በአገራችን ኢትዮጵያ ከሶስተኛዉ መቶ ክፍለ ዘመን ከንጉሥ ኢዛና ዘመነ መን

ንብ ማነብ

 

Image result for የንብ መንጋ

 

በአገራችን ኢትዮጵያ ከሶስተኛዉ መቶ ክፍለ ዘመን ከንጉሥ ኢዛና ዘመነ መንግሥት ጀምሮ የንብ ማነብ ሥራ ይታወቅ ነበር፡፡ ከትዉልድ ትዉልድ ለዘመናት ሲተላለፍ የነበረዉ ባሕላዊ የማነብ ዘዴ ይህ ነው የሚባል የዉጪ ሙያ እርዳታ ሳይታከልበት ማር ይመረት ነበር፡፡ በ1960ዎቹ ውስጥ የኢትዮጵያ መንግሥት በዘመናዊ ቀፎ ላይ ትኩረት ያደረገ የንብ ማነብ ልማት ጀመረ፡፡ እነዚህ ዘመናዊ ቀፎዎች የማር ምርቱን ጥራት መጠበቅና የተሻለ ብዛት ማስገኘት ብቻ ሳይሆን የማር ምርቱ መድረስ አለመድረሱን ማወቅ ያስችላሉ፡፡

 

 

በኢትዮጵያ በባህላዊ ቀፎዎች የሚጠቀሙ ብዙ አናቢዎች ምርትና ምርታማነት በጣም ዝቅተኛ ነዉ፡፡ በዓመት ከ5-6 ኪሎ የሚሆን ማር ብቻ ይቆርጣሉ፡፡ የተሻሻሉ ወይም ዘመናዊ ቀፎዎች ደግሞ ከ15-40 ኪሎ ማር ድረስ ሊያስገኙ ይችላሉ። በ1993 አጋማሽ ላይ ብሔራዊ የማር ምርት በአመት እስከ 24,600 ቶን ይደርሳል ተብሎ ተገምቷል። ግምቱ የተወሰደዉ 7.5 ሚሊዮን የ’ሚሆኑ ባህላዊ ቀፎዎችና 20,000 ከሚሆኑ የተሻሻሉ ዘመናዊ ቀፎዎች 65 ፐርሰንት እና 75 ፐርሰንት እንደ ቅደም ተከተላቸው የሚደርስ ምርታማነትን መሰረት በማድረግ ነዉ፡፡ በአገሪቱ አብዛኛዉ ክፍል፣ በጣም ቆላማ ወይም በጣም ደጋማ ከሆኑት አከባቢዎች በስተቀር ንብ ማነብ እንደ ጓሮ ሥራ የሚወሰድ ተግባር ነዉ፡፡

 

የኤክስቴንሽን ሰራተኞች የስልክመስመር ካላቸው የኢንተርኔት ግንኙነትእንዲያገኙ አመቻችቷል፡፡ የኢንተርኔትግንኙነት ለማግኘት አስቸጋሪ በሆነባቸውወረዳዎች የድረገፁ ግልባጭ ወይም ቅጂበDVD እንዲደርሳቸው ተደርጓል፡፡

 

ክህሎትን ማዳበር

 

በወረዳ ደረጃ የሰለጠነ የሰው ሃይል አናሳ በመሆኑ ከምርታማነት ማሻሻያና ገበያ ስኬት ፕሮጀክት ውጪ ካሉ አሰልጣኞች ጋር ትስስር እንዲፈጠር ተደርጓል፡፡ የገበያ ተሞክሮ ባላቸው መሪ አርሶአደሮች (በአፅቢ) ከንግድ ኩባንያ ባልደረቦች (በአፅቢና ጎማ) ከሆለታ የንብ ምርምር ማዕከል (አላባና ጎማ)፣ከአንዳሳ ምርምር (ቡሬና ፎገራ)፣ የግል አማካሪዎች ከአድአና ከምርታማነት ማሻሻያና የገበያ ስኬት ፕሮጀክት አባሎች ጋር ትስስር ተፈጥሯል፡፡ቀደም ብሎ ከተደረጉት ስልጠናዎች በተቃራኒው ይህ የቅድሚያ ስልጠና በመስክ ስልጠና እንዲታገዝ የተደረገና ለተጨማሪ አርሶ አደሩ እውቀቱንና ክህሎቱን ለማካፈልናለማስፋት የሚችልበት የመስክ ጉብኝትዝግጅት ተደርጓል፡፡ በንብ ማነብ ዘዴዎችላይ የማሰልጠኛ ጽሁፎችና መመሪያዎች ተዘጋጅተው ጥቅም ላይ ውለዋል፡፡

