሊደርስ ይችላል። ሄፕታይተስ ቢ ቫይረስ ከአንዱ ወደ ሌላ የመተላለፍ አቅሙ ኤድስ አምጪ ከሆነው ከኤች አይ ቪ ቫይረስ 100 እጥፍ ይበልጣል። በምላጭ ጫፍ ላይ ያለ የደም ቅንጣት እንኳ ሄፕታይተስ ቢ ቫይረስ ሊያስተላልፍ የሚችል ሲሆን የደረቀ የደም ጠብታ ለአንድ ሳምንት ወይም ከዚያ ለሚበልጥ ጊዜ ቫይረሱን የማስተላለፍ አቅም ሊኖረው ይችላል፡፡

==የሚታዩ ምልክቶች==

ዐይንና ቆዳ ቢጫ የመሆን(Jaundice)፣ የሻይ መልክ ያለው ጠቆር ያለ ሽንት፣ ከፍተኛ የሰውነት ድካም ስሜት፣ የሆድ ሕመም፣ ማቅለሽለሽና ማስመለስ ናቸው፡፡

ሄፕታይተስ ቢ ቫይረስ በበሽታው በተያዙ ሰዎች ደም እንዲሁም ከብልታቸው በሚወጡ ፈሳሾች ውስጥ ይገኛል። እንደነዚህ ያሉት ፈሳሾች ቫይረሱን የመከላከል አቅም በሌለው ሰው ሰውነት ውስጥ በሚገቡበት ጊዜ ቫይረሱ ይዛመታል። ቫይረሱ በሚከተሉት መንገዶች ሊተላለፍ ይችላል፦

● በወሊድ ወቅት (በቫይረሱ ከተያዘች እናት ወደ ልጅ)

● በተገቢው መንገድ ከጀርም ያልጸዳ የሕክምና፣ የጥርስ፣ የንቅሳት ወይም ሰውነትን ለመብሳት የሚያገለግል ሌላ መሣሪያ

● መድኃኒት ለመስጠት የሚያገለግል መርፌን፣ ምላጭን፣ የጥፍር መሞረጃን ወይም መቁረጫን፣ የጥርስ ብሩሽን ወይም በቆሰለ የአካል ክፍል በኩል የደም ቅንጣትን ሊያስተላልፍ የሚችል ማንኛውንም ሌላ መሣሪያ በጋራ መጠቀም የለብንም፡፡

==ሕክምናው==

በባለሙያተኞች የቅርብ ክትትልና እርዳታ የሚሰጥ ነው፤ ሕክምናው በሽተኛው እንደሚገኝበት የአስጊነት ደረጃ የሚሰጥ ነው፤ ነገር ግን አንድ ሰው እንደ አዲስ በመጀመሪያ በሚለከፍበት ጊዜ በቂ ፈሳሽ፣ ተመጣጣኝ ምግብና ዕረፍት ሲያገኝ የማገገም ሁኔታው የተሻለ ይሆናል፡፡

==የሄትታተስ ቢ በሽታ እውነታዎች==

• ሄትታተስ ቢ በቫይረስ ልክፍት አማካኝነት የሚከሰት የጉበት በሽታ ሲሆን በሰዎች ላይ ስር የሚሰድ ዘላቂ በሽታ ያስከትላል፡፡

• ቫይረሱ በበሽታው ከተለከፉ ሰዎች ደምና ሌላም የሰውነት ፈሳሽ ጋር በሚደረግ ንክኪ ይተላለፋል፡፡

• ከሰው ወደ ሰው የመተላለፍ እድሉ ከኤች አይ ቪ ኤድስ ከ50 እስከ 100 እጥፍ ይበላጣል፡፡

• በክትባት አማካኝነት ሄትታተስ ቢን መከላከል ይቻላል፡፡

ማስጠንቀቂያ! ሄትታተስ ቢ ለሕይወት አስጊ የሆነ የጉበት በሽታ ነው፤ በዓለም ላይ በከፍተኛ ደረጃ ሰፍኖ የሚገኝ በሽታ ነው፤ በአመት በሄትታተስ ቢ ጦስ ምክንያት የሚሞተው ሰው ቁጥር 600,000 እንደሆነ መረጃዎች ያሳያሉ፡፡ በቫይረሱ የተለከፉ ሰዎች ስር የሰደደ(chronic) ከሆነባቸው ሲውል ሲያድር ወደ ጉበት ብግነትና የጉበት ካንሰር በመቀየር ለህልፈተ ህይወት ይዳርጋል፡፡

ምክር፡- የአንድ ሰው በሽታ ተከላካይ ሕዋሳት ቫይረሱን በስድስት ወር ጊዜ ውስጥ ከሰውነት ማስወገድ ካልቻሉ በሽታው ሥር እንደ ሰደደ ይቆጠራል። በቫይረሱ ከተያዘ ሰው ደም በሚፈስበት ጊዜ አንድ እጅ በረኪናን በ10 እጅ ውኃ በመበጥበጥ ጓንት አድርጎ የፈሰሰውን ደም ወዲያውኑ በሚገባ ማጽዳት ያስፈልጋል።

ምንጭ ፡- ሰርቫይቫል 101/Survival