Notice: Undefined index: title in /home/hawassao/public_html/subpage_articles.php on line 174

Notice: Undefined index: title in /home/hawassao/public_html/subpage_articles.php on line 176

Notice: Undefined index: title in /home/hawassao/public_html/subpage_articles.php on line 216

Notice: Undefined index: title in /home/hawassao/public_html/subpage_articles.php on line 218

የወፍራም ሴቶችን ውበት የሚያወጡ 10 ዘዴዎች

 

የወፍራም ሴቶችን  ውበት የሚያወጡ 10 ዘዴዎች

 

Image result for fatty

 

    1. ሁሌ ባለረዥም ተረከዝ ጫማ ማድረግ

በእርግጥ፣ ባለረዥም ተረከዝ ጫማ በጣም ውድ ሊሆንና  ያደረገችውን ሴት ሊጎዳት እንደሚችል የታወቀ ነው፡፡ ይሁንና አስፈላጊ ነው፡፡  እንዲህ ዓይነቱ ጫማ የፈለፈው አይነት የሰውነት ቅርጽ ቢኒርሽም፣ ለማንኛውም አይነት ልብስ የአማላይነትን ድባብ እንደሚያላብስ ምንም ጥርጥር የለውም፡፡ ከዚህ በተጨማሪም፣ እግሮችሽን ይበልጥ  ረዥም በማስመሰል ሰውነትሽን ቀጠን አድርጎ ሊያሳይልሽ ይችላል፡፡

 

    1. የጓደኞችሽን አመጋገብ በቅርበት መከታተል

ወደ አንድ ምግብ ቤት ሄዳችሁ ጓደኛሽ የካሎሪው መጠን ከፍተኛ የሆነ  አንድ ድንች ጥብስ  የመሰለ ምግብ ስታዝ ታባያታለሽ፣ አሊያም የራስሽን ለማዘዝ አታቅማሚ ይሆናል፡፡ ለሌላ አጋጣሚ ቢራ ወይም ድራፍት ደጋግማ ከምትጎነጭ ጓደኛሽ  ጋር ስትውዪ  የሷን ፈለግ ለመከተል ውጥሽ ይገፋፋሽ ይሆናል፡፡  በእርግጥ ከእነኝህ ሴቶች ጋር አብረሽ መሆን የለብሽም የሚል ሰው አይኖርም፡፡ ይሁንና፣ ያንቺን ያህል ስለ ውበት ዕውቀት ከሌላቸው ሰዎች ጋር ስትሆኚ  ዙሪያ ገባሽን በተመለከተ ከበፊቱ የበለጠ ግንዛቤ ልታዳብሪ ይገባል፡፡

 

    1. የማያምርብሽን ነገር ማወቅ

ተራ ነጭ ቲ-ሸርትና ጂንስ በመልበስ ወንዶች በአድናቆት ተሞልተው ምራቃቸውን እንዲወጡ የምታደርግ ሴት አታውቅም?

ይህ የሚሆንበት ምክኒያት የምትለብሽው ልብስ ብቻ  ሳይሆን አለባበስሽም ትልቅ ቦታ ያለው በመሆኑ ነው፡፡ እንደ ስፔንሰር አባባል፣  የምትለብሽው ማንኛውም ልብስ ማንኛውም ልብስ የሰዎችን  ቀልብ የሚስብ ወይም ዘወር ብለው እንኳን እንዳያዩሽ የሚያደርጉ ምልክቶችን ይሰጣል፡፡ ስለዚህም ከአምስት ዓመታት በፊት  ታላቅ ቅናሽ  የሚል ማስታወቂያ ከለጠፈ መደብር  በቅናሽ ከገዛሽው ሹራብ ቢሆንም እንኳን የበለጠ ሙገሳ የሚያስገኝልሽንና ጥሩ ስሜት የሚሰጥሰሽን አለባበስ መከተል እንዳለብሽ አትዘንጊ፡፡

 

    1. ለምግብሽ መሉ ትኩረት መስጠት

የምትበይውን ምግብ በተመለከተ በአንድ ጊዜ የተለያ ነገሮችን ለማድረግ መሞከር የለብሽም፡፡ ለምሳሌ የምትወጂውን ፊልም በምትመለከችበት ወቅት ምግብ የምትበዪ ከሆነ፣  ከወትሮው ይልቅ ትመገብያለሽ  ወይም መብላትሽንም ጭራሽ ልትረሺ ትችያለሽ፡፡  ከዚህም በተጨማሪ፣  ምግብ መብላት ያለብሽ  ሐዘን ሲሰማሽ፣  በነገሮች ስትሰላቺ፣ ሲጨንቅሽ ወይም  ስትሰክሪ ሳይሆን ሲርብሽ እንደሆነ መዘንጋት የለብሽም፡፡ ምግብን በተመለከተ መመራት ያለብሽ በስሜትሽ ሳሆን በሆድሽ መሆን አለበት፡፡

 

