Notice: Undefined index: title in /home/hawassao/public_html/subpage_articles.php on line 216

Notice: Undefined index: title in /home/hawassao/public_html/subpage_articles.php on line 218

ሽንብራ ዓሳ ወጥ አሰራር

የሽንብራ ዓሳ ወጥ አሰራር

አስፈላጊ 

    • የሽንብራ ዱቄት 
    • አዋዜ 
    • ዘይት 
    • ሽንኩርት
    • በርበሬ
    • ነጭ ሽንኩርት 
    • ዝንጅብል 
    • ኮረሪማ 
    • ጨው
 
 
 
አሰራር  
    1. የሽንብራውን ዱቄት እንደስፈላጊነቱ መጥነን ጎድጎድ ባለ ሳህን እናረግና አዋዜ ፤ ዘይት እና ጨው ዱቄቱ ላይ መጨመር
    2. ከዛም በደንብ ማሸት እና ከታሸው ላይ እየቆነጠሩ በሚፈለገው ቅርፅ መቁረጥ
    3. መጥበሻ ላይ ዘይት ጨምሮ እያገላበጡ መጥበስ እና ዘርጋ ያለ ሳህን ላይ የጠተበሰውን አውጥቶ ማድረግ  
    4. በርከት ያለ ሽንኩርት አድቅቆ ከትፎ ለማብሰል አመቺ በሆነ ድስት መጣድ እና ዘይት እና በርበሬ ጨምሮ ማቁላላት 
    5. ቁሌቱ ላይ ነጭ ሽንኩርት እና ዝንጅብል ጨምሮ ለብ ያለ ውሃ ጠብ እያረጉ በደንብ ማቁላላት 
    6. ቁሌቱላይ የተጠበሰውን ሽንብራ አሳ መጨመር እና ኮረሪማ ነስንሶ ከቁሌቱ ጋር ማዋሃድ 
    7. አሳው እንዳይፈራርስ ተጠንቅቆ ማማሰል እናም ቁሌቱ አሳው ውስጥ እስኪገባ ማቆየትእና ጨዉን አስተካክለን ማውጣት

      ምንጭ፡- ከባህላዊ ምግብ አዘገጃጀት መጻፍ የተወሰደ