እሩዝ በእንቁላል አሰራር

 

እሩዝ በእንቁላል አሰራር

 

 

 

ብዙ ጊዜ ልጆች ከ 1 ዓመትታቸው በኃላ ምግብ የሚመርጡበትና የመብላት ፍላጎታቸው በትንሹ የሚወርድበት ጊዜ በመሆኑ ለዓይን የሚማርካቸውና ሲበሉት የሚጣፍጣቸው ምግብ ማዘጋጀት ይመከራል፡፡

ከ 1 ዓመት በላይ ለሆኑና ቤተሰብም ሊመገባቸው የሚችል ቀለል ያለ አሰራር ብናይ.

 • 50 ግራም ሩዝ

 • 2 መካከለኛ ቲማቲም በደቃቁ የተከተፈ

 • 2 እንቁላል

 • 1 መካከለኛ ሽንኩርት በደቃቁ የተከተፈ

 • 2 ፍሬ ነጭ ሽንኩርት

 • ጨው

 

አሰራሩ

 

1. ውሀ ሲፈላ ትንሽ ጨው ጨምሮ እሩዝ ቀቅሎ ለብቻው ማስቀመጥ

 2. በመጥበሻ ዘይት አግሎ ሽንኩርትና ነጭ ሽንኩርቱን ጨምሮ ማቁላላት

 3. ቲማቲሙን መጨመር በደንብ ሲቁላላ ትንሽ ጨው መጨመር

 4. የተመታውን እንቁላል ጨምሮ ማፈርፈር

 5. የተቀቀለውን እሩዝ ጨምሮ በደንብ ማዋሀድና ማቅረብ

 

ምንጭ፡- ከባህላዊ ምግብ አዘገጃጀት መጻፍ የተወሰደ