Notice: Undefined index: title in /home/hawassao/public_html/subpage_articles.php on line 174

Notice: Undefined index: title in /home/hawassao/public_html/subpage_articles.php on line 176

Notice: Undefined index: title in /home/hawassao/public_html/subpage_articles.php on line 216

Notice: Undefined index: title in /home/hawassao/public_html/subpage_articles.php on line 218

ለጤናችን ችላ ማለት የማይገቡን 10 የበሽታ ምልክቶች

 

 ለጤናችን ችላ ማለት የማይገቡን 10 የበሽታ ምልክቶች

 

Image result for madicale

 

እንደ የደረት ሕመምና ከባድ የሆድ ቁርጠት የመሰሉ የበሽታ ምልክቶች ካሉብን ወዲያውኑ ሕክምና ማድረግ እንዳለብን ብዙዎቻችን እናውቃለን፡፡ ይሁን  እንጂ፣ ሌሎች የበሽታ  ምልክቶች የሕመምና እርዳታ እንደሚያስፈልጋቸው እናውቅ ይሆናል፡፡ ቀጣዮቹ የበሽታ ምልክቶቹ ሌላው ቢቀር የጤና ባለሙያ ማማከር እንዳለብዎት የሚጠቁሙ ናቸው፡፡ የተወሰኑት ይበልጥ አሳሳቢ ቢሆኑም፣ ችላ መባል የለባቸውም፡፡

    1. ባልታወቀ ምክኒያት የሚያጋጥም የክብደት መቀነስ

ክብደት ለመቀነስ ምንም አይነት ሙከራ ሳያደርጉ ክብደትዎ መቀነሱን ሲረዱ ደስ ይልዎት ይሆናል፡፡ ይህንና፣ የጤንነት ችግር እንዳለብዎት ጠቋሚ ሊሆን ይችላል፡፡ ባለፉት ስድስት ወራት ከክብደትዎ ላይ 10  በመቶ ከቀነሱ ሐኪምዎን ማማከር ይኖርብዎታል፡፡ በሌላ አነጋገር፣ 68 ኪሎ ግራም ከቀነሱ የጤና ባለሙያ ዘንድ መሄድ ይኖርብዎታል፡፡

ባልታወቀ ምክኒያት የሚያጋጥም የክብደት መቀነስ በተለያየ የጤና ችግሮች ሳቢያ ሊከሰት ይችላል፡፡ ለእነኝህ መካከል የታይሮይድ እጢ ከልክ በላይ መስራት፣  የመደበር ስሜት፣ ጠጉበት በሽታ፣ ካንሰር፣ ኤች.አይ.ቪ/ኤድስ፣ እንዲሁም ሰውነታችን ንጥረ ምግቦችን በአግባቡ እንዳይቀበል የሚያደርጉት ሕመሞች ተጠቃሾች ናቸው፡፡

    1. ቶሎ የማይጠፋ ወይም ከባድ ትኩሳት

ትኩሳት በሽታ ባይሆንም፣ ብዙ ጊዜ ሕመም እንዳለብን ጠቋሚ ምልክት ነው፡፡ አብዛኛውን ጊዜ ትኩሳት ሰውነታችን የተለመደ የቫይረስ ወይም የባክቴሪያ ኢንፌክሽንን እየተፋለመ ለመሆኑ ጠቋሚ ነው፡፡ ይሁን እንጂ፣ ለሶስት ወይም ከዚያ በላይ ለሆኑ ቀናት  ሊጠፉ ያልቻለ 38.9 ዲግሪ ሴንቲ ግሬድ የሰውነት የሙቀት መጠን ካላብዎት ሀኪሙዎን ማማከር ይኖርቡዎታል፡፡ በተመሳሳይ መልኩ ከ40 ዲግሪ ሴንቲ ግራም የበለጠ የሰውነት የሙቀት መጠን ወይም ከባድ ሕመም ካለብዎት የጤና ባለሙያ ማማከር ይኖርብዎታል፡፡

የቅስሙ ተፈጥሮ መከላከያ ስርዓት ችግር ካለብዎት ወይም የበሽታ መከላከያ ስርዓትዎን የሚገድብ መድኃኒት የሚወስዱ ከሆነ ትኩሳት በሽታ  እንዳለብዎት ጠቋሚ ምልክት ላይሆን ይችላል በእንዲህ አይነቱ ሁኔታ ሕመም እንዳለብዎት የሚጠቁመውን ምልክት ለማወቅ ሐኪምዎን መጠየቅ ይኖርብዎታል፡፡

