የሳይንስና ቴክኖሎጂ ተቋማት ሀገሪቱ የተያያዘችውን ልማት

 የሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ተቋማት

 

የሳይንስና ቴክኖሎጂ ተቋማት ሀገሪቱ የተያያዘችውን ልማት ለማፋጠን ከሳይንስና ቴክኖሎጂ ጋር ተያያዥነት ያላቸው የሚኒስቴር መስሪያ ቤቶችና በስራቸው የሚገኙ ተጠሪ ተቋማት፣ የሳይንስና ቴክኖሎጂ መረጃ ማዕከል የአምስት አመት ስትራቴጅክ እቅድ 64 የጥራት መሰረተ-ልማት ተቋማት፣ የጨረራ ባለስልጣን፣ የአዕምሯዊ ፅ/ቤት እና ፖሊሲ አውጭ አካላት ናቸው፡፡ እነዚህ አካላትን ፈጣን፣ ግልጽ እና ተጠያቂነት የሰፈነበት አሰራር በማስፈን የበኩላቸውን ይወጣሉ፡፡ የሳይንስና ቴክኖሎጂ መረጃ ማዕከል ከነዚህ አካላት ጋር የሚኖረው ግንኙነት በአብዛኛው አገልግሎት ከመስጠት እና ከመቀበል ጋር የተያያዘ ነው፡፡

 

አብዛኞቹ ተቋማት የመንግስት አገልግሎት ሰጪ ተቋማት እንደመሆናቸው ተቋሙ ለሚፈልጋቸው ግልጋሎቶች ቀልጣፋ አሰራር በመዘርጋት ፈጣን የሆነ አገልግሎት መስጠት ይጠበቅባቸዋል፡፡ በተጨማሪ ተቋሙ ከሚሰራቸው ስራዎች ጋር ተያይዞ የሚፈልጋቸውን መረጃዎች በአግባቡ መስጠት እንዲሁም ትብብር በሚያስፈልግባቸው ቦታዎች ሁሉ የሀገሪቱን ህዳሴ እውን ማድረግ ይሆናል፡፡ በሌላ በኩል ይህ ተቋም ለእነዚህ ባለድርሻዎች የሚሰጠው አገልግሎት የሚፈልጉትን በአግባቡ የተሰበሰበ፣ የተደራጀና የተተነተነ የሳይንስና ቴክኖሎጂ መረጃ መስጠት እንዲሁም የአሰራር ሁኔታቸውን ለማሻሻል እና ለማቀላጠፍ እንዲችሉ እና በሳይንስና ቴክኖሎጂ የተደገፈ እንዲሆን የሚረዳቸውን የሳይንስ እና ቴክኖሎጂ መረጃ ማቅረብ ነው፡፡

 

በወሰዱት የሳይንስ እና ቴክኖሎጂ መረጃ ውጤት ላይ ግብረ-መልስ መስጠት እና ቀጣይነት ያለው ግንኙነት በመፍጠር በትብብር መስራት እንዲሁም ለፖሊሲ አውጪ አካላት ግብዓት ሊሆኑ የሚችሉ ጥናቶችን ማከናወን፤ ለምሳሌ የሃገሪቱን የሳይንስ እና ቴክኖሎጂ አመልካች ጥናት ማከናወን የመሳሰሉትን ያጠቃልላል፡፡ የሳይንስና ቴክኖሎጂ መረጃ ማዕከል የአምስት አመት ስትራቴጅክ እቅድ 65 እነዚህ አካላት በተቋሙ ላይ እምብዛም ፍላጎት ባይኖራቸውም ግን ከፍተኛ የሆነ ተጽእኖ የመፍጠር ሃይል አላቸው፡፡ ምክኒያቱም የተቋሙ ስራ የተሳካ ለማድረግ እነርሱ የሚሰጡት ግልጋሎት ወሳኝ ነው፡፡ ሀይል ስላላቸው የተቋሙ ስራ በእነርሱ ተጽእኖ ስር መውደቁ አይቀሬ ነው፡፡ ስለሆነም ለእነዚህ አካላት በቂ የሆነ ግንዛቤ በማስጨበጥ በተቋሙ ስራ ላይ ፍላጎት እንዲያሳድሩና ተባባሪ ማድረግ ተገቢ ይሆናል፡፡ ለዚህም ተከታታይነት ያለው የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ በመፍጠር ማወያየት ያስፈልጋል፡፡