    1. ማራኪ የውስጥ ሱሪ መልበስ

ከላይ ወንዶችን የሚያማልል አለባበስ ብትከተይም፣ ከሰር ጥሩ ስሜት የሚሰጥሽን የውስጥ ሱሪ መልበስ ይኖርብሻል፡፡ ማራኪ የውስጥ ሱሪሽን ከወንድ ጓደኛሽ  ጋር በምትወጭባቸው ምሽቶችና በግብዣዎች ላይ ብቻ የምታደርጊ ከሆነ፣  በእነኝህ ጊዜያት ጥሩ ስሜት የሚያላብስ  ነገር በመደበኛው የስራ ቀን ምን አይነት ስሜት  እንደሚሰጥሽ አስቢው፡፡  ሁላችንም የሚያምር ውስጥ ሱሪ ቀኑን በሙሉ እንዲደብርሽ    መሆኑን የምናውቅ እንደ መሆናችን መጠን፣ በመሳቢያሽ ውስጥ የተለያዩ ማራኪ ውስጥ ሱሪዎች መኖራቸውን አረጋግጪ፡፡

 

    1. የታሸጉ ምግቦችን መቀነስ

ገበያ ወጥተሽ ምግብሽን ለመግዛት ስትወስኚ በፕላስቲክ፣ በቆርቆሮ፣ በወረቀት፣ ወዘተ….. ከታሸጉ ምግቦች በተቻለሽ አቅም መራቅ ይኖርብሻል፡፡ ምግብ አነስተኛ ኬሚካል፣ ማቅለሚያ፣ አርቲፊሻል  ቅመም፣ ወዘተ…. ያለው ከሆነ፣ ይበልጥ ለጤና ተስማሚ እንደሆነ ብዙም አያጠራጥርም፡፡

 

    1. ጥቁር ብርሃን የማያስተላልፍ ታይት መልበስ

ጥቁር ታይት የማያስተላልፍ ታይት ከወገብሽ በታች ልዩ ውበት የሚያላብስ ዓይነት ልብስ ነው ይህ አይነቱ ልብስ የተለያዩ ጥቅሞች አሉት፡፡ በመጀመሪያ ረገድ እግሮችሽን ቀጭን ያስመስላቸዋል፡፡  በቀጣይነትም ቀዝቀዝ ባለ አየር ቢለበስ የሰውነትሽን ሙቀት  እንዳያመልጥ ያግዛል፡፡  አብዛኛው በርካሽ የሚገኝ ከመሆኑም ሌላ፣ በእግርሽ ላይ የሚታዩ የተለያዩ እንከኖችን ይደብቃል፡፡

    1. የምትመገቢውን ምግብ መጠን መቆጣጠር

ከአራት አሜሪካውያን መካከል አንዱ የፈለገውን ያህል የምግብ መጠን  ቢቀርብለትም ሁሉንም ጠራርጎ ይበላል፡፡ ደመወዝንና የጫማ ተዘከዝ ርዝመትን በተመለከተ ትልቅ መሆን ተመራጭ ቢሆንም፣ ትልቅነት ከምግብ መጠን ጋር አይጣጣምም፡፡ ስለዚህም ከፎርማጆ ጋር አብሮ የተዘጋጀ ፓስታ ለመብላት  በምትቀመጭበት ወቅት ሳሕኑ ላይ ብቻ ሳይሆን ጠረጳዛው ላይ  የቀረበውን በሙሉ ጠራርገሽ መመገብ እንደማይጠበቅብሽ አትርሺ፡፡

 

    1. አመጋገብሽን መከታተል

ሳታውቂው ያልፈለግሽውን ዓይነት ምግብ ልትመገቢ ትችያለሽ፡፡ ለምሳሌ ፣ምሳሽን  ሰላጣ ለመብላት ወስነሽ ይሆናል እንበል፡፡ በዚህም መሰረት፣ ስፒናች፣ የተፈቀፈቀ  ካሮትና ቲማቲም መርጠሻል፡፡ ይሁንና፣ በቀጣይነት ልብ ላትይው ሳሕንሽ ላይ ያለውን ምግብ ከተቀቀለ እንቁላል፣ በእንፋሎት ከደረቀ የአሳማ ስጋና ከወተት ከተሰራ ማጣ ፈጫ ጋር ታደባልቂዋለሽ፡፡ ይህን ለመሰለ አመጋገብ በተቻለ አቅም መራቅ ይኖርብሻል፡፡

 

    1. ስብ ሳይሆን ስብ አቃጣይ ምግቦችን መምረጥ

በተለያዩ ምክኒያቶች የተወሰኑ የምግብ ዓይነቶች አስደሳች ስሜት ይሰጡናል፡፡ ይሁንና፣ ቀጣዮቹን የምግብ ዓይነቶች በየዕለቱ በምትመገቢው ማዕድ ውስጥ ማካተቱ ጥሩ ነው፣ ትርንጎ፣ ፖም፣ የወይራ ዘይት፣ ተልባ፣ ሱፍና ነጭ ሽንኩርት፡፡ (በዙሪያሽ ያሉትን ሰዎች ጠረንሽ እንዳያርቃቸው  የነጭ ሽንኩርት አጠቃቀምሽ የተመጠነ መሆን አለበት፡፡

 

 ምንጭ፡- እቴጌ ቁ. 17 2002 ዓ.ም