የዶናትስ አሰራር

የዶናትስ አሰራር
 
አስፈላጊ 
  • 4  ብርጭቆ ፉርኖ ዱቄት 
  •  1  ብርጭቆ ስኯር 
  • 4  የሾርባ  ማንኪያ  የገበታ  ቅቤ 
  • 3  የሻይ ማንኪያ ቤኪንግ ፓውደር
  • 3   ዕቁላል 
  • 2  የሾርባ ማንኪያ ዘይት 
  • 1  ብርጭቆ ወተት 
  • 1  የሻይ  ማንኪያ  ጨው
  • 1 የሾርባ ማንኪያ ቫኔላ
  • ቸኮሌት (እንደስፈላጊነቱ) 
  • ግማሽ  ብርጭቆ ሞቅ ያለ  ውሃ 
 
አሰራር
  1. ጎድጎድ ባለ ሳህን የሞቀውን ውሃ መገልበጥ እናም ቤኪንግ ፓውደሩን ጨመሮ መበጥበጥ እና ለ 5ደቂቃ መጠበቅ 
  2. እርሾው ሲፈላ : ወተት ፤ ግማሽ ብርጭቆ ስኯር ፤ ጨዉ ፤ እንቁላል ፤ 2 ማንኪያ ቅቤው እና ዱቄቱን አንድ ላይ መቀላቀል(ማቡካት) 
  3. ሊጡ መወፈርም መቅጠንም የለበትም
  4.   ቡኮውን ተለቅ ባለ ጎድጏዳ ሳህን ውስጥ አድርጎ መሸፈን እና ኩፍ እስኪል መጠበቅ (ሙቀት ያለበት ቦታ ማሥቀመጡ ቶሎ ኩፍ እንዲል ይረዳዋል)
  5. ኩፍ ሲልልን ሰፋ ባለ መክተፊያ ላይ ቡኮውን አድርጎ በመዳመጫ መለጠጥ (በጣም መሳሳት የለበትም)
  6. ከዛም በቅርፅ ማውጫ መቁረጥ እና የቆረጥነውን ቡኮ በድጋሚ ኩፍ እስኪል መጠበቅ
  7. ለመጥበስ አመቺ በሆነ እቃ ላይ ዘይት በብዛት መጨመር እና የቆረጥነውን ዶናት አስገብተን መጥበስ
  8. የተጠበሠው ዶናት ዘይቱ እንዲንጠፈጠፍ ዓመቺ ቦታ ላይ ማስቀመጥ
 
 
ለክሬሙ 
  1.  * 2 የሾርባ ማንኪያ ቅቤ ፤ ግማሽ ብርጭቆ ስኯር እና ቫኒላ ካስፈለገም ቸኮሌት እሳት ላይ በድስት እያሞቁ በደንብ እስኪዋሃድ መምታት
  2. ከዛም ድስቱን ከ እሳቱ ላይ ማውረድ እና 4 የሻይ ብርጭቆ የሞቀ ውሃ ጨምሮ በድጋሚ መምታት 
  3. ከዛም እንዲንጠፈጠፍ ያስቀመጥነዉን ዶናት እያንዳንዱን በአንድ በኩል ብቻ እየነከርን ማውጣት
 

ምንጭ፡- ከባህላዊ ምግብ አዘገጃጀት መጻፍ የተወሰደ