    1. የትንፋሽ ማጠር

በታፈነ አፍንጫ ወይም በአካል ብቃት እንቅስቃሴ ከሚያጋጥመን  የበለጠ የትንፋሽ እጥረት ከደረሰብን የጤና ችግር እንዳለብን አመላካች ሊሆን ይችላል፡፡ መተንፈስ ካልቻሉ፣ ትንፋሽዎ ቁርጥ ቁርጥ ካለ፣ አሊያም ካቃተቱ ያለምንም ማመንታት የጤና ባለሙያ ዘንድ መሄድ ይኖርብዎትታል፡፡ ሲደክምዎትም ሆነ ሳይደክምዎት ጋደም ብለው የትንፈሽ ማጠር ካጋጠምዎትም እንዲሁ ያለምንም መዘግየት  ሐኪም ዘንድ መሄድ እንዳለብዎት ጠቋሚ ነው፡፡

 ለትንፋሽ ማጠር ምክኒያት ከሆኑት መካከል ስር የሰደደ የሳምባ በሽታ፣ ስር የሰደደ ብሮንካይቲስ፣ አስም፣ የሳምባ ምች፣ በሳምባ ውስጥ የደም መርጋት፣ እንዲሁም የተለያዩ የልብ ሕመሞች ይገኙባቸዋል፡፡

    1. ባልታወቀ ምክንያት የመጸዳዳት ልምድ መለወጥ

ብዙ ሰዎች መጸዳዳትን በተመለከተ ‘’ ጤናማ     ‘’ የሚባለው ምን አይነት ልምድ እንደሆነ ግራ ይገባቸዋል፡፡ የመጸዳዳት ልምድ ከሰው ሰው የተለያየ ቢሆንም፣ በቀን ሶስት  እስከ ሳምንት ሶስት ጊዜ መጸዳዳት ጤናማ ተደርጎ ሊወሰድ ይችላል፡፡

ከዚህም ቀጥሎ  የሰፈሩትን የመሰሉ ያልተለመዱ ወይም ባልታወቀ ምክኒያት የሚያጋጥሙ ለውጦችን ካስተዋሉ ሐኪም ዘንድ መሄድ ይኖርብዎታል፡፡

    • ደም የቀላቀለው ዓይነ ምድር
    • አንድ ሳምንት የዘለቀ ተቅማጥ
    • ከሶስት ሳምንታት በላይ የቆየ የሆድ ድርቀት
    • ባልታወቀ ምክኒያት ተዳጋጋሚ የመጸዳዳት ፍላጎት
    • ጥቁር ወይም ሬንጅ መሰል ዓይ-ምድር

የመጸዳዳት ልምድ ለውጥ እንደ campylobacter  ወይም  salmonella የመሰለ የባክቴሪያ ኢንፌክሽን፣  የቫይረስ ኢንፌክሽን፣ አሊያም የጥገኛ ተውሳክ ኢንፌክሽን ለመኖሩ ጠቋሚ ሊሆን ይችላል፡፡

    1. ቅዥት (  )

ቅዥት ድንገተኛ ከባድ ብዥታና ከደስታ ወደ ጭንቀት የመሰለ ፈጣን  የአእምሯዊ ሁኔታ ወይም ስሜት ለውጥ ነው፡፡ ይህን የበሽታ ምልክት  ያስታዋሉ የቅርብ ጓደኞች ወይም የቤተሰብ አባላት ሊሆኑ ይችላሉ፡፡  በቀጣይነት ከሰፈሩት ችግሮች መካከል አንዱ ካጋጠምዎት ወዲያውኑ ሐኪም ዘንድ መሄድ ይኖርብዎታል፡፡

    • ድንገተኛ የሐሳብ መብዛት
    • ጊዜንና  ቦታን ማማታት
    • ድንገተኛ የባህሪይ ወይም የጸባይ ለውጥ (ለምሳሌ፣ ጠበኛነት)
    • የማስተዋል ወይም የማስታወስ ድንገተኛ ችግር

የጸባይ ወይም መሰል ለውጥ የኢንፌክሽን፣ የደም ማነስ፣ የስኳር ሕመም፣ የስነ-አእምሮ ችግር፣ አሊያም የሚወስዱት መድኃኒት ውጤት ሊሆን ይችላል፡፡

    1. ድንገተኛ ከባድ ራስ ምታት

ራስ ምታት የተለመደ ከመሆኑም ሌላ፣  ቸብዛኛውን ጊዜ አሳሳቢ ነገር አይደለም፡፡ ይሁን እንጂ፣ ድንገተኛ ከባድ እራስ ምታት አሳሳቢ የጤና ችግር ለመኖሩ አመልካች ሊሆን ይችላል፡፡ ከዚህ ቀጥሎ የተቀመጡት ምልክቶች ካጋጠምዎት ወዲያውኑ የሐኪም እርዳታ ይጠይቁ፡፡