እነዚህ የስልጠና ጽሁፎች ከግብርናና ገጠር ልማት ሚንስቴር ምርጥ ተሞክሮዎች ውስጥ አብዛኛውን ክፍል የያዙ ናቸው ፡፡አሳታፊ በሆነ የእሴት ሰንሰለት ማበልፀጊያ ዘዴ የስራ ባልደረቦቹን ዝግጁ ለማድረግ በአሳታፊና ገበያ ተኮር የኤክስቴንሽን መመሪያዎችን አጠቃሎ ይዟል፡፡

 

የተሻሻሉ ዘመናዊ ቀፎዎች

አጠቃቀም በመሰረቱ ሁለት ዓይነት የተሻሻሉ ቀፎዎችን መጠቀም ይቻላል፡፡ እነሱም ባለፍሬም ቀፎ ወይም ዘመናዊ ቀፎና የርብራብ (Top bar) ወይም ሽግግር ቀፎ የሚባሉ ናቸው፡፡ ባለፉት ጊዜያት ዘመናዊ ቀፎን መጠቀም በስፋት ተነግሮለታል።ይህም ሆኖ የንግድ አገልግሎት ሰጪዎች በሌሉበት ቦታ ፕሮጀክቱ ከዘመናዊ ቀፎዎች ይልቅ የሽግግር ቀፎዎችን መጠቀምን ሲያበረታታ ቆይቷል፡፡የተሻሻሉ ቀፎዎችን ለማስተዋወቅ በግብርናና ገጠር ልማት ቢሮዎች፣መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች፣ በምግብዋስትና ፕሮግራሞች አማካኝነት የብድርአገልግሎቶች ተሰጥተዋል፡፡ እነዚህድርጅቶችና ፕሮግራሞች ብድሩን በቀጥታ ወይም በአነስተኛና ጥቃቅን የብድር ተቋማት አማካኝነት ይሰጡ ነበር፡፡በተጨማሪም ፕሮጀክቱ በአላባ፣ በአፅቢናበጎማ እንደሚፈለገው የቀፎ ብዛትና እንደብድሩ የአመላለስ ሁኔታ እየታየ በማይክሮ ፋይናንስ በኩል ብድር እንዲሰጥ አመቻችቷል፡፡

 

የቀፎዎች ማስቀመጫ ቦታ አያያዝ

ቀደም ሲል ቀፎዎች የሚሰቀሉት ለንብ የሚሆን የቀስም ተከል ባለበት አካባቢነበር፡፡ ይህ ዘዴ ለዘመናዊ ቀፎዎችም ተሞክሮ ነበር፡፡ ይሁንና በንቦቹ ላይበዱር እንሰሳት፣ በአእዋፋት፣ በጉንዳን፣በተባይና በመሳሰሉት የመጠቃት አደጋ ከመድረሱም በላይ ለስርቆት የተጋለጡ ነበሩ፡፡ ለምሳሌ በአፅቢ በማገገም ላይበነበሩ ጫካዎች በተሰቀሉ ቀፎዎች ውስጥ የነበሩ ንቦች በጥቁር ወፎች ጥቃት ደርሶባቸዋል፡፡ ከዚህም የተነሳ ባሁኑ ሰዓት ቀፎዎች ከቤት ጓሮ ወይም በቤት ዙሪያ ጥላ ባለበት አካባቢ ይቀመጣሉ።

 

