በቤንች ማጂ ዞን ከሚገኙ 10 ወረዳዎች አንዱ የሆነው የሜኤኒት ጎልዲያ ወረዳ

የሜኤኒት ጎልዲያ መስህቦች

 

 

 በቤንች ማጂ ዞን ከሚገኙ 10 ወረዳዎች አንዱ የሆነው የሜኤኒት ጎልዲያ ወረዳ ርእሰ ከተማ ባቹማ ትባላለች፡፡ ባቹማ ከአዲስ አበባ በ591 ኪሎ ሜትር ከሚዛን ደግሞ በ87 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ስትገኝ ወረዳው የሜኤኒት ብሔረሰብ መገኛም ነው፡፡

 

የባንዲሊ  የተፈጥሮ ዋሻ

 

በቤንች ማጂ ዞን የቱሪስቶችን ቀልብ የሚስቡ በርካታ ተፈጥሮአዊና ባህላዊ መስህቦች ይገኛሉ፡፡ በዞኑ በየጊዜው አዳዲስ የቱሪስት መስህቦችን ማግኘት የተለመደ ክስተት ነው፡፡ ከዚህ ቀደም በመኤኒት ጎልዲያ ወረዳ መኖሩ የማይታወቅ በይዘቱና በመስህብነቱ ወደር የማይገኝለት የተፈጥሮ ዋሻ በአካባቢ ነዋሪዎች ጥቆማ ተገኝቷል፡፡ ዋሻውን የአካባቢ ነዋሪዎች ቀፎ ለመስቀልና የጫካ ማር ከዱር ለመቁረጥ በሚንቀሳቀሱበት ወቅት እንዳገኙት ይናገራሉ፡፡ በመሆኑም የተፈጥሮ መስህቡን በማጥናት በዞኑ የተፈጥሮ መስህቦች ዝርዝር ውስጥ ሊካተት ችሏል፡፡

ምንጭ፡-tubamegazine