    • በትኩሳት መዞር ባቃተው አንገት፣ ነሽፍታ፣ በብዥታ ወይም በሚጥል በሽታ የታጀበ ራስ ምታት
    • 55 አመት ከሞላዎት በኃላ ያልተለመደ አይነት ራስ ምታት የመጨረሻው ነጥብ በመካከለኛው የዕድሜ ክልል ውስጥ ሲገቡ እምብዛም የማያጋጥም ህክምና ያለው የአናት፣  የአንጎልና የዓይን ደም ቅዳዎች  መጉረብረብ (temporal arteritis  ) እንዳለብዎት ሊያመለክት ከሚችሉ ሌሎች ምክኒያቶች መካከል የአንጎል እባጭ ወይም የደም ቅዳ ያልተለመደ እብጠት (aneurysm) ተጠቃሾች ናቸው፡፡
    1. ድንገተኛ ድካም ፣ እንዲሁም ማየት ወይም መናገር አለመቻል

እነኝህ የበሽታ ምልክቶችን ካስተዋሉ እያንዳንዷ ደቂቃ ትልቅ ትርጉም አላት፡፡ የደም መርጋታ የበሽታ (stocke  ) ወይም አንዳንድ ጊዜ  ministrocke በሚል መጠሪያ transient ischemic attack እንደሚከሰት የማስጠንቀቂያ ምልክቶች ናቸው፡፡

ቀጣዮቹን ምልክቶች ካስተዋሉ ወዲያውኑ የሐኪም እርዳታ ማግኘት እንዳለብዎት ይወቁ፡፡

    • በአንደኛው የሰውነትዎ ጎን ድንገተኛ ዝለት ወይም የመደንዘዝ ስሜት
    • ድንገተኛ የዕይታ መደብዘዝ፣ የዓይን ብርሀን መድከም ወይም ማየት አለመቻል
    • ባልታወቀ ምክኒያት የሚያጋጥም መጫጫን፣ መቆም አለመቻል፣ ወይም በድንገት መውደቅ
    • ድንገተኛ ከባድ ራስ ምታት ያስገድዱ የጤና ችግሮች መካከል ቃርና irritable bowel syndrome፣                      እንዲሁም የሬብ መዘጋት፣ የጉሮሮ ካንሰር ወይም የጨጓራ መታወክ የመሰሉ ከባድ ሕመሞች ተጨቃሾች ናቸው፡፡

 

    1. የብርሃን ብልጭታ

በድንገት የብርሃን ብልጭታዎችን የተመለከቱ  ከመልስዎት የሬቲና ከመደበኛ ቦታው መነሳትን ወይም መልቀቅን አመላካች ሊሆን ይችላል፡፡ ወዲያውኑ የህክምና እርዳታ ካገኙ ሊያጋጥም የሚችለውን የዓይን ስውርነትን አደጋ ሊከላከሉ ይችላል፡፡

    1. ትንሽ እንደበሉ መጥገብ

ከአንድ ሳምንት በላይ የዘለቀ  ከሌላው ጊዜ በበለጠ ፍጥነት መጥገብ የጤና ባለሙያ ትኩረት የሚያሻው ችግር ነው፡፡ ችግሩ እንደ ማቅለሽለሽ፣ ትውከት፣ ግሳት፣ትኩሳት እንዲሁም ክብደት መቀነስ ወይም መጨመር በመሰሉ የበሽታ ምልክቶች የታጀበ ሊሆን ይችላል፡፡ እነኝህን ምልክቶች ካስተዋሉ ይህንኑ ለሐኪምዎ መግለጽ እንዳለብዎት አይዘንጉ፡፡

    1. ሲነኩት የሚያቃጥል፣ የቀላ ወይም የበጠ መገጣጠሚያ

ከመገጣጠሚያዎችዎ መካከል አንዱ ካበጠ ወይም ከቀላ  አስቸኳይ ጊዜ ሕክምና   የሚያስፈልገው የመገጣጠሚያ ኢንፌክሽን ለመኖሩ ጠቋሚ ሊሆን ይችላል፡፡ ይህን ችግር  ከሚያስከትሉት ሌሎች የጤና እክሎች መካከል ረህና የአንጓ ብግነት (አርትራይቲስ) ዋነኞቹ ናቸው፡፡

 

ምንጭ፡- እቴጌ ቁ፡17 2002 ዓ.ም