በሽታና ተባይን መከላከል

በንቦችና ቀፎዎች አያያዝ ውስጥ ከሚጠቀሱት ዋና ዋና ተግባሮች አንዱ ተገቢውን የንፅህና አሰጣጥ መንገዶችን መከተል ነው፡፡ ንፅህና ከተለያዩ ፈንገሶችና ከሰም በልትል ሊከላከልልን ችሏል፡፡

ቀፎ መሥራት አብዛኛውን ጊዜ ዘመናዊ ቀፎዎች የሚመረቱት በመካከለኛ ደረጃ ላይ በሚገኙ ኩባንያዎች ነው፡፡ የቀፎዎቹን ጥራት የሚቆጣጠሩት የግብርናና ገጠር ልማት ቢሮዎች ናቸው ፡፡ እነዚህ ዘመናዊ ቀፎዎች ግን ለአርሶ አደሩ ውድ ሆነው ተገኝተዋል፡፡ ዋጋቸው ከተጨማሪ መገልገያዎች ውጪ ብር 550.00 ይደርሳል፡፡ ስለዚህ የአካባቢ አናፂዎችና ፈጠራን የሚያበረታቱ አርሶ አደሮች ከአካባቢው በሚገኝ ቁሳቁስ የርብራብ ቀፎ ወይም ቶፕ ባር ቀፎ የሚባለውን መስራት እንዲችሉ ስልጠና ተሰጥቷቸዋል፡፡ በዚህም በወረዳ ደረጃ ተጨማሪ ገቢ ሊያስገኝ የሚችል የስራ መስክ ሊፈጠር ችሏል፡፡

 

የተጣራ ማር ማምረት

 በመጨረሻም አብዛኛው ባህላዊ ቀፎ ማር ሲቆረጥባቸው ጉዳት በሚያስከትልና ጥራት በሌለው መንገድ ስለሚቆረጥ ማሩ ከሰፈፍና ከእጭ ጋር የተደበላለቀ ነው። ዘመናዊ ቀፎ መጠቀም ከዚህ ጉዳት የሚከላከልና በቀላሉ ማሩን በመቁረጥ ንፁህ ምርት ማግኘት ያስችላል፡፡

 

የንብ ቀሰም ዕፅዋት አያያዝ

የንብ ቀሰም ዕፅዋት የሚገኘው በተፈጥሮከበቀሉ ወይም ሰው ተክሎ ካበቀላቸውዕፅዋቶች ነው፡፡ የንብ ቀሰም ዕፅዋትአቅርቦት ከቦታቦታናከወቅት ወቅት በእጅጉሚለያይና የተስተካከለ የአቅርቦት ስልት ለመንደፍ የዳሰሳ ጥናት የሚያስፈልገው ነው፡፡ በተለያዩ አካባቢዎችና ወረዳዎችለምሳሌ በአፅቢና በፎገራ በተደረጉ የግጦሽመሬት ማሻሻያ ድጋፎች የተነሳ የአበባምርቶችና የተፈጥሮ አበቦች የአበቃቀልወቅታቸውን ጠብቀው የሚበቅሉትእንዲስፋፉ ረድቷል፡፡ ፕሮጀክቱ በእነዚህየአበባ ክምችቶች አካባቢ የሚኖሩ አርሶ አደሮችን የዚህ ዕድል ተጠቃሚ እንዲሆኑአበረታቷል፡፡ ከተተከሉ ዕፅዋቶች የሚገኘው የንብ ቀሰም ዕፅዋት አብዛኛውን ጊዜ ለከብት መኖ ከተተከሉ ተክሎች ወይም ለምግብነት ከሚውሉ ተክሎች የሚገኝ ነው፡፡ ለዚህ ጥሩ ምሳሌ የሚሆነው የአልፋ አልፋ ተክል፣ ሴስፓንያ ሊዩካኒያ የመሳሰሉት ሲሆኑ ከምግብ ተክሎች ደግሞ የቡና ተክል፣ የቅባት እህሎችና የፍራፍሬ ዛፎች የመሳሰሉት ናቸው፡፡

ምንጭ፡- አዲስ ዘመን ጋዜጣ