 

  ኢንዱስትሪዎች

ኢንዱስትሪዎች የሀገሪቱ የቴክኖሎጂ ሽግግር ማዕከላት እንደመሆናቸው የሚያመርቱት ምርት በአለም ገበያ ተወዳዳሪ ለማድረግ የሳይንስ እና ቴክኖሎጂ መረጃ ያስፈልጋቸዋል፡፡ ኢንዱስትሪዎች ሲባል ከፍተኛ፣መካከለኛና ጥቃቅንና አነስተኛ ኢንዱስትሪዎች ሆነው በግብርና ዘርፍ የተሰማሩ፣በማኑፋክቸሪንግ ዘርፍና በአገልግሎት ዘርፍ የተሰማሩ ተቋማት ናቸው፡፡ ኢንዱስትሪዎች ከከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የሚወጡ ባለሙያዎች የተሻለ እድል አግኝተው ያላቸውን እውቀት በተግባር ለመግለጥ እንዲሁም የፈጠራ ክህሎታቸውን የሚያዳብሩባቸው ቦታዎች ናቸው፡፡

 

በመሆኑም እነዚህ ኢንዱስትሪዎች የተቋሙ ባለድርሻዎች ናቸው፡፡ ስለዚህ ማዕከሉ የፍላጎት ትንተና (need analysis) በመስራት ያለባቸውን የቴክኖሎጂ ክፍተት ለመሙላት የሳይንስ እና ቴክኖሎጂ መረጃ ይሰጣል፡፡ ከትምህርት እና ከምርምር ተቋማት የሚመጡ ችግር ፈቺ የሆኑ ምርምሮችን በማቅረብ በእነዚህ ተቋማት ወደ ተግባር የሚቀየሩበትን ሁኔታ የሳይንስና ቴክኖሎጂ መረጃ ማዕከል የአምስት አመት ስትራቴጅክ እቅድ 66 ያመቻቻል፡፡

 

በተጨማሪም በወሰዱት መረጃ ውጤት ላይ ግብረ- መልስ መስጠት እና የማሻሻያ ሃሳቦችን ያቀርባል፡፡ በተጨማሪ ከዩኒቨርሲቲ ኢንዱስትሪ ሊንኬጅ ጋር በተያያዘ በተሰራው የፍላጎት ትንተና የኢንዱስትሪዎች የቴክኖሎጂ ክፍተት ታይቶ ዩኒቨርስቲዎች በዚህ ላይ ትኩረት እንዲያደርጉ እንዲሁም ሁሉንም ዩኒቨርሰቲዎች የምርምር ውጤቶች ወደ ማዕከሉ ዳታ ቤዝ በማስገባት ኢንዱስትሪዎች እንዲያገኙት (access) ማድረግ እንዲችሉ ይሆናል፡፡ እነዚህ ተቋማት በማዕከሉ ስራ ላይ ከፍተኛ ፍላጎት ያላቸው ሲሆኑ ነገር ግን አነስተኛ የሆነ ሃይል ያላቸው ናቸው፡፡ በተጨማሪም የተቋሙ ወሳኝ ባለድርሻዎች ስለሆኑ ትኩረት ይሰጣቸዋል፡፡ በአንጸሩ ደግሞ ኢንዱስትሪዎቹ ያገኙዋቸውን የሳይንስ እና ቴክኖሎጂ መረጃዎች በአግባቡ መጠቀም እና የደረሱበትን ውጤት ለተቋሙ ማድረስ ይጠበቅባቸዋል፡፡ ማዕከሉም ተከታታይነት ያለው የግንዛቤ የማስጨበጫ መድረኮችን በማዘጋጀት እንዲሁም ስልጠናዎችን በመስጠት ያግዛል፡፡

 

ምንጭ፡- አዲስ ዘመን ጋዜጣ

 

  

Related Topics